የበትረሳረንሰት ክፍለስፍን

የበትረሳረንሰት ክፍለስፍን (Lycopodiophyta ወይም Lycophyta) ከአትክልት ስፍን ውስጥ አንድ የአትክልት ክፍለስፍን ነው።

የአረንቋ በትረሳርንሰት

እንደ ሳርንስት በመምሰል፣ ዱኬ ወለድ ዕጽዋት ናቸው እንጂ ዘር የላቸውም። ነገር ግን እንደ ሳርንስት ሳይሆኑ፣ ሸንዳማ ዕጽ ናቸው። እንደ ሌሎቹ ሸንዳማ ዕጽዋት ሁሉ ሳይሆኑ፣ ነጠላ ሸንዳ ብቻ አላቸው።

አሁን በዚህ ክፍለስፍን 1,290 ሕያው ዝርዮች ይኖራሉ። በዘመናዊ ሥነ ሕይወት ጥናት ዘንድ የክፍለስፍኑ ሶስት መደባት እነዚህ ናቸው፦

  • የበትረሳርንሰት መደብ (Lycopodiopsida) - በትረሳርንሰትአስታ ሳርንስት
  • የላባ ተክል መደብ (Isoetopsida) - ላባ ተክልዛላ ሳርንስት፣ እና በቅድመ-ታሪክ የጠፋው ታላላቁ ቅርፊት ዛፍ
  • እባብ-አሳ-ሳር ቅጠል (Zosterophyllopsida) - በቅድመ-ታሪክ የጠፋ መደብ
በቅድመ-ታሪክ የጠፋው የቅርፊት ዛፍ ልጥ ቅሪት። የቅርፊት ዛፍ እስከ 30m ድረስ ሊቆም ቻለ።
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.