የነጩ ቢትወደድ መጽሐፍ
የነጩ ቢትወደድ መጽሐፍ (እንግሊዝኛ፦ The Book of the White Earl ወይም Bodleian Laud Misc. MS 610) በ1450 ዓም ገደማ በአይርላንድ የተፈጠረ ሥነ-ጽሑፋዊ፣ ሃይማኖታዊ ወይም አፈታሪካዊ ክምችት ነው። በአይርላንድኛ በ«ነጩ ቢትወደድ» ጄምዝ በትለር፣ የኦርሞንድ 4ኛው እርል (ቢትወደድ) ሲሆን በርሱ ደጋፍ ነበር የተጻፈው። በክምችቱ ውስጥ «የወንጉስ ሰማዕታት ዝርዝር» በ820 ዓም ያህል እንደተቀነባበረ ይታስባል፤ ሌሎች ክፍሎች ከ1160 ዓም እንደ ሆኑ ይመስላል።
በይዞታው መጨረሻ «የላውድ አቆጣጠሮች» የተባለው ሰነድ ይጨመራል፤ ይህ የአይርላንድ ነገሥታት ዝርዝር በሙሉ ከስላንጋ እስከ ማይል ሰቅናይል ማክ ዶምናይል ድረስ ይሰጣል። እነዚህ የአይርላንድ ከፍተኛ ነገስታት እስከ 1014 ዓም ገዙ፤ ሰነዱም በዚያው ወቅት ያህል አሁን ከጠፋው «የካሼል መዛሙርት» ዝርዝር ተቀድቶ እንደ ተዘጋጀ ይታመናል። ስለዚህ በሌቦር ጋባላ ኤረን ከተገኘው ዝርዝር (1065 ዓም ግድም) ይልቅ ጥንታዊ ነው።
ውጭ መያያዣ
- መጽሐፉ በአይርላንድኛ
- የላውድ አቆጣጠሮች ክፍል
- የአይርላንድ አፈታሪካዊ ነገሥታት ዝርዝሮች Archived ሜይ 26, 2014 at the Wayback Machine
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.