የሉቃስ ወንጌል

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ቅዱስ ሉቃስ እንደ ጻፈው። ቅዱስ ሉቃስ ሙያው ጥንቃቄ የሚፈልግ ስለነበረ ወንጌልንም ሲፅፍ ትልቅ ጥንቃቄ እያደረገ ለምሳሌ ከቃሉ ምንጭ ከሆነች ከእመቤታችን ቅድስ ድንግል ማርያም ዘንድ ድረስ እየሄደ በማነጋገር እንደፃፈ ይነገርለታል። በተጨማሪም ሐዋርያት ሥራ የፃፈ ይሄው ቅዱስ ነው። ከቅዱስ ጳውሎስ ጋርም ብዙ ቦታዎች ላይ ተገኝቷል። እንዲሁም ጌታ ከሙታን ተለይቶ ምትን ድል አድርጎ በተነሣበት ቀን በፍኖተ ኢማሑስ (በኢማሑስ መንገድ) ጌታችን ከተገለጠላቸው ከሁለቱ ደቀመዛሙርት አንዱ ቅዱስ ሉቃስ እንደሆነ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ያስተምራሉ።

ቅ.ሉቃስ ወንጌላዊው
ሉቃስ የሥጋና የነፍስ ሐኪም
ሉቃስ የሥጋና የነፍስ ሐኪም
የቅዱስ ሉቃስ ወንጌል
የፀሐፊው ስም ሉቃስ
የተወለደበት ቀን ጥቅምት ፳፪ በ፩ኛው ክፍለዘመን
የተወለደበት ቦታ አንፆኪያ (ሶርያ)
ሥራው ሐኪም፣ወንጌል ፀሐፊ፣ሰባኪ፣ሰዐሊ
ያረፈበት ቀን መጋቢት ወር ፹፬ ዓ.ም ግሪክ(ቦዬሺያ)ከተማ
በዓለ ንግሥ ጥቅምት ፳፪
ምልክቱ
የሚከበረው በዓለም ክርስቲያን ሕዝብ
የጻፈው ወንጌል ፳፬ ምዕራፍ

ወንጌላዊው ሉቃስ በላህም ይመሰላል ምክኒያቱም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከብቶች በረት መወለዱን በእለተ ልደቱም የከብት እረኞች ከመላእክት ጋር መዘመራቸውን ከሌሎች ወንጌላውያን ሠፋ አድርጐ ስለሚተርክ ነው። (ሉቃ፡፪.፰-፲፰) ከዚህ ሌላ ላህም በብሉይ ኪዳን የመሥዋዕት እንሰሳ ሲሆን ሉቃስም የክርስቶስን መስዋትነት በፍሪዳ ምሳሌ ጽፎአል። (ሉቃ፡፲፭.፳፪-፳፬) ላም የቀንድ ከብት ነው በዚሁም መሠረት ወንጌላዊው ሉቃስ ክርስቶስ ቀርነ መድኃኒት እንደሆነ ነብዩ ዘካርያስ የተናገረውን ትንቢት በመግለጽ ስለፃፈ የላህም ምልክት እንደተሰጠው መተርጉማን ሊቃውንት ይናገራሉ[1]

ቅዱስ ሉቃስ ሰዐሊም ነበረ ፣ ቅድስት ማርያም ምስለ ፍቁርን ታቅፋ ሲስላት



የሉቃስ ወንጌል

ምዕራፍ ፩

1-4፤የከበርኽ፡ቴዎፍሎስ፡ሆይ፥ከመዠመሪያው፡በዐይን፡ያዩትና፡የቃሉ፡አገልጋዮች፡የኾኑት፡ እንዳስተላለፉልን፥በኛ፡ዘንድ፡ስለተፈጸመው፡ነገር፡ብዙዎች፡ታሪክን፡በየተራው፡ ለማዘጋጀት፡ስለ፡ሞከሩ፥እኔ፡ደግሞ፡ስለተማርኸው፡ቃል፡ርግጡን፡እንድታውቅ፡ በጥንቃቄ፡ዅሉን፡ከመዠመሪያው፡ተከትዬ፡በየተራው፡ልጽፍልኽ፡መልካም፡ኾኖ፡ታየኝ።

ቅዱስ ሉቃስ ወንጌልን ሲፅፍ

5፤በይሁዳ፡ንጉሥ፡በሄሮድስ፡ዘመን፡ከአብያ፡ክፍል፡የኾነ፡ዘካርያስ፡የሚባል፡አንድ፡ካህን፡ነበረ፤ሚስቱም፡ ከአሮን፡ልጆች፡ነበረች፥ስሟም፡ኤልሳቤጥ፡ነበረ። 6፤ኹለቱም፡በጌታ፡ትእዛዝና፡ሕግጋት፡ዅሉ፡ያለነቀፋ፡እየኼዱ፥በእግዚአብሔር፡ፊት፡ ጻድቃን፡ነበሩ። 7፤ኤልሳቤጥም፡መካን፡ነበረችና፡ልጅ፡አልነበራቸውም፤ኹለቱም፡በዕድሜያቸው፡ አርጅተው፡ነበር።8፤ርሱም፡በክፍሉ፡ተራ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ሲያገለግል፥ 9፤እንደ፡ካህናት፡ሥርዐት፡ወደጌታ፡ቤተ፡መቅደስ፡ገብቶ፡ለማጠን፡ዕጣ፡ደረሰበት። 10፤በዕጣንም፡ጊዜ፡ሕዝቡ፡ዅሉ፡በውጭ፡ቆመው፡ይጸልዩ፡ነበር። 11፤የጌታም፡መልአክ፡በዕጣኑ፡መሠዊያ፡ቀኝ፡ቆሞ፡ታየው። 12፤ዘካርያስም፡ባየው፡ጊዜ፡ደነገጠ፥ፍርሀትም፡ወደቀበት። 13፤መልአኩም፡እንዲህ፡አለው፦ዘካርያስ፡ሆይ፥ጸሎትኽ፡ተሰምቶልኻልና፥አትፍራ፤ ሚስትኽ፡ኤልሳቤጥም፡ ወንድ፡ልጅ፡ትወልድልኻለች፥ስሙንም፡ዮሐንስ፡ትለዋለኽ። 14፤ደስታና፡ተድላም፡ይኾንልኻል፥በመወለዱም፡ብዙዎች፡ደስ፡ይላቸዋል። 15፤በጌታ፡ፊት፡ታላቅ፡ይኾናልና፥የወይን፡ጠጅና፡የሚያሰክር፡መጠጥ፡አይጠጣም፤ ገናም፡በእናቱ፡ማሕፀን፡ ሳለ፡መንፈስ፡ቅዱስ፡ይሞላበታል፤ 16፤ከእስራኤልም፡ልጆች፡ብዙዎችን፡ወደ፡ጌታ፡ወደ፡አምላካቸው፡ይመልሳል። 17፤ርሱም፡የተዘጋጁትን፡ሕዝብ፡ለጌታ፡እንዲያሰናዳ፥የአባቶችን፡ልብ፡ወደ፡ልጆች፡የማይታዘዙትንም፡ ወደጻድቃን፡ጥበብ፡ይመልስ፡ዘንድ፡በኤልያስ፡መንፈስና፡ኀይል፡በፊቱ፡ይኼዳል። 18፤ዘካርያስም፡መልአኩን፦እኔ፡ሽማግሌ፡ነኝ፥ሚስቴም፡በዕድሜዋ፡አርጅታለችና፥ይህን፡በምን፡ ዐውቃለኹ፧አለው። 19፤መልአኩም፡መልሶ፦እኔ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡የምቆመው፡ገብርኤል፡ ነኝ፥እንድናገርኽም፡ይህችንም፡ የምሥራች፡እንድሰብክልኽ፡ተልኬ፡ነበር፤ 20፤እንሆም፥በጊዜው፡የሚፈጸመውን፡ቃሌን፡ስላላመንኽ፥ይህ፡ነገር፡እስከሚኾን፡ቀን፡ድረስ፡ዲዳ፡ ትኾናለኽ፡መናገርም፡አትችልም፡አለው። 21፤ሕዝቡም፡ዘካርያስን፡ይጠብቁት፡ነበር፤በቤተ፡መቅደስም፡ውስጥ፡ስለ፡ዘገየ፡ይደነቁ፡ነበር። 22፤በወጣም፡ጊዜ፡ሊነግራቸው፡አልቻለም፥በቤተ፡መቅደስም፡ራእይ፡እንዳየ፡አስተዋሉ፤ርሱም፡ ይጠቅሳቸው፡ነበር፤ድዳም፡ኾኖ፡ኖረ። 23፤የማገልገሉም፡ወራት፡ሲፈጸም፡ወደ፡ቤቱ፡ኼደ። 24-25፤ከዚህም፡ወራት፡በዃላ፡ሚስቱ፡ኤልሳቤጥ፡ፀነሰችና፦ነቀፌታዬን፡ከሰው፡መካከል፡ያስወግድልኝ፡ ዘንድ፡ጌታ፡በተመለከተበት፡ወራት፡እንዲህ፡አድርጎልኛል፡ስትል፡ራሷን፡ዐምስት፡ወር፡ሰወረች። 26፤በስድስተኛውም፡ወር፡መልአኩ፡ገብርኤል፡ናዝሬት፡ወደምትባል፡ወደ፡ገሊላ፡ከተማ፥ 27፤ከዳዊት፡ወገን፡ለኾነው፡ዮሴፍ፡ለሚባል፡ሰው፡ወደ፡ታጨች፡ወደ፡አንዲት፡ድንግል፡ከእግዚአብሔር፡ ዘንድ፡ተላከ፥የድንግሊቱም፡ስም፡ማርያም፡ነበረ። 28፤መልአኩም፡ወደ፡ርሷ፡ገብቶ፦ደስ፡ይበልሽ፥ጸጋ፡የሞላብሽ፡ሆይ፥ጌታ፡ከአንቺ፡ጋራ፡ነው፤አንቺ፡ ከሴቶች፡መካከል፡የተባረክሽ፡ነሽ፡አላት። 29፤ርሷም፡ባየችው፡ጊዜ፡ከንግግሩ፡በጣም፡ደነገጠችና፦ይህ፡እንዴት፡ያለ፡ሰላምታ፡ነው፧ብላ፡ዐሰበች። 30፤መልአኩም፡እንዲህ፡አላት፦ማርያም፡ሆይ፥በእግዚአብሔር፡ፊት፡ጸጋ፡አግኝተሻልና፥አትፍሪ። 31፤እንሆም፥ትፀንሻለሽ፡ወንድ፡ልጅም፡ትወልጃለሽ፥ስሙንም፡ኢየሱስ፡ትዪዋለሽ። 32፤ርሱ፡ታላቅ፡ይኾናል፡የልዑል፡ልጅም፡ይባላል፥ጌታ፡አምላክም፡የአባቱን፡የዳዊትን፡ዙፋን፡ይሰጠዋል፤ 33፤በያዕቆብ፡ቤትም፡ላይ፡ለዘለዓለም፡ይነግሣል፥ለመንግሥቱም፡መጨረሻ፡የለውም። 34፤ማርያምም፡መልአኩን፦ወንድ፡ስለማላውቅ፡ይህ፡እንዴት፡ይኾናል፧አለችው። 35፤መልአኩም፡መልሶ፡እንዲህ፡አላት፦መንፈስ፡ቅዱስ፡ባንቺ፡ላይ፡ይመጣል፥የልዑልም፡ኀይል፡ ይጸልልሻል፡ስለዚህ፡ደግሞ፡ከአንቺ፡የሚወለደው፡ቅዱስ፡የእግዚአብሔር፡ልጅ፡ይባላል። 36፤እንሆም፡ዘመድሽ፡ኤልሳቤጥ፥ርሷ፡ደግሞ፡በእርጅናዋ፡ወንድ፡ልጅ፡ፀንሳለች፥ለርሷም፡መካን፡ትባል፡ ለነበረችው፡ይህ፡ስድስተኛ፡ወር፡ነው፤ 37፤ለእግዚአብሔር፡የሚሳነው፡ነገር፡የለምና። 38፤ማርያምም፦እንሆኝ፡የጌታ፡ባሪያ፡እንደ፡ቃልኽ፡ይኹንልኝ፡አለች።መልአኩም፡ከርሷ፡ኼደ። 39፤ማርያምም፡በዚያ፡ወራት፡ተነሥታ፡ወደ፡ተራራማው፡አገር፡ወደይሁዳ፡ከተማ፡ፈጥና፡ወጣች፥ 40፤ወደዘካርያስም፡ቤት፡ገብታ፡ኤልሳቤጥን፡ተሳለመቻት። 41፤ኤልሳቤጥም፡የማርያምን፡ሰላምታ፡በሰማች፡ጊዜ፡ፅንሱ፡በማሕፀኗ፡ውስጥ፡ዘለለ፤በኤልሳቤጥም፡መንፈስ፡ ቅዱስ፡ሞላባት፥ 42፤በታላቅ፡ድምፅም፡ጮኻ፡እንዲህ፡አለች፦አንቺ፡ከሴቶች፡መካከል፡የተባረክሽ፡ነሽ፥የማሕፀንሽም፡ፍሬ፡ የተባረከ፡ነው። 43፤የጌታዬ፡እናት፡ወደ፡እኔ፡ትመጣ፡ዘንድ፡እንዴት፡ይኾንልኛል፧ 44፤እንሆ፥የሰላምታሽ፡ድምፅ፡በዦሮዬ፡በመጣ፡ጊዜ፡ፅንሱ፡በማሕፀኔ፡በደስታ፡ዘሏልና። 45፤ከጌታ፡የተነገረላት፡ቃል፡ይፈጸማልና፥ያመነች፡ብፅዕት፡ናት። 46፤ማርያምም፡እንዲህ፡አለች

47፤ነፍሴ፡ጌታን፡ታከብረዋለች፥መንፈሴም፡በአምላኬ፡በመድኀኒቴ፡ሐሴት፡ታደርጋለች፤ 48፤የባሪያዪቱን፡ውርደት፡ተመልክቷልና።እንሆም፥ከዛሬ፡ዠምሮ፡ትውልድ፡ዅሉ፦ብፅዕት፡ይሉኛል፤ 49፤ብርቱ፡የኾነ፡ርሱ፡በእኔ፡ታላቅ፡ሥራ፡አድርጓልና፤ስሙም፡ቅዱስ፡ነው። 50፤ምሕረቱም፡ለሚፈሩት፡እስከ፡ትውልድና፡ትውልድ፡ይኖራል። 51፤በክንዱ፡ኀይል፡አድርጓል፤ትዕቢተኛዎችን፡በልባቸው፡ዐሳብ፡በትኗል፤ 52፤ገዢዎችን፡ከዙፋናቸው፡አዋርዷል፤ትሑታንንም፡ከፍ፡አድርጓል፤ 53፤የተራቡትን፡በበጎ፡ነገር፡አጥግቧል፤ባለጠጋዎችንም፡ባዷቸውን፡ሰዷቸዋል። 54-55፤ለአባቶቻችን፡እንደ፡ተናገረ፥ለአብርሃምና፡ለዘሩ፡ለዘለዓለም፡ምሕረቱ፡ትዝ፡እያለው፡እስራኤልን፡ብላቴናውን፡ረድቷል።

56፤ማርያምም፡ሦስት፡ወር፡የሚያኽል፡በርሷ፡ዘንድ፡ተቀመጠች፡ወደ፡ቤቷም፡ተመለሰች። 57፤የኤልሳቤጥም፡የመውለጃዋ፡ጊዜ፡ደረሰ፥ወንድ፡ልጅም፡ወለደች። 58፤ጎረቤቶቿም፡ዘመዶቿም፡ጌታ፡ምሕረቱን፡እንዳገነነላት፡ሰምተው፡ከርሷ፡ጋራ፡ደስ፡አላቸው። 59፤በስምንተኛውም፡ቀን፡ሕፃኑን፡ሊገርዙት፡መጡ፥በአባቱም፡ስም፡ዘካርያስ፡ሊሉት፡ወደዱ። 60፤እናቱ፡ግን፡መልሳ፦አይኾንም፥ዮሐንስ፡ይባል፡እንጂ፡አለች። 61፤እነርሱም፦ከወገንሽ፡ማንም፡በዚህ፡ስም፡የተጠራ፡የለም፡አሏት። 62፤አባቱንም፡ማን፡ሊባል፡እንዲወድ፡ጠቀሱት። 63፤ብራናም፡ለምኖ፦ስሙ፡ዮሐንስ፡ነው፡ብሎ፡ጻፈ።ዅሉም፡አደነቁ። 64፤ያን፡ጊዜም፡አፉ፡ተከፈተ፥ምላሱም፡ተፈታ፥እግዚአብሔርንም፡እየባረከ፡ተናገረ። 65፤ለጎረቤቶቻቸውም፡ዅሉ፡ፍርሀት፡ኾነ፤ይህም፡ዅሉ፡ነገር፡በይሁዳ፡በተራራማው፡አገር፡ዅሉ፡ተወራ፤ 66፤የሰሙትም፡ዅሉ፦እንኪያ፡ይህ፡ሕፃን፡ምን፡ይኾን፧እያሉ፡በልባቸው፡አኖሩት፤የጌታ፡እጅ፡ከርሱ፡ ጋራ፡ነበረችና። 67፤አባቱ፡ዘካርያስም፡መንፈስ፡ቅዱስ፡ሞላበትና፡ትንቢት፡ተናገረ፡እንዲህም፡አለ።

68፤የእስራኤል፡ጌታ፡አምላክ፡ይባረክ፥ጐብኝቶ፡ለሕዝቡ፡ቤዛ፡አድርጓልና፤ 69-70፤ከጥንት፡ዠምሮ፡በነበሩት፡በቅዱሳን፡ነቢያት፡አፍ፡እንደ፡ተናገረ፥በብላቴናው፡በዳዊት፡ቤት፡የመዳን፡ቀንድን፡አስነሥቶልናል፤ 71፤ማዳኑም፡ከወደረኛዎቻችንና፡ከሚጠሉን፡ዅሉ፡እጅ፡ነው፤ 72-73፤እንደዚህ፡ለአባቶቻችን፡ምሕረት፡አደረገ፤ለአባታችን፡ለአብርሃምም፡የማለውን፡መሐላውን፡ቅዱሱን፡ኪዳን፡ዐሰበ፤ 74-75፤በርሱም፡ከጠላቶቻችን፡እጅ፡ድነን፡በዘመናችን፡ዅሉ፡ያለፍርሀት፡በቅድስናና፡በጽድቅ፡በፊቱ፡እንድናገለግለው፡ሰጠን። 76፤ደግሞም፡አንተ፡ሕፃን፡ሆይ፥የልዑል፡ነቢይ፡ትባላለኽ፥መንገዱን፡ልትጠርግ፡በጌታ፡ፊት፡ትኼዳለኽና፤ 77፤እንደዚህም፡የኀጢአታቸው፡ስርየት፡የኾነውን፡የመዳን፡ዕውቀት፡ለሕዝቡ፡ትሰጣለኽ፤ 78፤ይህም፡ከላይ፡የመጣ፡ብርሃን፡በጐበኘበት፡በአምላካችን፡ምሕረትና፡ርኅራኄ፡ምክንያት፡ነው፤79፤ብርሃኑም፡በጨለማና፡በሞት፡ጥላ፡ተቀምጠው፡ላሉት፡ያበራል፡እግሮቻችንንም፡በሰላም፡መንገድ ያቀናል።

80፤ሕፃኑም፡አደገ፡በመንፈስም፡ጠነከረ፥ለእስራኤልም፡እስከታየበት፡ቀን፡ድረስ፡በምድረ፡በዳ፡ኖረ።

ምዕራፍ ፪

1፤በዚያም፡ወራት፡ዓለሙ፡ዅሉ፡እንዲጻፍ፡ከAአውግስጦስ፡ቄሳር፡ትእዛዝ፡ወጣች። 2፤ቄሬኔዎስ፡በሶርያ፡አገር፡ገዢ፡በነበረ፡ጊዜ፡ይህ፡የመዠመሪያ፡ጽሕፈት፡ኾነ። 3፤ዅሉም፡እያንዳንዱ፡ይጻፍ፡ዘንድ፡ወደ፡ከተማው፡ኼደ። 4-5፤ዮሴፍም፡ደግሞ፡ከዳዊት፡ቤትና፡ወገን፡ስለ፡ነበረ፡ከገሊላ፡ከናዝሬት፡ከተማ፡ተነሥቶ፡ቤተ ልሔም፡ ወደምትባል፡ወደዳዊት፡ከተማ፡ወደ፡ይሁዳ፥ፀንሳ፡ከነበረች፡ከዕጮኛው፡ከማርያም፡ጋራ፡ይጻፍ፡ዘንድ፡ወጣ። 6፤በዚያም፡ሳሉ፡የመውለጃዋ፡ወራት፡ደረሰ፥ 7፤የበኵር፡ልጇንም፡ወለደች፥በመጠቅለያም፡ጠቀለለችው፤በእንግዳዎችም፡ማደሪያ፡ስፍራ፡ስላልነበራቸው፡ በግርግም፡አስተኛችው።

ክርስቶስ በበረት ተኝቶ

8፤በዚያም፡ምድር፡መንጋቸውን፡በሌሊት፡ሲጠብቁ፡በሜዳ፡ያደሩ፡እረኛዎች፡ነበሩ። 9፤እንሆም፥የጌታ፡መልአክ፡ወደ፡እነርሱ፡ቀረበ፡የጌታ፡ክብርም፡በዙሪያቸው፡አበራ፥ታላቅ፡ፍርሀትም፡ ፈሩ። 10፤መልአኩም፡እንዲህ፡አላቸው፦እንሆ፥ለሕዝቡ፡ዅሉ፡የሚኾን፡ታላቅ፡ደስታ፡የምሥራች፡ እነግራችዃለኹና፡አትፍሩ፤ 11፤ዛሬ፡በዳዊት፡ከተማ፡መድኀኒት፡ርሱም፡ክርስቶስ፡ጌታ፡የኾነ፡ተወልዶላችዃልና። 12፤ይህም፡ምልክት፡ይኾንላችዃል፤ሕፃን፡ተጠቅሎ፟፡በግርግምም፡ተኝቶ፡ታገኛላችኹ። 13፤ድንገትም፡ብዙ፡የሰማይ፡ሰራዊት፡ከመልአኩ፡ጋራ፡ነበሩ።እግዚአብሔርንም፡እያመሰገኑ። 14፤ክብር፡ለእግዚአብሔር፡በአርያም፡ይኹን፡ሰላምም፡በምድር፡ለሰውም፡በጎ፡ፈቃድ፡አሉ። 15፤መላእክትም፡ከነርሱ፡ተለይተው፡ወደ፡ሰማይ፡በወጡ፡ጊዜ፥እረኛዎቹ፡ርስ፡በርሳቸው።እንግዲህ፡እስከ፡ ቤተ፡ልሔም፡ድረስ፡እንኺድ፡እግዚአብሔርም፡የገለጠልንን፡ይህን፡የኾነውን፡ነገር፡እንይ፡ተባባሉ። 16፤ፈጥነውም፡መጡ፡ማርያምንና፡ዮሴፍን፡ሕፃኑንም፡በግርግም፡ተኝቶ፡አገኙ። 17፤አይተውም፡ስለዚህ፡ሕፃን፡የተነገረላቸውን፡ነገር፡ገለጡ። 18፤የሰሙትን፡ዅሉ፡እረኛዎቹ፡በነገሯቸው፡ነገር፡አደነቁ፤ 19፤ማርያም፡ግን፡ይህን፡ነገር፡ዅሉ፡በልቧ፡እያሰበች፡ትጠብቀው፡ነበር። 20፤እረኛዎችም፡እንደ፡ተባለላቸው፡ስለ፡ሰሙትና፡ስላዩት፡ዅሉ፡እግዚአብሔርን፡እያመሰገኑና፡እያከበሩ፡ ተመለሱ። 21፤ሊገርዙት፡ስምንት፡ቀን፡በሞላ፡ጊዜ፥በማሕፀን፡ሳይረገዝ፡በመልአኩ፡እንደ፡ተባለ፥ስሙ፡ኢየሱስ፡ ተብሎ፡ተጠራ። 22-24፤እንደ፡ሙሴም፡ሕግ፡የመንጻታቸው፡ወራት፡በተፈጸመ፡ጊዜ፥በጌታ፡ሕግ፦የእናቱን፡ማሕፀን፡ የሚከፍት፡ወንድ፡ዅሉ፡ለጌታ፡የተቀደሰ፡ይባላል፡ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ፡በጌታ፡ፊት፡ሊያቆሙት፥በጌታም፡ ሕግ።ኹለት፡ዋሊያ፡ወይም፡ኹለት፡የርግብ፡ጫጩቶች፡እንደ፡ተባለ፥መሥዋዕት፡ሊያቀርቡ፡ወደ፡ ኢየሩሳሌም፡ወሰዱት። 25፤እንሆም፥በኢየሩሳሌም፡ስምዖን፡የሚባል፡ሰው፡ነበረ፥ይህም፡ሰው፡የእስራኤልን፡መጽናናት፡ይጠባበቅ፡ ነበር፤ጻድቅና፡ትጉህም፡ነበረ፥መንፈስ፡ቅዱስም፡በርሱ፡ላይ፡ነበረ።

ቅዱስ ስምዖን እየሱስን ታቅፎ ከፃድቋ ሀና ጋር ስለ ክርስቶስ ሲተነብዩ

26፤በጌታም፡የተቀባውን፡ሳያይ፡ሞትን፡እንዳያይ፡በመንፈስ ቅዱስ፡ተረድቶ፡ነበር። 27፤በመንፈስም፡ወደ፡መቅደስ፡ወጣ፤ወላጆቹም፡እንደ፡ሕጉ፡ልማድ፡ያደርጉለት፡ዘንድ፡ሕፃኑን፡ኢየሱስን፡ በአስገቡት፡ጊዜ፥ 28፤ርሱ፡ደግሞ፡ተቀብሎ፡ዐቀፈው፡እግዚአብሔርንም፡እየባረከ፡እንዲህ፡አለ።

29፤ጌታ፡ሆይ፥አኹን፡እንደ፡ቃልኽ፡ባሪያኽን፡በሰላም፡ታሰናብተዋለኽ፤ 30-31፤ዐይኖቼ፡በሰዎች፡ዅሉ፡ፊት፡ያዘጋጀኸውን፡ማዳንኽን፡አይተዋልና፤ 32፤ይህም፡ለአሕዛብ፡ዅሉን፡የሚገልጥ፡ብርሃን፡ለሕዝብኽም፡ለእስራኤል፡ክብር፡ነው።

33፤ዮሴፍና፡እናቱም፡ስለ፡ርሱ፡በተባለው፡ነገር፡ይደነቁ፡ነበር። 34-35፤ስምዖንም፡ባረካቸው፡እናቱን፡ማርያምንም፦እንሆ፥የብዙዎች፡ልብ፡ዐሳብ፡ይገለጥ፡ዘንድ፥ይህ፡ በእስራኤል፡ላሉት፡ለብዙዎቹ፡ለመውደቃቸውና፡ለመነሣታቸው፡ለሚቃወሙትም፡ምልክት፡ተሾሟል፥ባንቺም፡ ደግሞ፡በነፍስሽ፡ሰይፍ፡ያልፋል፡አላት። 36፤ከአሴር፡ወገንም፡የምትኾን፡የፋኑኤል፡ልጅ፡ሐና፡የምትባል፡አንዲት፡ነቢዪት፡ነበረች፤ርሷም፡ከድንግልናዋ፡ዠምራ፡ከባሏ፡ጋራ፡ሰባት፡ዓመት፡ኖረች፤ 37፤ርሷም፡ሰማንያ፡አራት፡ዓመት፡ያኽል፡መበለት፡ኾና፡በጣም፡አርጅታ፡ነበር፤በጾምና፡በጸሎትም፡ ሌሊትና፡ቀን፡እያገለገለች፡ከመቅደስ፡አትለይም፡ነበር። 38፤በዚያችም፡ሰዓት፡ቀርባ፡እግዚአብሔርን፡አመሰገነች፤የኢየሩሳሌምንም፡ቤዛ፡ለሚጠባበቁ፡ዅሉ፡ስለ፡ርሱ፡ ትናገር፡ነበር። 39፤ዅሉንም፡እንደ፡ጌታ፡ሕግ፡ከፈጸሙ፡በዃላ፥ወደ፡ገሊላ፡ወደ፡ከተማቸው፡ወደ፡ናዝሬት፡ተመለሱ። 40፤ሕፃኑም፡አደገ፥ጥበብም፡ሞልቶበት፡በመንፈስ፡ጠነከረ፤የእግዚአብሔርም፡ጸጋ፡በርሱ፡ላይ፡ነበረ። 41፤ወላጆቹም፡በያመቱ፡በፋሲካ፡በዓል፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ይወጡ፡ነበር። 42፤የዐሥራ፡ኹለት፡ዓመት፡ልጅ፡በኾነ፡ጊዜ፥እንደ፡በዓሉ፡ሥርዐት፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ወጡ፤ 43፤ቀኖቹንም፡ከፈጸሙ፡በዃላ፥ሲመለሱ፡ብላቴናው፡ኢየሱስ፡በኢየሩሳሌም፡ቀርቶ፡ነበር፥ዮሴፍም፡እናቱም፡ አላወቁም፡ነበር። 44፤ከመንገደኛዎች፡ጋራ፡የነበረ፡ስለ፡መሰላቸው፡ያንድ፡ቀን፡መንገድ፡ኼዱ፥ከዘመዶቻቸውም፡ ከሚያውቋቸውም፡ዘንድ፡ፈለጉት፤ 45፤ባጡትም፡ጊዜ፡እየፈለጉት፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ተመለሱ። 46፤ከሦስት፡ቀንም፡በዃላ፡በመምህራን፡መካከል፡ተቀምጦ፡ሲሰማቸውም፡ሲጠይቃቸውም፡በመቅደስ፡ አገኙት፤ 47፤የሰሙትም፡ዅሉ፡በማስተዋሉና፡በመልሱ፡ተገረሙ። 48፤ባዩትም፡ጊዜ፡ተገረሙ፥እናቱም፦ልጄ፡ሆይ፥ለምን፡እንዲህ፡አደረግኽብን፧እንሆ፥አባ ትኽና፡እኔ፡ እየተጨነቅን፡ስንፈልግኽ፡ነበርን፡አለችው። 49፤ርሱም፦ስለ፡ምን፡ፈለጋችኹኝ፧በአባቴ፡ቤት፡እኾን፡ዘንድ፡እንዲገባኝ፡አላወቃችኹምን፧አላቸው። 50፤እነርሱም፡የተናገራቸውን፡ነገር፡አላስተዋሉም። 51፤ከነርሱም፡ጋራ፡ወርዶ፡ወደ፡ናዝሬት፡መጣ፥ይታዘዝላቸውም፡ነበር።እናቱም፡ይህን፡ነገር፡ዅሉ፡በልቧ፡ ትጠብቀው፡ነበር። 52፤ኢየሱስም፡ደግሞ፡በጥበብና፡በቁመት፡በሞገስም፡በእግዚአብሔርና፡በሰው፡ፊት፡ያድግ፡ነበር።

ምዕራፍ ፫

1፤ጢባርዮስ፡ቄሳርም፡በነገሠ፡በዐሥራ፡ዐምስተኛዪቱ፡ዓመት፥ጰንጤናዊው፡ጲላጦስም፡በይሁዳ፡ ሲገዛ፥ሄሮድስም፡በገሊላ፡የአራተኛው፡ክፍል፡ገዢ፥ወንድሙ፡ፊልጶስም፡በኢጡርያስ፡በጥራኮኒዶስም፡አገር፡ የአራተኛው፡ክፍል፡ገዢ፥ሊሳኒዮስም፡በሳቢላኒስ፡የአራተኛው፡ክፍል፡ገዢ፡ኾነው፡ሳሉ፥ 2፤ሐናና፡ቀያፋም፡ሊቃነ፡ካህናት፡ሳሉ፥የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደዘካርያስ፡ልጅ፡ወደ፡ዮሐንስ፡በምድረ፡በዳ፡መጣ። 3-6፤በነቢዩ፡በኢሳይያስ፡ቃል፡መጽሐፍ፦የጌታን፡መንገድ፡አዘጋጁ፡ጥርጊያውንም፡አቅኑ፡እያለ፡በምድረ፡ በዳ፡የሚጮኽ፡ሰው፡ድምፅ፤ዐዘቅቱ፡ዅሉ፡ይሙላ፡ተራራውና፡ኰረብታውም፡ዅሉ፡ዝቅ፡ ይበል፥ጠማማውም፡የቀና፡መንገድ፡ይኹን፥ሻካራውም፡መንገድ፡ትክክል፡ይኹን፤ሥጋም፡የለበሰ፡ዅሉ፡ የእግዚአብሔርን፡ማዳን፡ይይ፡ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ፡ለኀጢአት፡ስርየት፡የንስሓን፡ጥምቀት፡እየሰበከ፡ በዮርዳኖስ፡ዙሪያ፡ወዳለችው፡አገር፡ዅሉ፡መጣ። 7፤ስለዚህ፥ከርሱ፡ሊጠመቁ፡ለወጡት፡ሕዝብ፡እንዲህ፡ይላቸው፡ነበር፦እናንተ፡የእፍኝት፡ ልጆች፥ከሚመጣው፡ቍጣ፡እንድትሸሹ፡ማን፡አመለከታችኹ፧ 8፤እንግዲህ፡ለንስሓ፡የሚገ፟ባ፟፡ፍሬ፡አድርጉ፤በልባችኹም፦አብርሃም፡አባት፡አለን፡ማለትን፡ አትዠምሩ፤ከነዚህ፡ድንጋዮች፡ለአብርሃም፡ልጆች፡ሊያስነሣለት፡እግዚአብሔር፡እንዲችል፡እላችዃለኹና። 9፤አኹንስ፡ምሣር፡ደግሞ፡በዛፎች፡ሥር፡ተቀምጧል፤እንግዲህ፡መልካም፡ፍሬ፡የማያደርግ፡ዛፍ፡ዅሉ፡ ይቈረጣል፡ወደ፡እሳትም፡ይጣላል። 10፤ሕዝቡም፦እንግዲህ፡ምን፡እናድርግ፧ብለው፡ይጠይቁት፡ነበር። 11፤መልሶም፦ኹለት፡ልብስ፡ያለው፡ለሌለው፡ያካፍል፥ምግብም፡ያለው፡እንዲሁ፡ያድርግ፡ይል፡ነበር። 12፤ቀራጮችም፡ደግሞ፡ሊጠመቁ፡መጥተው፦መምህር፡ሆይ፥ምን፡እናድርግ፧አሉት። 13፤ከታዘዘላችኹ፡አብልጣችኹ፡አትውሰዱ፡አላቸው። 14፤ጭፍራዎችም፡ደግሞ፦እኛ፡ደግሞ፡ምን፡እናድርግ፧ብለው፡ይጠይቁት፡ነበር።ርሱም፦በማንም፡ግፍ፡ አትሥሩ፡ማንንም፡በሐሰት፡አትክሰሱ፥ደመ፡ወዛችኹም፡ይብቃችኹ፡አላቸው። 15፤ሕዝቡም፡ሲጠብቁ፡ሳሉ፡ዅሉም፡በልባቸው፡ስለ፡ዮሐንስ፦ይህ፡ክርስቶስ፡ይኾንን፧ብለው፡ሲያስቡ፡ ነበር፥ 16፤ዮሐንስ፡መልሶ፦እኔስ፡በውሃ፡አጠምቃችዃለኹ፤ነገር፡ግን፥የጫማውን፡ጠፍር፡መፍታት፡ከማይገ፟ባ፟ኝ፡ ከእኔ፡የሚበረታ፡ይመጣል፤ርሱ፡በመንፈስ፡ቅዱስና፡በእሳት፡ያጠምቃችዃል፤ 17፤መንሹም፡በእጁ፡ነው፥ዐውድማውንም፡ፈጽሞ፡ያጠራል፥ስንዴውንም፡በጐተራው፡ይከታል፥ገለባውን፡ ግን፡በማይጠፋ፡እሳት፡ያቃጥለዋል፡አላቸው። 18፤ስለዚህ፥ሕዝቡን፡በብዙ፡ሌላ፡ምክር፡እየመከራቸው፡ወንጌልን፡ይሰብክላቸው፡ነበር፤ 19፤የአራተኛው፡ክፍል፡ገዢ፡ሄሮድስ፡ግን፥ስለ፡ሄሮድያዳ፡ስለ፡ወንድሙ፡ስለ፡ፊልጶስ፡ሚስትና፡ሄሮድስ፡ ስላደረገው፡ሌላ፡ክፋት፡ዅሉ፡ዮሐንስ፡ስለ፡ገሠጸው፥ 20፤ይህን፡ደግሞ፡ከዅሉ፡በላይ፡ጨምሮ፡ዮሐንስን፡በወህኒ፡አገባው። 21፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡ከተጠመቁ፡በዃላ፡ኢየሱስ፡ደግሞ፡ተጠመቀ።ሲጸልይም፡ሰማይ፡ተከፈተ፥ 22፤መንፈስ፡ቅዱስም፡በአካል፡መልክ፡እንደ፡ርግብ፡በርሱ፡ላይ፡ወረደ፤የምወድኽ፡ልጄ፡አንተ፡ ነኽ፥ባንተ፡ደስ፡ይለኛል፡የሚል፡ድምፅም፡ከሰማይ፡መጣ። 23፤ኢየሱስም፡ሊያስተምር፡ሲዠምር፡ዕድሜው፡ሠላሳ፡ዓመት፡ያኽል፡ኾኖት፡ነበር፤እንደመሰላቸው፡ የዮሴፍ፡ልጅ፡ኾኖ፥የኤሊ፡ልጅ፥ 24፤የማቲ፡ልጅ፥የሌዊ፡ልጅ፥የሚልኪ፡ልጅ፥ 25፤የዮና፡ልጅ፥የዮሴፍ፡ልጅ፥የማታትዩ፡ልጅ፥የዓሞጽ፡ልጅ፥የናሖም፡ልጅ፥የኤሲሊም፡ልጅ፡ 26፤የናጌ፡ልጅ፥የማአት፡ልጅ፥የማታትዩ፡ልጅ፡የሴሜይ፡ልጅ፥የዮሴፍ፡ልጅ፥ 27፤የዮዳ፡ልጅ፥የዮናን፡ልጅ፥የሬስ፡ልጅ፥የዘሩባቤል፡ልጅ፥የሰላትያል፡ልጅ፥የኔሪ፡ልጅ፥ 28፤የሚልኪ፡ልጅ፥የሐዲ፡ልጅ፥የዮሳስ፡ልጅ፥የቆሳም፡ልጅ፥የኤልሞዳም፡ልጅ፥የኤር፡ልጅ፥ 29፤የዮሴዕ፡ልጅ፥የኤልዓዘር፡ልጅ፡የዮራም፡ልጅ፥የማጣት፡ልጅ፥የሌዊ፡ልጅ፥ 30፤የስምዖን፡ልጅ፥የይሁዳ፡ልጅ፥የዮሴፍ፡ልጅ፥ 31፤የዮናን፡ልጅ፥የኤልያቄም፡ልጅ፥የሜልያ፡ልጅ፥የማይናን፡ልጅ፥የማጣት፡ልጅ፥የናታን፡ልጅ፡ 32፤የዳዊት፡ልጅ፥የእሴይ፡ልጅ፥የኢዮቤድ፡ልጅ፥የቦዔዝ፡ልጅ፥የሰልሞን፡ልጅ፥ 33፤የነአሶን፡ልጅ፥የዐሚናዳብ፡ልጅ፥የአራም፡ልጅ፥የአሮኒ፡ልጅ፥የኤስሮም፡ልጅ፥ 34፤የፋሬስ፡ልጅ፥የይሁዳ፡ልጅ፥የያዕቆብ፡ልጅ፥የይሥሐቅ፡ልጅ፥የአብርሃም፡ልጅ፥የታራ፡ልጅ፥ 35፤የናኮር፡ልጅ፥የሴሮህ፡ልጅ፥የራጋው፡ልጅ፥የፋሌቅ፡ልጅ፥የአቤር፡ልጅ፥የሳላ፡ልጅ፥ 36፤የቃይንም፡ልጅ፥የአርፋክስድ280፡ልጅ፥የሴም፡ልጅ፥የኖኅ፡ልጅ፥የላሜህ፡ልጅ፥ 37፤የማቱሳላ፡ልጅ፥የሔኖክ፡ልጅ፥የያሬድ፡ልጅ፥ 38፤የመላልኤል፡ልጅ፥የቃይናን፡ልጅ፥የሄኖስ፡ልጅ፥የሴት፡ልጅ፥የአዳም፡ልጅ፥የእግዚአብሔር፡ልጅ።

ምዕራፍ ፬

1፤ኢየሱስም፡መንፈስ፡ቅዱስ፡መልቶበት፡ከዮርዳኖስ፡ተመለሰ፥በመንፈስም፡ወደ፡ምድረ፡በዳ፡ተመርቶ፥ 2፤አርባ፡ቀን፡ከዲያብሎስ፡ተፈተነ።በነዚያም፡ቀኖች፡ምንም፡አልበላም፥ከተጨረሱም፡በዃላ፡ተራበ። 3፤ዲያብሎስም፦የእግዚአብሔር፡ልጅ፡ከኾንኽ፥ይህን፡ድንጋይ፦እንጀራ፡ኹን፡ብለኽ፡እዘዝ፡አለው። 4፤ኢየሱስም፦ሰው፡በእግዚአብሔር፡ቃል፡ዅሉ፡እንጂ፡በእንጀራ፡ብቻ፡አይኖርም፡ተብሎ፡ተጽፏል፡ብሎ፡ መለሰለት። 5፤ዲያብሎስም፡ረዥም፡ወደ፡ኾነ፡ተራራ፡አውጥቶ፡የዓለምን፡መንግሥታት፡ዅሉ፡በቅጽበት፡አሳየው። 6፤ዲያብሎስም፦ይህ፡ሥልጣን፡ዅሉ፡ክብራቸውም፡ለእኔ፡ተሰጥቷል፡ለምወደ፟ውም፡ለማንም፡እሰጠዋለኹና፡ ለአንተ፡እሰጥኻለኹ፤ 7፤ስለዚህ፥አንተ፡በእኔ፡ፊት፡ብትሰግድ፥ዅሉ፡ለአንተ፡ይኾናል፡አለው። 8፤ኢየሱስም፡መልሶ፦ለጌታ፡ለአምላክኽ፡ስገድ፡ርሱንም፡ብቻ፡አምልክ፡ተብሎ፡ተጽፏል፡አለው። 9-11፤ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ደግሞ፡ወሰደው፤በመቅደስም፡ጫፍ፡ላይ፡አቁሞ፦ይጠብቁኽ፡ዘንድ፡መላእክቱን፡ ስለ፡አንተ፡ያዝ፟ልኻል፥እግርኽንም፡በድንጋይ፡ከቶ፡እንዳትሰናከል፡በእጃቸው፡ያነሡኻል፡ተብሎ፡ ተጽፏልና፥የእግዚአብሔር፡ልጅስ፡ከኾንኽ፥ከዚህ፡ወደ፡ታች፡ራስኽን፡ወርውር፡አለው። 12፤ኢየሱስም፡መልሶ፦ጌታን፡አምላክኽን፡አትፈታተነው፡ተብሏል፡አለው። 13፤ዲያብሎስም፡ፈተናውን፡ዅሉ፡ከጨረሰ፡በዃላ፡እስከ፡ጊዜው፡ከርሱ፡ተለየ። 14፤ኢየሱስም፡በመንፈስ፡ኀይል፡ወደ፡ገሊላ፡ተመለሰ፤ስለ፡ርሱም፡በዙሪያው፡ባለችው፡አገር፡ዅሉ፡ዝና፡ ወጣ። 15፤ርሱም፡በምኵራባቸው፡ያስተምር፥ዅሉም፡ያመሰግኑት፡ነበር። 16፤ወዳደገበትም፡ወደ፡ናዝሬት፡መጣ፤እንደ፡ልማዱም፡በሰንበት፡ቀን፡ወደ፡ምኵራብ፡ገባ፥ሊያነብም፡ ተነሣ። 17-19፤የነቢዩንም፡የኢሳይያስን፡መጽሐፍ፡ሰጡት፥መጽሐፉንም፡በተረተረ፡ጊዜ፦የጌታ፡መንፈስ፡በእኔ፡ላይ፡ ነው፥ለድኻዎች፡ወንጌልን፡እሰብክ፡ዘንድ፡ቀብቶኛልና፤ለታሰሩትም፡መፈታትን፡ለዕውሮችም፡ማየትን፡ እሰብክ፡ዘንድ፥የተጠቁትንም፡ነጻ፡አወጣ፡ዘንድ፡የተወደደችውንም፡የጌታን፡ዓመት፡እሰብክ፡ዘንድ፡ልኮኛል፡ ተብሎ፡የተጻፈበትን፡ስፍራ፡አገኘ። 20፤መጽሐፉንም፡ጠቅሎ፟፡ለአገልጋዩ፡ሰጠውና፡ተቀመጠ፤በምኵራብም፡የነበሩት፡ዅሉ፡ትኵር፡ብለው፡ ይመለከቱት፡ነበር። 21፤ርሱም፦ዛሬ፡ይህ፡መጽሐፍ፡በዦሯችኹ፡ተፈጸመ፡ይላቸው፡ዠመር። 22፤ዅሉም፡ይመሰክሩለት፡ነበር፡ከአፉም፡ከሚወጣው፡ከጸጋው፡ቃል፡የተነሣ፡እየተደነቁ፦ይህ፡የዮሴፍ፡ ልጅ፡አይደለምን፧ይሉ፡ነበር። 23፤ርሱም፦ያለጥርጥር፡ይህን፡ምሳሌ፦ባለመድኀኒት፡ሆይ፥ራስኽን፡ፈውስ፤በቅፍርናሖም፡እንዳደረግኸው፡ የሰማነውን፡ዅሉ፡በዚህ፡በገዛ፡አገርኽ፡ደግሞ፡አድርግ፡ትሉኛላችኹ፡አላቸው። 24፤እንዲህም፡አለ፦እውነት፡እላችዃለኹ፥ነቢይ፡በገዛ፡አገሩ፡ከቶ፡አይወደድም። 25፤ነገር፡ግን፥እውነት፡እላችዃለኹ፥በኤልያስ፡ዘመን፡ሦስት፡ዓመት፡ከስድስት፡ወር፡ሰማይ፡ተዘግቶ፡ሳለ፡ በምድር፡ዅሉ፡ብርቱ፡ራብ፡በነበረ፡ጊዜ፥በእስራኤል፡ብዙ፡መበለቶች፡ነበሩ፤ 26፤ኤልያስም፡በሲዶና፡አገር፡ወዳለች፡ወደ፡ሰራጵታ፣ወደ፡አንዲት፡መበለት፡እንጂ፥ከነርሱ፡ወደ፡አንዲቱ፡ አልተላከም። 27፤በነቢዩ፡በኤልሳዕ፡ዘመንም፡በእስራኤል፡ብዙ፡ለምጻሞች፡ነበሩ፥ከሶርያዊው፡ከንዕማን፡በቀር፡ከነርሱ፡ አንድ፡ስንኳ፡አልነጻም። 28፤በምኵራብም፡የነበሩ፡ዅሉ፡ይህን፡ሰምተው፡ቍጣ፡ሞላባቸው፥ተነሥተውም፡ከከተማ፡ወደ፡ውጭ፡ አወጡት፥ 29፤ይጥሉትም፡ዘንድ፡ከተማቸው፡ተሠርታባት፡ወደነበረች፡ወደተራራው፡አፋፍ፡ወሰዱት፤ 30፤ርሱ፡ግን፡በመካከላቸው፡ዐልፎ፡ኼደ። 31፤ወደገሊላ፡ከተማም፡ወደ፡ቅፍርናሖም፡ወረደ።በሰንበትም፡ያስተምራቸው፡ነበር፤ 32፤ቃሉ፡በሥልጣን፡ነበርና፥በትምህርቱ፡ተገረሙ። 33፤በምኵራብም፡የርኩስ፡ጋኔን፡መንፈስ፡ያደረበት፡ሰው፡ነበረ፥በታላቅ፡ድምፅም፡ጮኾ፦ 34፤ተው፥የናዝሬቱ፡ኢየሱስ፡ሆይ፥ከአንተ፡ጋራ፡ምን፡አለን፧ልታጠፋን፡መጣኽን፧ማን፡እንደ፡ኾንኽ፡ ዐውቄኻለኹ፥አንተ፡የእግዚአብሔር፡ቅዱሱ፡አለ። 35፤ኢየሱስም፦ዝም፡በል፡ከርሱም፡ውጣ፡ብሎ፡ገሠጸው።ጋኔኑም፡በመካከላቸው፡ጥሎት፡ሳይጐዳው፡ ከርሱ፡ወጣ። 36፤ዅሉንም፡መደነቅ፡ያዛቸው፥ርስ፡በርሳቸውም፦ይህ፡ቃል፡ምንድር፡ነው፧በሥልጣንና፡በኀይል፡ርኩሳን፡መናፍስትን፡ያዛ፟ልና፥ይወጡማል፡ብለው፡ተነጋገሩ። 37፤ዝናም፡በዙሪያው፡ባለች፡አገር፡ወደ፡ስፍራው፡ዅሉ፡ስለ፡ርሱ፡ወጣ። 38፤በምኵራብም፡ተነሥቶ፡ወደስምዖን፡ቤት፡ገባ።የስምዖንም፡ዐማት፡በብርቱ፡ንዳድ፡ታማ፡ነበር፡ስለ፡ ርሷም፡ለመኑት። 39፤በአጠገቧም፡ቆሞ፡ንዳዱን፡ገሠጸውና፡ለቀቃት፤ያን፡ጊዜውንም፡ተነሥታ፡አገለገለቻቸው። 40፤ፀሓይም፡በገባ፡ጊዜ፡በልዩ፡ልዩ፡ደዌ፡የተያዙ፡በሽተኛዎችን፡ዅሉ፡ወደ፡ርሱ፡አመጧቸው፤ርሱም፡ በያንዳንዳቸው፡ላይ፡እጁን፡ጭኖ፡ፈወሳቸው። 41፤አጋንንትም፡ደግሞ፦አንተ፡ክርስቶስ፡የእግዚአብሔር፡ልጅ፡ነኽ፡እያሉ፡እየጮኹም፡ከብዙዎች፡ይወጡ፡ ነበር፤ገሠጻቸውም፡ክርስቶስም፡እንደ፡ኾነ፡ዐውቀውት፡ነበርና፥እንዲናገሩ፡አልፈቀደላቸውም። 42፤በጸባም፡ጊዜ፡ወጥቶ፡ወደ፡ምድረ፡በዳ፡ኼደ፤ሕዝቡም፡ይፈልጉት፡ነበር፤ወደ፡ርሱም፡ መጡ፥ከነርሱም፡ተለይቶ፡እንዳይኼድ፡ሊከለክሉት፡ወደዱ። 43፤ርሱ፡ግን፦ስለዚህ፡ተልኬያለኹና፡ለሌላዎቹ፡ከተማዎች፡ደግሞ፡የእግዚአብሔርን፡መንግሥት፡ወንጌል፡ እሰብክ፡ዘንድ፡ይገ፟ባ፟ኛል፡አላቸው። 44፤በገሊላም፡ምኵራቦች፡ይሰብክ፡ነበር።

ምዕራፍ ፭

1፤ሕዝቡም፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡እየሰሙ፡ሲያስጠብቡት፡ሳሉ፥ርሱ፡ራሱ፡በጌንሳሬጥ፡ባሕር፡ዳር፡ቆሞ፡ ነበር፤ 2፤በባሕር፡ዳርም፡ቆመው፡የነበሩትን፡ኹለት፡ታንኳዎች፡አየ፤ዓሣ፡አጥማጆች፡ግን፡ከነርሱ፡ውስጥ፡ ወጥተው፡መረቦቻቸውን፡ያጥቡ፡ነበር። 3፤ከታንኳዎቹም፡የስምዖን፡ወደነበረች፡ወደ፡አንዲቱ፡ገብቶ፡ከምድር፡ጥቂት፡ፈቀቅ፡እንዲያደርጋት፡ለመነው፤በታንኳዪቱም፡ተቀምጦ፡ሕዝቡን፡ያስተምር፡ነበር። 4፤ነገሩንም፡ከጨረሰ፡በዃላ፥ስምዖንን፦ወደ፡ጥልቁ፡ፈቀቅ፡በል፡መረቦቻችኹንም፡ለማጥመድ፡ጣሉ፡ አለው። 5፤ስምዖንም፡መልሶ፦አቤቱ፥ሌሊቱን፡ዅሉ፡ዐድረን፡ስንደክም፡ምንም፡አልያዝንም፤ነገር፡ግን፥በቃልኽ፡ መረቦቹን፡እጥላለኹ፡አለው። 6፤ይህንም፡ባደረጉ፡ጊዜ፡እጅግ፡ብዙ፡ዓሣ፡ያዙ፤መረቦቻቸውም፡ተቀደዱ። 7፤በሌላ፡ታንኳም፡የነበሩትን፡ጓደኛዎቻቸውን፡መጥተው፡እንዲያግዟቸው፡ጠቀሱ፤መጥተውም፡ኹለቱ፡ ታንኳዎች፡እስኪሰጥሙ፡ድረስ፡ሞሏቸው። 8፤ስምዖን፡ጴጥሮስ፡ግን፡ባየ፡ጊዜ፡በኢየሱስ፡ጕልበት፡ላይ፡ወድቆ፦ጌታ፡ሆይ፥እኔ፡ኀጢአተኛ፡ነኝና፡ ከእኔ፡ተለይ፡አለው። 9፤ስላጠመዱት፡ዓሣ፡ርሱ፡ከርሱ፡ጋራም፡የነበሩ፡ዅሉ፡ተደንቀዋልና፥ 10፤እንዲሁም፡ደግሞ፡የስምዖን፡ባልንጀራዎች፡የነበሩ፡የዘብዴዎስ፡ልጆች፡ያዕቆብና፡ዮሐንስም፡ተደነቁ።ኢየሱስም፡ስምዖንን፦አትፍራ፤ከእንግዲህ፡ወዲህ፡ሰውን፡የምታጠምድ፡ትኾናለኽ፡አለው። 11፤ታንኳዎችንም፡ወደ፡ምድር፡አድርሰው፡ዅሉን፡ትተው፡ተከተሉት። 12፤ከከተማዎችም፡በአንዲቱ፡ሳለ፥እንሆ፥ለምጽ፡የሞላበት፡ሰው፡ነበረ፤ኢየሱስንም፡አይቶ፡በፊቱ፡ ወደቀና፦ጌታ፡ሆይ፥ብትወድስ፥ልታነጻኝ፡ትችላለኽ፡ብሎ፡ለመነው። 13፤እጁንም፡ዘርግቶ፡ዳሰሰውና፦እወዳለኹ፥ንጻ፡አለው፤ወዲያውም፡ለምጹ፡ለቀቀው። 14፤ርሱም፡ለማንም፡እንዳይናገር፡አዘዘው፥ነገር፡ግን፦ኼደኽ፡ራስኽን፡ለካህን፡አሳይ፥ለእነርሱም፡ምስክር፡እንዲኾን፡ስለ፡መንጻትኽ፡ሙሴ፡እንዳዘዘ፡መሥዋዕት፡አቅርብ፡አለው። 15፤ወሬው፡ግን፡አብዝቶ፡ወጣ፥ብዙ፡ሕዝብም፡ሊሰሙትና፡ከደዌያቸው፡ሊፈወሱ፡ይሰበሰቡ፡ነበር፤ 16፤ነገር፡ግን፥ርሱ፡ወደ፡ምድረ፡በዳ፡ፈቀቅ፡ብሎ፡ይጸልይ፡ነበር። 17፤አንድ፡ቀንም፡ያስተምር፡ነበር፤ከገሊላና፡ከይሁዳ፡መንደሮችም፡ዅሉ፡ከኢየሩሳሌምም፡መጥተው፡የነበሩ፡ፈሪሳውያንና፡የሕግ፡መምህራን፡ይቀመጡ፡ነበር፤ርሱም፡እንዲፈውስ፡የጌታ፡ኀይል፡ኾነለት። 18፤እንሆም፥አንድ፡ሽባ፡በዐልጋ፡ተሸክመው፡አመጡ፤አግብተውም፡በፊቱ፡ሊያኖሩት፡ይሹ፡ነበር። 19፤ስለ፡ሕዝቡም፡ብዛት፡እንዴት፡አድርገው፡እንዲያገቡት፡ሲያቅታቸው፥ወደ፡ሰገነቱ፡ወጡ፡የጣራውንም፡ ጡብ፡አሳልፈው፡በመካከል፡በኢየሱስ፡ፊት፡ከነዐልጋው፡አወረዱት። 20፤እምነታቸውንም፡አይቶ፦አንተ፡ሰው፥ኀጢአትኽ፡ተሰረየችልኽ፡አለው። 21፤ጻፊዎችና፡ፈሪሳውያንም፦ይህ፡የሚሳደብ፡ማን፡ነው፧ከአንዱ፡ከእግዚአብሔር፡በቀር፡ኀጢአት፡ ሊያስተሰርይ፡ማን፡ይችላል፧ብለው፡ያስቡ፡ዠመር። 22፤ኢየሱስም፡ዐሳባቸውን፡እያወቀ፡መልሶ፦በልባችኹ፡ምን፡ታስባላችኹ፧ 23፤ኀጢአትኽ፡ተሰረየችልኽ፡ከማለት፡ወይስ፦ተነሣና፡ኺድ፡ከማለት፡ማናቸው፡ይቀላል፧ 24፤ነገር፡ግን፥በምድር፡ላይ፡ኀጢአት፡ሊያስተሰርይ፡ለሰው፡ልጅ፡ሥልጣን፡እንዳለው፡እንድታውቁ፡ ብሎ፥ሽባውን፦አንተን፡እልኻለኹ፥ተነሣ፥ዐልጋኽን፡ተሸክመኽ፡ወደ፡ቤትኽ፡ኺድ፡አለው። 25፤በዚያን፡ጊዜም፡በፊታቸው፡ተነሣ፥ተኝቶበትም፡የነበረውን፡ተሸክሞ፡እግዚአብሔርን፡እያመሰገነ፡ወደ፡ ቤቱ፡ኼደ። 26፤ዅሉንም፡መገረም፡ያዛቸው፥እግዚአብሔርንም፡አመስግነው።ዛሬስ፡ድንቅ፡ነገር፡አየን፡እያሉ፡ፍርሀት፡ ሞላባቸው። 27፤ከዚህም፡በዃላ፡ወጥቶ፡ሌዊ፡የሚባል፡ቀራጭ፡በመቅረጫው፡ተቀምጦ፡ተመለከተና፦ተከተለኝ፡አለው። 28፤ዅሉንም፡ተወ፤ተነሥቶም፡ተከተለው። 29፤ሌዊም፡በቤቱ፡ታላቅ፡ግብዣ፡አደረገለት፤ከነርሱም፡ጋራ፡በማእዱ፡ተቀምጠው፡የነበሩ፡ከቀራጮችና፡ ከሌላዎች፡ሰዎች፡ብዙ፡ሕዝብ፡ነበሩ። 30፤ፈሪሳውያንና፡ጻፊዎቻቸውም፡በደቀ፡መዛሙርቱ፡ላይ፦ስለ፡ምን፡ከቀራጮችና፡ከኀጢአተኛዎች፡ጋራ፡ ትበላላችኹ፡ትጠጡማላችኹ፧ብለው፡አንጐራጐሩ። 31፤ኢየሱስም፡መልሶ፦ሕመምተኛዎች፡እንጂ፡ባለጤናዎች፡ባለመድኀኒት፡አያስፈልጋቸውም፤ 32፤ኀጢአተኛዎችን፡ወደ፡ንስሓ፡እንጂ፡ጻድቃንን፡ልጠራ፡አልመጣኹም፡አላቸው። 33፤እነርሱም፦የዮሐንስ፡ደቀ፡መዛሙርት፡ስለ፡ምን፡ብዙ፡ይጦማሉ፡ጸሎትስ፡ስለ፡ምን፡ ያደርጋሉ፥ደግሞም፡የፈሪሳውያን፡ደቀ፡መዛሙርት፡ስለ፡ምን፡እንደዚሁ፡ያደርጋሉ፤የአንተ፡ደቀ፡ መዛሙርት፡ግን፡ይበላሉ፡ይጠጣሉም፧አሉት። 34፤ኢየሱስም፦ሙሽራው፡ከነርሱ፡ጋራ፡ሳለ፡ሚዜዎችን፡ልታስጦሙ፡ትችላላችኹን፧ 35፤ነገር፡ግን፥ወራት፡ይመጣል፥ሙሽራውም፡ከነርሱ፡ሲወሰድ፡ያን፡ጊዜ፥በዚያ፡ወራት፡ይጦማሉ፡ አላቸው። 36፤ደግሞም፡ምሳሌ፡እንዲህ፡ሲል፡ነገራቸው፦የዐዲስ፡ልብስ፡ዕራፊ፡ባረጀ፡ልብስ፡ላይ፡የሚያኖር፡ የለም፤ቢደረግ፡ግን፡ዐዲሱን፡ይቀደዋል፡ደግሞም፡ዐዲስ፡ዕራፊ፡ለአሮጌው፡አይስማማውም። 37፤ባረጀ፡አቍማዳም፡ዐዲስ፡የወይን፡ጠጅ፡የሚያኖር፡የለም፤ቢደረግ፡ግን፡ዐዲሱ፡የወይን፡ጠጅ፡ አቍማዳውን፡ያፈነዳል፥ርሱም፡ይፈሳል፡አቍማዳውም፡ይጠፋል። 38፤ዐዲሱን፡የወይን፡ጠጅ፡ግን፡በዐዲስ፡አቍማዳ፡ማኖር፡ይገ፟ባ፟ል፥ኹለቱም፡ይጠባበቃሉ። 39፤አሮጌ፡የወይን፡ጠጅ፡ሲጠጣ፡ዐዲሱን፡የሚሻ፡ማንም፡የለም፤አሮጌው፡ይጣፍጣል፡ይላልና።

ምዕራፍ ፮

1፤በሰንበትም፡በዕርሻ፡መካከል፡ያልፍ፡ነበር፡ደቀ፡መዛሙርቱም፡እሸት፡ይቀጥፉ፡በእጃቸውም፡እያሹ፡ ይበሉ፡ነበር። 2፤ከፈሪሳውያን፡ግን፡አንዳንዶቹ፦በሰንበት፡ሊያደርግ፡ያልተፈቀደውን፡ስለ፡ምን፡ታደርጋላችኹ፧አሏቸው። 3-4፤ኢየሱስም፡ለእነርሱ፡መልሶ፦ዳዊት፡በተራበ፡ጊዜ፡ርሱ፡ዐብረውት፡ከነበሩ፡ጋራ፡ ያደረገውን፥ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡እንደ፡ገባ፡ከካህናት፡ብቻ፡በቀር፡መብላቱ፡ያልተፈቀደውን፡ የመሥዋዕትን፡እንጀራ፡ይዞ፡እንደ፡በላ፥ከርሱም፡ጋራ፡ለነበሩት፡ደግሞ፡እንደ፡ሰጣቸው፡ይህን፡ አላነበባችኹምን፧አለ። 5፤የሰው፡ልጅ፡የሰንበት፡ጌታ፡ነው፡አላቸውም። 6፤በሌላው፡ሰንበትም፡ወደ፡ምኵራብ፡ገብቶ፡አስተማረ፤በዚያም፡ቀኝ፡እጁ፡የሰለለች፡ሰው፡ነበረ፤ 7፤ጻፊዎችና፡ፈሪሳውያንም፡መክሰሻ፡ሊያገኙበት፡በሰንበት፡ይፈውስ፡እንደ፡ኾነ፡ይጠባበቁት፡ነበር። 8፤ርሱ፡ግን፡ዐሳባቸውን፡ዐውቆ፡እጁ፡የሰለለችውን፡ሰው፦ተነሣና፡በመካከል፡ቁም፡አለው፤ተነሥቶም፡ ቆመ። 9፤ኢየሱስም፦እጠይቃችዃለኹ፤በሰንበት፡በጎ፡ማድረግ፡ተፈቅዷልን፡ወይስ፡ክፉ፧ነፍስ፡ማዳንን፡ወይስ፡ መግደል፧አላቸው። 10፤ኹላቸውንም፡ዙሪያውን፡አየና፡ሰውዬውን፦እጅኽን፡ዘርጋ፡አለው።ርሱም፡እንዲህ፡አደረገ፥እጁም፡ እንደ፡ኹለተኛዪቱ፡ዳነች። 11፤እነርሱም፡ቍጣ፡ሞላባቸው፥በኢየሱስም፡ምን፡እንዲያደርጉበት፡ርስ፡በርሳቸው፡ተባባሉ። 12፤በነዚህም፡ወራት፡ይጸልይ፡ዘንድ፡ወደ፡ተራራ፡ወጣ፥ሌሊቱንም፡ዅሉ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ሲጸልይ፡ ዐደረ። 13፤በነጋም፡ጊዜ፡ደቀ፡መዛሙርቱን፡ጠራ፥ከነርሱም፡ዐሥራ፡ኹለት፡መረጠ፡ደግሞም፡ሐዋርያት፡ብሎ፡ ሰየማቸው፤ 14፤እነርሱም፥ጴጥሮስ፡ብሎ፡እንደ፡ገና፡የሰየመው፡ስምዖን፥ወንድሙም፡እንድርያስ፥ያዕቆብም፡ ዮሐንስም፥ፊልጶስም፡በርተሎሜዎስም፥ 15፤ማቴዎስም፡ቶማስም፥የእልፍዮስ፡ልጅ፡ያዕቆብም፡ቀናተኛ፡የሚባለው፡ስምዖንም፥ 16፤የያዕቆብ፡ይሁዳም፥አሳልፎ፡የሰጠውም፡የአስቆሮቱ፡ይሁዳ፡ናቸው። 17፤ከነርሱም፡ጋራ፡ወርዶ፡በተካከለ፡ስፍራ፡ቆመ፥ከደቀ፡መዛሙርቱም፡ወገን፡ብዙ፡ሕዝብ፡ ነበረ፥ደግሞም፡ሊሰሙትና፡ከደዌያቸው፡ሊፈወሱ፡ከይሁዳ፡ዅሉ፡ከኢየሩሳሌምም፡ከጢሮስና፡ከሲዶና፡ባሕር፡ ዳርም፡የመጡ፡ብዙ፡ሰዎች፡ነበሩ፤ 18፤ከርኩሳንም፡መናፍስት፡ይሠቃዩ፡የነበሩት፡ተፈወሱ፤ 19፤ከርሱም፡ኀይል፡ወጥቶ፡ዅሉን፡ይፈውስ፡ነበርና፥ሕዝቡ፡ዅሉ፡ሊዳስሱት፡ይሹ፡ነበር። 20፤ርሱም፡ወደ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡ዐይኑን፡አነሣ፡እንዲህም፡አላቸው፦እናንተ፡ድኻዎች፡ብፁዓን፡ ናችኹ፥የእግዚአብሔር፡መንግሥት፡የእናንተ፡ነውና። 21፤እናንተ፡አኹን፡የምትራቡ፡ብፁዓን፡ናችኹ፥ትጠግባላችኹና።እናንተ፡አኹን፡የምታለቅሱ፡ብፁዓን፡ናችኹ፥ትሥቃላችኹና። 22፤ሰዎች፡ስለሰው፡ልጅ፡ሲጠሏችኹ፡ሲለይዋችኹም፡ሲነቅፏችኹም፡ስማችኹንም፡እንደ፡ክፉ፡ ሲያወጡ፥ብፁዓን፡ናችኹ። 23፤እንሆ፥ዋጋችኹ፡በሰማይ፡ታላቅ፡ነውና፥በዚያን፡ቀን፡ደስ፡ይበላችኹ፡ዝለሉም፤አባቶቻቸው፡ነቢያትን፡ እንዲህ፡ያደርጉባቸው፡ነበርና። 24፤ነገር፡ግን፥እናንተ፡ባለጠጋዎች፡ወዮላችኹ፥መጽናናታችኹን፡ተቀብላችዃልና። 25፤እናንተ፡አኹን፡የጠገባችኹ፡ወዮላችኹ፥ትራባላችኹና።እናንተ፡አኹን፡የምትሥቁ፡ ወዮላችኹ፥ታዝናላችኹና፡ታለቅሱማላችኹ። 26፤ሰዎች፡ዅሉ፡መልካም፡ሲናገሩላችኹ፥ወዮላችኹ፤አባቶቻቸው፡ለሐሰተኛዎች፡ነቢያት፡እንዲሁ፡ ያደርጉላቸው፡ነበርና። 27፤ነገር፡ግን፥ለእናንተ፡ለምትሰሙ፡እላችዃለኹ፥ጠላቶቻችኹን፡ውደዱ፥ለሚጠሏችኹ፡መልካም፡ አድርጉ፥ 28፤የሚረግሟችኹንም፡መርቁ፥ስለሚበድሏችኹም፡ጸልዩ። 29፤ጕንጭኽን፡ለሚመታኽ፡ደግሞ፡ኹለተኛውን፡ስጠው፥መጐናጸፊያኽንም፡ለሚወስድ፡እጀ፡ጠባብኽን፡ ደግሞ፡አትከልክለው። 30፤ለሚለምንኽ፡ዅሉ፡ስጥ፥ገንዘብኽንም፡የሚወስድ፡እንዲመልስ፡አትጠይቀው። 31፤ሰዎችም፡ሊያደርጉላችኹ፡እንደምትወዱ፡እናንተ፡ደግሞ፡እንዲሁ፡አድርጉላቸው። 32፤የሚወዷ፟ችኹንማ፡ብትወዱ፥ምን፡ምስጋና፡አላችኹ፧ኀጢአተኛዎች፡ደግሞ፡የሚወዷ፟ቸውን፡ይወዳሉና። 33፤መልካምም፡ለሚያደርጉላችኹ፡መልካም፡ብታደርጉ፥ምን፡ምስጋና፡አላችኹ፧ኀጢአተኛዎች፡ደግሞ፡ያን፡ ያደርጋሉና። 34፤እንድትወስዱባቸው፡ተስፋ፡ለምታደርጓቸው፡ብታበድሩ፥ምን፡ምስጋና፡አላችኹ፧ኀጢአተኛዎች፡ደግሞ፡ በትክክል፡እንዲቀበሉ፡ለኀጢአተኛዎች፡ያበድራሉ። 35፤ነገር፡ግን፥ጠላቶቻችኹን፡ውደዱ፤መልካም፡አድርጉ፤ምንም፡ተስፋ፡ሳታደርጉም፡አበድሩ፥ዋጋችኹም፡ ታላቅ፡ይኾናል፥የልዑልም፡ልጆች፡ትኾናላችኹ፥ርሱ፡ለማያመሰግኑ፡ለክፉዎችም፡ቸር፡ነውና። 36፤አባታችኹ፡ርኅሩኅ፡እንደ፡ኾነ፡ርኅሩኆች፡ኹኑ። 37፤አትፍረዱ፡አይፈረድባችኹምም፤አትኰንኑ፡አትኰነኑምም።ይቅር፡በሉ፡ይቅርም፡ትባላላችኹ። 38፤ስጡ፡ይሰጣችኹማል፤በምትሰፍሩበት፡መስፈሪያ፡ተመልሶ፡ይሰፈርላችዃልና፥የተጨቈነና፡የተነቀነቀ፡ የተትረፈረፈም፡መልካም፡መስፈሪያ፡በዕቅፋችኹ፡ይሰጣችዃል። 39፤ምሳሌም፡አላቸው፦ዕውር፡ዕውርን፡ሊመራ፡ይችላልን፧ኹለቱ፡በጕድጓድ፡አይወድቁምን፧ 40፤ደቀ፡መዝሙር፡ከመምህሩ፡አይበልጥም፤ፈጽሞ፡የተማረ፡ዅሉ፡ግን፡እንደ፡መምህሩ፡ይኾናል። 41፤በወንድምኽም፡ዐይን፡ያለውን፡ጕድፍ፡ስለ፡ምን፡ታያለኽ፥በራስኽ፡ዐይን፡ግን፡ያለውን፡ምሰሶ፡ስለ፡ ምን፡አትመለከትም፧ 42፤በዐይንኽ፡ያለውን፡ምሰሶ፡ራስኽ፡ሳታይ፥እንዴት፡ወንድምኽን፦ወንድሜ፡ሆይ፥በዐይንኽ፡ያለውን፡ ጕድፍ፡ላውጣ፡ፍቀድልኝ፡ልትል፡ትችላለኽ፧አንተ፡ግብዝ፥አስቀድመኽ፡ከዐይንኽ፡ምሰሶውን፡አውጣ፡ ከዚያም፡በዃላ፡በወንድምኽ፡ዐይን፡ያለውን፡ጕድፍ፡ታወጣ፡ዘንድ፡አጥርተኽ፡ታያለኽ። 43፤ክፉ፡ፍሬ፡የሚያደርግ፡መልካም፡ዛፍ፡የለምና፥እንዲሁም፡መልካም፡ፍሬ፡የሚያደርግ፡ክፉ፡ዛፍ፡ የለም። 44፤ዛፍ፡ዅሉ፡ከፍሬው፡ይታወቃልና፤ከሾኽ፡በለስ፡አይለቅሙም፥ከዐጣጥ፡ቍጥቋጦም፡ወይን፡ አይቈርጡም። 45፤በልብ፡ሞልቶ፡ከተረፈው፡አፉ፡ይናገራልና፥መልካም፡ሰው፡ከልብ፡መልካም፡መዝገብ፡መልካሙን፡ ያወጣል፥ክፉ፡ሰውም፡ከልብ፡ክፉ፡መዝገብ፡ክፉውን፡ያወጣል። 46፤ስለ፡ምን፦ጌታ፡ሆይ፥ጌታ፡ሆይ፥ትሉኛላችኹ፥የምለውንም፡አታደርጉም፧ 47፤ወደ፡እኔ፡የሚመጣ፡ዅሉ፡ቃሌንም፡ሰምቶ፡የሚያደርገው፥ማንን፡እንዲመስል፡አሳያችዃለኹ። 48፤ቤት፡ሲሠራ፡አጥልቆ፡የቈፈረ፡በአለት፡ላይም፡የመሠረተ፡ሰውን፡ይመስላል፤ጐርፍም፡በመጣ፡ጊዜ፡ ወንዙ፡ያን፡ቤት፡ገፋው፥በአለት፡ላይም፡ስለ፡ተመሠረተ፡ሊያናውጠው፡አልቻለም። 49፤ሰምቶ፡የማያደርገው፡ግን፡ያለመሠረት፡በምድር፡ላይ፡ቤቱን፡የሠራ፡ሰውን፡ይመስላል፤ወንዙም፡ ገፋው፡ወዲያውም፡ወደቀ፡የዚያ፡ቤት፡አወዳደቅም፡ታላቅ፡ኾነ።

ምዕራፍ ፯

1፤ቃሉን፡ዅሉ፡በሕዝብ፡ዦሮዎች፡በጨረሰ፡ጊዜ፡ወደ፡ቅፍርናሖም፡ገባ። 2፤አንድ፡የመቶ፡አለቃም፡ነበረ፤የሚወደ፟ውም፡ባሪያው፡ታሞ፡ሊሞት፡ቀርቦ፡ነበር። 3፤ስለ፡ኢየሱስም፡በሰማ፡ጊዜ፡የአይሁድን፡ሽማግሌዎች፡ወደ፡ርሱ፡ላከና፡መጥቶ፡ባሪያውን፡እንዲያድን፡ ለመነው። 4፤እነርሱም፡ወደ፡ኢየሱስ፡መጥተው፦ይህን፡ልታደርግለት፡ይገ፟ባ፟ዋል፤ 5፤ሕዝባችንን፡ይወዳልና፥ምኵራብም፡ራሱ፡ሠርቶልናል፡ብለው፡አጽንተው፡ለመኑት። 6፤ኢየሱስም፡ከነርሱ፡ጋራ፡ኼደ።አኹንም፡ወደ፡ቤቱ፡በቀረበ፡ጊዜ፡የመቶው፡አለቃ፡ወዳጆቹን፡ወደ፡ርሱ፡ ላከ፤አለውም፦ጌታ፡ሆይ፡በቤቴ፡ጣራ፡በታች፡ልትገባ፡አይገ፟ባ፟ኝምና፥አትድከም፤ 7፤ስለዚህም፡ወዳንተ፡ልመጣ፡እንዲገባኝ፡ሰውነቴን፡አልቈጠርኹትም፤ነገር፡ግን፥ቃል፡ ተናገር፥ብላቴናዬም፡ይፈወሳል። 8፤እኔ፡ደግሞ፡ከሌላዎች፡በታች፡የምገዛ፡ሰው፡ነኝ፥ከእኔም፡በታች፡ወታደሮች፡አሉኝ፥አንዱንም፦ኺድ፡ ብለው፡ይኼዳል፥ሌላውንም፦ና፡ብለው፡ይመጣል፥ባሪያዬንም፦ይህን፡አድርግ፡ብለው፡ያደርጋል። 9፤ኢየሱስም፡ይህን፡ሰምቶ፡በርሱ፡ተደነቀ፥ዘወርም፡ብሎ፡ለተከተሉት፡ሕዝብ፦እላችዃለኹ፥በእስራኤልስ፡ እንኳ፡እንዲህ፡ያለ፡ትልቅ፡እምነት፡አላገኘኹም፡አላቸው። 10፤የተላኩትም፡ወደ፡ቤት፡ተመልሰው፡ባሪያውን፡ባለጤና፡ኾኖ፡አገኙት። 11፤በነገውም፡ናይን፡ወደምትባል፡ወደ፡አንዲት፡ከተማ፡ኼደ፥ደቀ፡መዛሙርቱም፡ብዙ፡ሕዝብም፡ከርሱ፡ ጋራ፡ዐብረው፡ኼዱ። 12፤ወደ፡ከተማዪቱም፡በር፡በቀረበ፡ጊዜ፥እንሆ፥የሞተ፡ሰው፡ተሸክመው፡አወጡ፤ርሱም፡ለእናቱ፡አንድ፡ ልጅ፡ነበረ፥ርሷም፡መበለት፡ነበረች፥ብዙም፡የከተማ፡ሕዝብ፡ከርሷ፡ጋራ፡ዐብረው፡ነበሩ። 13፤ጌታም፡ባያት፡ጊዜ፡ዐዘነላትና፦አታልቅሺ፡አላት። 14፤ቀርቦም፡ቃሬዛውን፡ነካ፥የተሸከሙትም፡ቆሙ፤አለውም፦አንተ፡ጐበዝ፥እልኻለኹ፥ተነሣ። 15፤የሞተውም፡ቀና፡ብሎ፡ተቀመጠ፡ሊናገርም፡ዠመረ፥ለእናቱም፡ሰጣት። 16፤ዅሉንም፡ፍርሀት፡ያዛቸውና፦ታላቅ፡ነቢይ፡በእኛ፡መካከል፡ተነሥቷል፥ደግሞ፦እግዚአብሔር፡ ሕዝቡን፡ጐበኘ፡እያሉ፡እግዚአብሔርን፡አመሰገኑ። 17፤ይህም፡ዝና፡ስለ፡ርሱ፡በይሁዳ፡ዅሉ፡በዙሪያውም፡ባለች፡አገር፡ዅሉ፡ወጣ። 18፤ደቀ፡መዛሙርቱም፡ለዮሐንስ፡እነዚህን፡ዅሉ፡አወሩ። 19፤ዮሐንስም፡ከደቀ፡መዛሙርቱ፡ኹለት፡ወደ፡ርሱ፡ጠርቶ፦የሚመጣው፡አንተ፡ነኽን፡ወይስ፡ሌላውን፡ እንጠብቅ፧ብሎ፡ወደ፡ኢየሱስ፡ላከ። 20፤ሰዎቹም፡ወደ፡ርሱ፡መጥተው፦መጥምቁ፡ዮሐንስ፦የሚመጣው፡አንተ፡ነኽን፡ወይስ፡ሌላውን፡ እንጠብቅ፧ብሎ፡ወዳንተ፡ላከን፡አሉት። 21፤በዚያች፡ሰዓት፡ከደዌና፡ከሥቃይ፡ከክፉዎች፡መናፍስትም፡ብዙዎችን፡ፈወሰ፥ለብዙ፡ዕውሮችም፡ማየትን፡ ሰጠ። 22፤ኢየሱስም፡መልሶ፦ኼዳችኹ፡ያያችኹትን፡የሰማችኹትንም፡ለዮሐንስ፡አውሩለት፤ዕውሮች፡ ያያሉ፥ዐንካሳዎችም፡ይኼዳሉ፥ለምጻሞችም፡ይነጻሉ፥ደንቈሮዎችም፡ይሰማሉ፥ሙታንም፡ ይነሣሉ፥ለድኻዎችም፡ወንጌል፡ይሰበካል፤ 23፤በእኔም፡የማይሰናከለው፡ዅሉ፡ብፁዕ፡ነው፡አላቸው። 24፤የዮሐንስ፡መልክተኛዎችም፡ከኼዱ፡በዃላ፥ለሕዝቡ፡ስለ፡ዮሐንስ፡ይናገር፡ዠመር፡እንዲህም፡ አለ፦ምን፡ልታዩ፡ወደ፡ምድረ፡በዳ፡ወጣችኹ፧ነፋስ፡የሚወዘውዘውን፡ሸምበቆን፧ወይስ፡ምን፡ልታዩ፡ ወጣችኹ፧ 25፤ቀጭን፡ልብስ፡የለበሰውን፡ሰውን፧እንሆ፥ጌጠኛ፡ልብስ፡የሚለብሱና፡በቅምጥልነት፡የሚኖሩ፡በነገሥታት፡ ቤት፡አሉ። 26፤ወይስ፡ምን፡ልታዩ፡ወጣችኹ፧ነቢይን፧አዎን፡እላችዃለኹ፥ከነቢይም፡የሚበልጠውን። 27፤እንሆ፥መንገድኽን፡በፊትኽ፡የሚጠርግ፡መልክተኛዬን፡በፊትኽ፡እልካለኹ፡ተብሎ፡የተጻፈለት፡ይህ፡ ነው። 28፤እላችዃለኹ፥ከሴቶች፡ከተወለዱት፡መካከል፡ከመጥምቁ፡ዮሐንስ፡የሚበልጥ፡ማንም፡ የለም፤በእግዚአብሔር፡መንግሥት፡ግን፡ከዅሉ፡የሚያንሰው፡ይበልጠዋል። 29፤የሰሙትም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ቀራጮች፡እንኳ፡ሳይቀሩ፡በዮሐንስ፡ጥምቀት፡ተጠምቀው፡እግዚአብሔርን፡ አጸደቁ፤ 30፤ፈሪሳውያንና፡ሕግ፡ዐዋቂዎች፡ግን፡በርሱ፡ስላልተጠመቁ፡የእግዚአብሔርን፡ምክር፡ከራሳቸው፡ጣሉ። 31፤እንግዲህ፡የዚችን፡ትውልድ፡ሰዎች፡በምን፡አስመስላቸዋለኹ፧ማንንስ፡ይመስላሉ፧ 32፤በገበያ፡የሚቀመጡትን፡ልጆች፡ይመስላሉ፥ርስ፡በርሳቸውም፡እየተጠራሩ።እንቢልታ፡ነፋንላችኹ፡ አልዘፈናችኹምም፤ሙሾ፡አወጣንላችኹ፡አላለቀሳችኹምም፡ይላል። 33፤መጥምቁ፡ዮሐንስ፡እንጀራ፡ሳይበላ፡የወይን፡ጠጅም፡ሳይጠጣ፡መጥቶ፡ነበርና፦ጋኔን፡አለበት፡ አላችኹት። 34፤የሰው፡ልጅ፡እየበላና፡እየጠጣ፡መጥቷልና፦እንሆ፥በላተኛና፡የወይን፡ጠጅ፡ጠጪ፥የቀራጮችና፡ የኀጢአተኛዎች፡ወዳጅ፡አላችኹት። 35፤ጥበብም፡ለልጆቿ፡ዅሉ፡ጸደቀች። 36፤ከፈሪሳውያንም፡አንድ፡ከርሱ፡ጋራ፡ይበላ፡ዘንድ፡ለመነው፤በፈሪሳዊው፡ቤትም፡ገብቶ፡በማእዱ፡ ተቀመጠ። 37፤እንሆም፡በዚያች፡ከተማ፡ኀጢአተኛ፡የነበረች፡አንዲት፡ሴት፤በፈሪሳዊው፡ቤት፡በማእዱ፡እንደ፡ ተቀመጠ፡ባወቀች፡ጊዜ፥ሽቱ፡የሞላበት፡የአልባስጥሮስ፡ቢልቃጥ፡አመጣች። 38፤በስተዃላውም፡በእግሩ፡አጠገብ፡ቆማ፡እያለቀሰች፡በእንባዋ፡እግሩን፡ታርስ፡ዠመር፥በራስ፡ጠጕሯም፡ ታብሰው፡እግሩንም፡ትስመው፡ሽቱም፡ትቀባው፡ነበር። 39፤የጠራው፡ፈሪሳዊም፡አይቶ፦ይህስ፡ነቢይ፡ቢኾን፥ይህች፡የምትዳስሰው፡ሴት፡ማን፡እንደ፡ኾነች፡ እንዴትስ፡እንደ፡ነበረች፡ባወቀ፡ነበር፥ኀጢአተኛ፡ናትና፥ብሎ፡በልቡ፡ዐሰበ። 40፤ኢየሱስም፡መልሶ፦ስምዖን፡ሆይ፥የምነግርኽ፡ነገር፡አለኝ፡አለው።ርሱም፦መምህር፡ሆይ፥ተናገር፡ አለ። 41፤ላንድ፡አበዳሪ፡ኹለት፡ተበዳሪዎች፡ነበሩት፡በአንዱ፡ዐምስት፡መቶ፡ዲናር፡ነበረበት፡በኹለተኛውም፡ ዐምሳ። 42፤የሚከፍሉትም፡ቢያጡ፡ለኹለቱም፡ተወላቸው።እንግዲህ፡ከነርሱ፡አብልጦ፡የሚወደ፟ው፡ማንኛው፡ነው፧ 43፤ስምዖንም፡መልሶ፦ብዙ፡የተወለቱ፡ይመስለኛል፡አለ።ርሱም፦በእውነት፡ፈረድኽ፡አለው። 44፤ወደ፡ሴቲቱም፡ዘወር፡ብሎ፡ስምዖንን፡እንዲህ፡አለው፦ይህችን፡ሴት፡ታያለኽን፧እኔ፡ወደ፡ቤትኽ፡ ገባኹ፥ውሃ፡ስንኳ፡ለእግሬ፡አላቀረብኽልኝም፤ርሷ፡ግን፡በእንባዋ፡እግሬን፡አራሰች፡በጠጕሯም፡አበሰች። 45፤አንተ፡አልሳምኸኝም፤ርሷ፡ግን፡ከገባኹ፡ዠምራ፡እግሬን፡ከመሳም፡አላቋረጠችም። 46፤አንተ፡ራሴን፡ዘይት፡አልቀባኸኝም፤ርሷ፡ግን፡እግሬን፡ሽቱ፡ቀባች። 47፤ስለዚህ፥እልኻለኹ፥እጅግ፡ወዳ፟ለችና፥ብዙ፡ያለው፡ኀጢአቷ፡ተሰርዮላታል፤ጥቂት፡ግን፡የሚሰረይለት፡ ጥቂት፡ይወዳል። 48፤ርሷንም፦ኀጢአትሽ፡ተሰርዮልሻል፡አላት። 49፤ከርሱም፡ጋራ፡በማእዱ፡ተቀምጠው፡የነበሩት፡በልባቸው፦ኀጢአትን፡እንኳ፡የሚያስተሰርይ፡ይህ፡ማን፡ ነው፧ይሉ፡ዠመር። 50፤ሴቲቱንም፦እምነትሽአድኖሻል፤ በሰላም፡ኺጂ፡አላት።

ምዕራፍ ፰

1፤ከዚህም፡በዃላ፡እየሰበከና፡ስለእግዚአብሔር፡መንግሥት፡የምሥራች፡እየተናገረ፡በየከተማዪቱ፡በየመንደሩም፡ ያልፍ፡ነበር፤ 2፤ዐሥራ፡ኹለቱም፡ከርሱ፡ጋራ፡ነበሩ፥ከክፉዎች፡መናፍስትና፡ከደዌም፡ተፈውሰው፡የነበሩ፡አንዳንድ፡ ሴቶች፤እነርሱም፡ሰባት፡አጋንንት፡የወጡላት፡መግደላዊት፡የምትባል፡ማርያም፥ 3፤የሄሮድስ፡አዛዥ፡የኩዛ፡ሚስት፡ዮሐናም፡ሶስናም፡ብዙዎች፡ሌላዎችም፡ኾነው፡በገንዘባቸው፡ያገለግሉት፡ ነበር። 4፤ብዙ፡ሕዝብም፡በተሰበሰቡ፡ጊዜ፡ከከተማዎችም፡ዅሉ፡ወደ፡ርሱ፡በመጡ፡ጊዜ፡በምሳሌ፡እንዲህ፡ሲል፡ ተናገራቸው፦ 5፤ዘሪ፡ዘሩን፡ሊዘራ፡ወጣ።ሲዘራም፡አንዳንዱ፡በመንገድ፡ዳር፡ወደቀ፡ተረገጠም፥የሰማይ፡ወፎችም፡ በሉት። 6፤ሌላውም፡በአለት፡ላይ፡ወደቀ፥በበቀለም፡ጊዜ፡ርጥበት፡ስላልነበረው፡ደረቀ። 7፤ሌላውም፡በሾኽ፡መካከል፡ወደቀ፥ሾኹም፡ዐብሮ፡በቀለና፡ዐነቀው። 8፤ሌላውም፡በመልካም፡መሬት፡ላይ፡ወደቀ፤በበቀለም፡ጊዜ፡መቶ፡ዕጥፍ፡አፈራ።ይህን፡በተናገረ፡ ጊዜ፦የሚሰማ፡ዦሮ፡ያለው፡ይስማ፡ብሎ፡ጮኸ። 9፤ደቀ፡መዛሙርቱም፦ይህ፡ምሳሌ፡ምንድር፡ነው፧ብለው፡ጠየቁት። 10፤ርሱም፡እንዲህ፡አለ፦ለእናንተ፡የእግዚአብሔርን፡መንግሥት፡ምስጢር፡ማወቅ፡ ተሰጥቷችዃል፤ለሌላዎች፡ግን፡እያዩ፡እንዳያዩ፡እየሰሙም፡እንዳያስተውሉ፡በምሳሌ፡ነው። 11፤ምሳሌው፡ይህ፡ነው።ዘሩ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ነው። 12፤በመንገድ፡ዳርም፡ያሉት፡የሚሰሙ፡ናቸው፤ከዚህ፡በዃላም፡ዲያብሎስ፡ይመጣል፡አምነውም፡ እንዳይድኑ፡ቃሉን፡ከልባቸው፡ይወስዳል። 13፤በአለት፡ላይም፡ያሉት፡ሲሰሙ፡ቃሉን፡በደስታ፡የሚቀበሉ፡ናቸው፤እነርሱም፡ለጊዜው፡ብቻ፡ያምናሉ፡ እንጂ፡በፈተና፡ጊዜ፡የሚክዱ፡ሥር፡የሌላቸው፡ናቸው። 14፤በሾኽ፡መካከልም፡የወደቀ፡እነዚህ፡የሚሰሙት፡ናቸው፤መንገዳቸውንም፡ኼደው፡በሕይወት፡ዘመን፡በዐሳብና፡በባለጠግነት፡ምቾት፡ይታነቃሉ፥ሙሉ፡ፍሬም፡አያፈሩም። 15፤በመልካም፡መሬት፡ላይም፡የወደቀ፡እነርሱ፡በመልካምና፡በበጎ፡ልብ፡ቃሉን፡ሰምተው፡የሚጠብቁት፡ በመጽናትም፡ፍሬ፡የሚያፈሩ፡ናቸው። 16፤መብራትንም፡አብርቶ፡በዕቃ፡የሚከድነው፡ወይም፡ከዐልጋ፡በታች፡የሚያኖረው፡የለም፥የሚገቡት፡ሰዎች፡ ብርሃኑን፡እንዲያዩ፡በመቅረዝ፡ላይ፡ያኖረዋል፡እንጂ። 17፤የማይገለጥ፡የተሰወረ፡የለምና፥የማይታወቅም፡ወደ፡ግልጥም፡የማይመጣ፡የተሸሸገ፡የለም። 18፤እንግዲህ፡እንዴት፡እንድትሰሙ፡ተጠበቁ፤ላለው፡ዅሉ፡ይሰጠዋልና፥ከሌለውም፡ዅሉ፥ያው፡ያለው፡ የሚመስለው፡እንኳ፡ይወሰድበታል። 19፤እናቱና፡ወንድሞቹም፡ወደ፡ርሱ፡መጡ፥ከሕዝቡም፡ብዛት፡የተነሣ፡ሊያገኙት፡አልተቻላቸውም። 20፤እናትኽና፡ወንድሞችኽ፡ሊያዩኽ፡ወደ፟ው፡በውጭ፡ቆመዋል፡ብለው፡ነገሩት። 21፤ርሱም፡መልሶ፦እናቴና፡ወንድሞቼስ፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ሰምተው፡የሚያደርጉት፡እነዚህ፡ናቸው፡ አላቸው። 22፤ከዕለታቱም፡በአንዱ፡ርሱ፡ከደቀ፡መዛሙርቱ፡ጋራ፡ወደ፡ታንኳ፡ገብቶ፦ወደባሕር፡ማዶ፡እንሻገር፡ አላቸው፤ተነሡም። 23፤ሲኼዱም፡አንቀላፋ።ዐውሎ፡ነፋስም፡በባሕር፡ላይ፡ወረደ፥ውሃውም፡ታንኳዪቱን፡ይሞላ፡ ነበርና፥ይጨነቁ፡ነበር። 24፤ቀርበውም፦አቤቱ፥አቤቱ፡ጠፋን፡እያሉ፡አስነሡት።ርሱም፡ነቅቶ፡ነፋሱንና፡የውሃውን፡ማዕበል፡ገሠጻቸው፤ተዉም፥ጽጥታም፡ኾነ። 25፤ርሱም፦እምነታችኹ፡የት፡ነው፧አላቸው።ፈርተውም፡ተደነቁ፥ርስ፡በርሳቸውም፦እንዲህ፡ነፋሳትንና፡ ውሃን፡እንኳ፡የሚያዝ፡ለርሱም፡የሚታዘዙለት፡ይህ፡ማን፡ነው፧አሉ። 26፤በገሊላም፡አንጻር፡ወዳለችው፡ወደጌርጌሴኖን፡አገር፡በታንኳ፡ደረሱ። 27፤ወደ፡ምድርም፡በወጣ፡ጊዜ፡አጋንንት፡ያደሩበት፡አንድ፡ሰው፡ከከተማ፡ወጥቶ፡ተገናኘው፥ከብዙ፡ ዘመንም፡ዠምሮ፡ልብስ፡ሳይለብስ፡በመቃብር፡እንጂ፡በቤት፡አይኖርም፡ነበር። 28፤ኢየሱስንም፡ባየ፡ጊዜ፡ጮኾ፡በፊቱ፡ተደፋ፡በታላቅ፡ድምፅም፦የልዑል፡እግዚአብሔር፡ልጅ፡ኢየሱስ፡ ሆይ፥ከአንተ፡ጋራ፡ምን፡አለኝ፧እንዳትሣቀየኝ፡እለምንኻለኹ፡አለ። 29፤ርኩሱን፡መንፈስ፡ከሰውዬው፡እንዲወጣ፡ያዘ፟ው፡ነበርና።ብዙ፡ዘመንም፡ይዞት፡ነበርና፥በሰንሰለትና፡ በእግር፡ብረትም፡ታስሮ፡ይጠበቅ፡ነበር፤እስራቱንም፡ሰብሮ፡በጋኔኑ፡ወደ፡ምድረ፡በዳ፡ይነዳ፡ነበር። 30፤ኢየሱስም፦ስምኽ፡ማን፡ነው፧ብሎ፡ጠየቀው።ርሱም፡ብዙዎች፡አጋንንት፡ገብተውበት፡ ነበርና፦ሌጌዎን፡አለው። 31፤ወደ፡ጥልቁም፡ሊኼዱ፡እንዳያዛቸው፡ለመኑት። 32፤በዚያም፡በተራራው፡የብዙ፡ዕሪያ፡መንጋ፡ይሰማሩ፡ነበር፤ወደ፡እነርሱም፡ሊገቡ፡እንዲፈቅድላቸው፡ ለመኑት፤ፈቀደላቸውም። 33፤አጋንንትም፡ከሰውዬው፡ወጥተው፡ወደ፡ዕሪያዎች፡ገቡ፥መንጋውም፡ከአፋፉ፡ወደ፡ባሕር፡ተጣደፉና፡ ሰጠሙ። 34፤እረኛዎችም፡የኾነውን፡ባዩ፡ጊዜ፡ሸሽተው፡በከተማውና፡በአገሩ፡አወሩት። 35፤የኾነውን፡ነገር፡ሊያዩ፡ወጥተውም፡ወደ፡ኢየሱስ፡መጡ፥አጋንንትም፡የወጡለትን፡ሰው፡ለብሶ፡ልቡም፡ ተመልሶ፡በኢየሱስ፡እግር፡አጠገብ፡ተቀምጦ፡አገኙትና፡ፈሩ። 36፤ያዩትም፡ደግሞ፡አጋንንት፡ያደሩበት፡ሰው፡እንዴት፡እንደ፡ዳነ፡አወሩላቸው። 37፤በዙሪያውም፡በጌርጌሴኖን፡አገር፡ያሉት፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ታላቅ፡ፍርሀት፡ይዟቸዋልና፥ከነርሱ፡እንዲኼድ፡ ለመኑት፡በታንኳም፡ገብቶ፡ተመለሰ። 38፤አጋንንት፡የወጡለት፡ሰውም፡ከርሱ፡ጋራ፡ይኖር፡ዘንድ፡ለመነው፤ 39፤ነገር፡ግን፦ወደ፡ቤትኽ፡ተመለስ፥እግዚአብሔር፡እንዴት፡ያለ፡ታላቅ፡ነገር፡እንዳደረገልኽ፡ንገር፡ ብሎ፡አሰናበተው።ኢየሱስም፡እንዴት፡ያለ፡ታላቅ፡ነገር፡እንዳደረገለት፡በከተማው፡ዅሉ፡እየሰበከ፡ኼደ። 40፤ኢየሱስም፡በተመለሰ፡ጊዜ፡ዅሉ፡ይጠብቁት፡ነበርና፥ሕዝቡ፡ተቀበሉት። 41፤እንሆም፥ኢያኢሮስ፡የሚባል፡ሰው፡መጣ፥ርሱም፡የምኵራብ፡አለቃ፡ነበረ፡በኢየሱስም፡እግር፡ላይ፡ ወድቆ፡ወደ፡ቤቱ፡እንዲገባ፡ለመነው፤ 42፤ዐሥራ፡ኹለት፡ዓመት፡የኾናት፡አንዲት፡ሴት፡ልጅ፡ነበረችውና፤ርሷም፡ለሞት፡ቀርባ፡ነበር።ሲኼድም፡ ሕዝቡ፡ያጨናንቁት፡ነበር። 43፤ከዐሥራ፡ኹለት፡ዓመትም፡ዠምሮ፡ደም፡የሚፈሳ፟ት፡ሴት፡ነበረች፥ትዳሯንም፡ዅሉ፡ለባለመድኀኒቶች፡ ከስራ፥ማንም፡ሊፈውሳት፡አልተቻለውም። 44፤በዃላውም፡ቀርባ፡የልብሱን፡ጫፍ፡ዳሰሰች፥የደሟም፡ፈሳሽ፡በዚያን፡ጊዜ፡ቆመ። 45፤ኢየሱስም፦የዳሰሰኝ፡ማን፡ነው፧አለ።ዅሉም፡በካዱ፡ጊዜ፥ጴጥሮስና፡ከርሱ፡ጋራ፡ የነበሩት፦አቤቱ፥ሕዝቡ፡ያጫንቁኻልና፥ያጋፉኽማል፤የዳሰሰኝ፡ማን፡ነው፡ትላለኽን፧አሉ። 46፤ኢየሱስ፡ግን፦አንድ፡ሰው፡ዳሶ፟ኛል፥ኀይል፡ከእኔ፡እንደ፡ወጣ፡እኔ፡ዐውቃለኹና፡አለ። 47፤ሴቲቱም፡እንዳልተሰወረች፡ባየች፡ጊዜ፡እየተንቀጠቀጠች፡መጥታ፡በፊቱ፡ተደፋች፥በምን፡ምክንያትም፡ እንደ፡ዳሰሰችው፡ፈጥናም፡እንደ፡ተፈወሰች፡በሕዝቡ፡ዅሉ፡ፊት፡አወራች። 48፤ርሱም፦ልጄ፡ሆይ፥እምነትሽ፡አድኖሻል፤በሰላም፡ኺጂ፡አላት። 49፤ርሱም፡ገና፡ሲናገር፡አንድ፡ሰው፡ከምኵራብ፡አለቃው፡ቤት፡መጥቶ፦ልጅኽ፡ሞታለች፤እንግዲህ፡ መምህሩን፡አታድክም፡አለ። 50፤ኢየሱስ፡ግን፡ሰምቶ፦አትፍራ፤እመን፡ብቻ፡ትድንማለች፡ብሎ፡መለሰለት። 51፤ወደ፡ቤትም፡ሲገባ፡ከጴጥሮስና፡ከያዕቆብ፡ከዮሐንስም፡ከብላቴናዪቱም፡አባትና፡እናት፡በቀር፡ማንም፡ ከርሱ፡ጋራ፡ይገባ፡ዘንድ፡አልፈቀደም። 52፤ዅሉም፡እያለቀሱላት፡ዋይ፡ዋይ፡ይሉ፡ነበር።ርሱ፡ግን፦አታልቅሱ፤ተኝታለች፡እንጂ፡አልሞተችም፡ አለ። 53፤እንደ፡ሞተችም፡ዐውቀው፡በጣም፡ሣቁበት። 54፤ርሱ፡ግን፡እጇን፡ይዞ፦አንቺ፡ብላቴና፥ተነሺ፡ብሎ፡ጮኸ። 55፤ነፍሷም፡ተመለሰች፥ፈጥናም፡ቆመች፥የምትበላውንም፡እንዲሰጧት፡አዘዘ። 56፤ወላጆቿም፡ተገረሙ፤ርሱ፡ግን፡የኾነውን፡ለማንም፡እንዳይነግሩ፡አዘዛቸው።

ምዕራፍ ፱

1፤ዐሥራ፡ኹለቱንም፡ሐዋርያት፡በአንድነት፡ወደ፡ርሱ፡ጠርቶ፡በአጋንንት፡ዅሉ፡ላይ፡ደዌንም፡ይፈውሱ፡ ዘንድ፡ኀይልና፡ሥልጣን፡ሰጣቸው፤ 2፤የእግዚአብሔርንም፡መንግሥት፡እንዲሰብኩና፡ድውዮችን፡እንዲፈውሱ፡ላካቸው፥ 3፤እንዲህም፡አላቸው፦በትርም፡ቢኾን፥ከረጢትም፡ቢኾን፥እንጀራም፡ቢኾን፥ብርም፡ቢኾን፡ለመንገድ፡ ምንም፡አትያዙ፥ኹለት፡እጀ፡ጠባብም፡አይኹንላችኹ። 4፤በማናቸውም፡በምትገቡበት፡ቤት፡በዚያ፡ተቀመጡ፡ከዚያም፡ውጡ። 5፤ማናቸውም፡የማይቀበሏችኹ፡ቢኾኑ፥ከዚያ፡ከተማ፡ወጥታችኹ፡ምስክር፡እንዲኾንባቸው፡ከእግራችኹ፡ ትቢያ፡አራግፉ። 6፤ወጥተውም፡ወንጌልን፡እየሰበኩና፡በስፍራው፡ዅሉ፡እየፈወሱ፡በየመንደሩ፡ያልፉ፡ነበር። 7፤የአራተኛው፡ክፍል፡ገዢ፡ሄሮድስም፡የተደረገውን፡ነገር፡ዅሉ፡ሰምቶ፥አንዳንድ፡ሰዎች፦ 8፤ዮሐንስ፡ከሙታን፡ተነሣ፥ሌላዎችም፦ኤልያስ፡ተገለጠ፥ሌላዎችም፦ከቀደሙት፡ነቢያት፡አንዱ፡ ተነሥቷል፡ይሉ፡ስለ፡ነበር፡አመነታ። 9፤ሄሮድስም፦ዮሐንስንስ፡እኔ፡ራሱን፡አስቈረጥኹት፤ይህ፡እንዲህ፡ያለ፡ነገር፡የምሰማበት፡ማን፡ ነው፧አለ።ሊያየውም፡ይሻ፡ነበር። 10፤ሐዋርያትም፡ተመልሰው፡ያደረጉትን፡ዅሉ፡ነገሩት።ከርሱ፡ጋራም፡ወስዷቸው፡ቤተ፡ሳይዳ፡ከምትባል፡ ከተማ፡አጠገብ፡ወደ፡ምድረ፡በዳ፡ለብቻው፡ፈቀቅ፡አለ። 11፤ሕዝቡም፡ዐውቀው፡ተከተሉት፤ተቀብሏቸውም፡ስለእግዚአብሔር፡መንግሥት፡ይነግራቸው፡ነበር፥መፈወስ፡ ያስፈለጋቸውንም፡ፈወሳቸው። 12፤ቀኑም፡ይመሽ፡ዠመር፤ዐሥራ፡ኹለቱም፡ቀርበው፦በዚህ፡በምድረ፡በዳ፡ነንና፡በዙሪያችን፡ወዳሉ፡ መንደሮችና፡ገጠሮች፡ኼደው፡እንዲያድሩና፡ምግብ፡እንዲያገኙ፡ሕዝቡን፡አሰናብት፡አሉት። 13፤ርሱ፡ግን፦እናንተ፡የሚበሉትን፡ስጧቸው፡አላቸው።እነርሱም፦ኼደን፡ለዚህ፡ዅሉ፡ሕዝብ፡ምግብ፡ ካልገዛን፥ከዐምስት፡እንጀራና፡ከኹለት፡ዓሣ፡የሚበልጥ፡የለንም፡አሉት፤ዐምስት፡ሺሕ፡ሰዎች፡ያኽሉ፡ነበርና። 14፤ለደቀ፡መዛሙርቱ፦በየክፍሉ፡ዐምሳ፡ዐምሳውን፡አስቀምጧቸው፡አላቸው። 15፤እንዲህም፡አደረጉ፡ዅሉንም፡አስቀመጧቸው። 16፤ዐምስቱንም፡እንጀራና፡ኹለቱን፡ዓሣ፡ይዞ፥ወደ፡ሰማይ፡አሻቅቦ፡አየና፡ባረካቸው፡ቈርሶም፡ለሕዝቡ፡ እንዲያቀርቡ፡ለደቀ፡መዛሙርቱ፡ሰጠ። 17፤ዅሉም፡በልተው፡ጠገቡ፥ከነርሱም፡የተረፈውን፡ቍርስራሽ፡ዐሥራ፡ኹለት፡መሶብ፡ወሰዱ። 18፤ለብቻውም፡ሲጸልይ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡ከርሱ፡ጋራ፡ነበሩና፦ሕዝቡ፡እኔ፡ማን፡እንደ፡ኾንኹ፡ ይላሉ፧ብሎ፡ጠየቃቸው። 19፤እነርሱም፡መልሰው፦መጥምቁ፡ዮሐንስ፥ሌላዎችም፦ኤልያስ፥ሌላዎችም፦ከቀደሙት፡ነቢያት፡አንዱ፡ ተነሥቷል፡ይላሉ፡አሉት። 20፤እናንተስ፡እኔ፡ማን፡እንደ፡ኾንኹ፡ትላላችኹ፧አላቸው።ጴጥሮስም፡መልሶ፦ከእግዚአብሔር፡የተቀባኽ፡ ነኽ፡አለ። 21-22፤ርሱ፡ግን፦የሰው፡ልጅ፡ብዙ፡መከራ፡ሊቀበል፡በሽማግሌዎችም፡በካህናት፡አለቃዎችም፡በጻፊዎችም፡ ሊጣል፡ሊገደልም፡በሦስተኛውም፡ቀን፡ሊነሣ፡ይገ፟ባ፟ዋል፡ብሎ፡ለማንም፡ይህን፡እንዳይናገሩ፡አስጠንቅቆ፡ አዘዘ። 23፤ለዅሉም፡እንዲህ፡አላቸው፦በዃላዬ፡ሊመጣ፡የሚወድ፡ቢኖር፥ራሱን፡ይካድ፡መስቀሉንም፡ዕለት፡ ዕለት፡ተሸክሞ፡ይከተለኝ። 24፤ነፍሱን፡ሊያድን፡የሚወድ፡ዅሉ፡ያጠፋታልና፤ስለ፡እኔ፡ነፍሱን፡የሚያጠፋ፡ዅሉ፡ግን፡ርሱ፡ያድናታል። 25፤ሰው፡ዓለሙን፡ዅሉ፡አትርፎ፡ራሱን፡ቢያጠፋ፡ወይም፡ቢያጐድል፡ምን፡ይጠቅመዋል፧ 26፤በእኔና፡በቃሌ፡የሚያፍር፡ዅሉ፥የሰው፡ልጅ፡በክብሩ፡በአባቱና፡በቅዱሳን፡መላእክቱ፡ክብርም፡ሲመጣ፡ በርሱ፡ያፍርበታል። 27፤እውነት፡እላችዃለኹ፥በዚህ፡ከሚቆሙት፡ሰዎች፡የእግዚአብሔርን፡መንግሥት፡እስኪያዩ፡ድረስ፡ሞትን፡ የማይቀምሱ፡አንዳንድ፡አሉ። 28፤ከዚህም፡ቃል፡በዃላ፡ስምንት፡ቀን፡ያኽል፡ቈይቶ፡ጴጥሮስንና፡ዮሐንስን፡ያዕቆብንም፡ይዞ፡ሊጸልይ፡ ወደ፡ተራራ፡ወጣ። 29፤ሲጸልይም፡የፊቱ፡መልክ፡ተለወጠ፤ልብሱም፡ተብለጭልጮ፡ነጭ፡ኾነ። 30፤እንሆም፥ኹለት፡ሰዎች፡እነርሱም፡ሙሴና፡ኤልያስ፡ከርሱ፡ጋራ፡ይነጋገሩ፡ነበር፤ 31፤በክብርም፡ታይተው፡በኢየሩሳሌም፡ሊፈጽም፡ስላለው፡ስለ፡መውጣቱ፡ይናገሩ፡ነበር። 32፤ነገር፡ግን፥ጴጥሮስንና፡ከርሱ፡ጋራ፡የነበሩት፡እንቅልፍ፡ከበደባቸው፤ነቅተው፡ግን፡ክብሩንና፡ከርሱ፡ ጋራ፡ቆመው፡የነበሩትን፡ኹለት፡ሰዎች፡አዩ። 33፤ከርሱም፡ሲለ፟ዩ፥ጴጥሮስ፡ኢየሱስን፦አቤቱ፥በዚህ፡መኾን፡ለእኛ፡መልካም፡ነውና፥አንድ፡ለአንተ፡ አንድም፡ለሙሴ፡አንድም፡ለኤልያስ፡ሦስት፡ዳሶች፡እንሥራ፡አለው፤የሚለውንም፡አያውቅም፡ነበር። 34፤ይህንም፡ሲናገር፡ደመና፡መጣና፡ጋረዳቸው፤ወደ፡ደመናውም፡ሲገቡ፡ሳሉ፡ፈሩ። 35፤ከደመናውም፦የመረጥኹት፡ልጄ፡ይህ፡ነው፥ርሱን፡ስሙት፡የሚል፡ድምፅ፡መጣ። 36፤ድምፁም፡ከመጣ፡በዃላ፡ኢየሱስ፡ብቻውን፡ኾኖ፡ተገኘ።እነርሱም፡ዝም፡አሉ፥ካዩትም፡ነገር፡በዚያ፡ወራት፡ምንም፡ለማንም፡አላወሩም። 37፤በነገውም፡ከተራራ፡ሲወርዱ፡ብዙ፡ሕዝብ፡ተገናኙት። 38፤እንሆም፥ከሕዝቡ፡አንድ፡ሰው፡እንዲህ፡እያለ፡ጮኸ፦መምህር፡ሆይ፥ለእኔ፡አንድ፡ልጅ፡ ነውና፥ልጄን፡እንድታይልኝ፡እለምንኻለኹ። 39፤እንሆም፥ጋኔን፡ይይዘዋል፥ድንገትም፡ይጮኻል፡ዐረፋም፡እያስደፈቀው፡ያንፈራግጠዋል፥እየቀጠቀጠም፡ በጭንቅ፡ይለቀዋል፤ 40፤ደቀ፡መዛሙርትኽንም፡እንዲያወጡት፡ለመንኹ፥አልቻሉምም። 41፤ኢየሱስም፡መልሶ፦እናንተ፡የማታምን፡ጠማማ፡ትውልድ፥እስከ፡መቼ፡ከእናንተ፡ጋራ፡ እኖራለኹ፧እስከ፡መቼስ፡እታገሣችዃለኹ፧ልጅኽን፡ወደዚህ፡አምጣው፡አለ። 42፤ሲቀርብም፡ጋኔኑ፡ጣለውና፡አንፈራገጠው፤ኢየሱስ፡ግን፡ርኩሱን፡መንፈስ፡ገሥጾ፡ብላቴናውን፡ፈወሰው፡ ለአባቱም፡መለሰው። 43፤ዅሉም፡ከእግዚአብሔር፡ታላቅነት፡የተነሣ፡ተገረሙ።ዅሉም፡ኢየሱስ፡ባደረገው፡ዅሉ፡ሲደነቁ፥ 44፤ለደቀ፡መዛሙርቱ፦የሰው፡ልጅ፡በሰው፡እጅ፡ይሰጥ፡ዘንድ፡አለውና፥እናንተ፡ይህን፡ቃል፡በዦሯችኹ፡ አኑሩ፡አለ። 45፤እነርሱ፡ግን፡ይህን፡ነገር፡አላስተዋሉም፥እንዳይገባቸውም፡ተሰውሮባቸው፡ነበር፤ስለዚህ፡ነገርም፡ እንዳይጠይቁት፡ፈሩ። 46፤ከነርሱም፡ማን፡እንዲበልጥ፡ክርክር፡ተነሣባቸው። 47፤ኢየሱስም፡የልባቸውን፡ዐሳብ፡ዐውቆ፡ሕፃንን፡ያዘ፤በአጠገቡም፡አቁሞ፦ 48፤ማንም፡ይህን፡ሕፃን፡በስሜ፡የሚቀበል፡እኔን፡ይቀበላል፤የሚቀበለኝም፡ዅሉ፡የላከኝን፡ይቀበላል፤ከኹላችኹ፡የሚያንስ፡ርሱ፡ታላቅ፡ነውና፥አላቸው። 49፤ዮሐንስም፡መልሶ፦አቤቱ፥አንድ፡ሰው፡በስምኽ፡አጋንንትን፡ሲያወጣ፡አየነው፥ከእኛ፡ጋራም፡ ስለማይከተል፡ከለከልነው፡አለው። 50፤ኢየሱስ፡ግን፦የማይቃወማችኹ፡ከእናንተ፡ጋራ፡ነውና፥አትከልክሉት፡አለው። 51፤የሚወጣበትም፡ወራት፡በቀረበ፡ጊዜ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ለመኼድ፡ፊቱን፡አቀና፥ 52፤በፊቱም፡መልክተኛዎችን፡ሰደደ።ኼደውም፡ሊያሰናዱለት፡ወደ፡አንድ፡ወደሳምራውያን፡መንደር፡ገቡ፤ 53፤ፊቱም፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡እንደሚኼድ፡ስለ፡ነበር፥አልተቀበሉትም። 54፤ደቀ፡መዛሙርቱም፡ያዕቆብና፡ዮሐንስ፡አይተው፦ጌታ፡ሆይ፥ኤልያስ፡ደግሞ፡እንዳደረገ፡እሳት፡ ከሰማይ፡ወርዶ፡ያጥፋቸው፡እንል፡ዘንድ፡ትወዳለኽን፧አሉት። 55፤ርሱ፡ግን፡ዘወር፡ብሎ፡ገሠጻቸውና፦ምን፡ዐይነት፡መንፈስ፡እንደ፡ኾነላችኹ፡አታውቁም፤ 56፤የሰው፡ልጅ፡የሰውን፡ነፍስ፡ሊያድን፡እንጂ፡ሊያጠፋ፡አልመጣም፡አለ።ወደ፡ሌላ፡መንደርም፡ኼዱ። 57፤እነርሱም፡በመንገድ፡ሲኼዱ፡አንድ፡ሰው፦ጌታ፡ሆይ፥ወደምትኼድበት፡ዅሉ፡እከተልኻለኹ፡አለው። 58፤ኢየሱስም፦ለቀበሮዎች፡ጕድጓድ፡ለሰማይም፡ወፎች፡መሳፈሪያ፡አላቸው፥ለሰው፡ልጅ፡ግን፡ራሱን፡ የሚያስጠጋበት፡የለውም፡አለው። 59፤ሌላውንም፦ተከተለኝ፡አለው።ርሱ፡ግን፦ጌታ፡ሆይ፥አስቀድሜ፡ልኺድና፡አባቴን፡እቀብር፡ዘንድ፡ፍቀድልኝ፡አለ። 60፤ኢየሱስም፦ሙታናቸውን፡እንዲቀብሩ፡ሙታንን፡ተዋቸው፤አንተስ፡ኼደኽ፡የእግዚአብሔርን፡መንግሥት፡ ስበክ፡አለው። 61፤ደግሞ፡ሌላው፦ጌታ፡ሆይ፥እከተልኻለኹ፤ነገር፡ግን፥አስቀድሜ፡ከቤቴ፡ሰዎች፡እንድሰናበት፡ ፍቀድልኝ፡አለ። 62፤ኢየሱስ፡ግን፦ማንም፡ዕርፍ፡በእጁ፡ይዞ፡ወደ፡ዃላ፡የሚመለከት፡ለእግዚአብሔር፡መንግሥት፡የተገባ፡ አይደለም፡አለው።

ምዕራፍ ፲

1፤ከዚህም፡በዃላ፡ጌታ፡ሌላዎቹን፡ሰብዓ፡ሾመ፥ኹለት፡ኹለትም፡አድርጎ፡ርሱ፡ሊኼድበት፡ወዳለው፡ ከተማና፡ስፍራ፡ዅሉ፡በፊቱ፡ላካቸው። 2፤አላቸውም፦መከሩስ፡ብዙ፡ነው፥ሠራተኛዎች፡ግን፡ጥቂቶች፡ናቸው፤እንግዴህ፡የመከሩን፡ጌታ፡ ለመከሩ፡ሠራተኛዎች፡እንዲልክ፡ለምኑት። 3፤ኺዱ፤እንሆ፥እንደ፡በጎች፡በተኵላዎች፡መካከል፡እልካችዃለኹ። 4፤ኰረጆም፡ከረጢትም፡ጫማም፡አትያዙ፤በመንገድም፡ለማንም፡እጅ፡አትንሡ። 5፤ወደምትገቡበት፡ቤት፡ዅሉ፡አስቀድማችኹ፦ሰላም፡ለዚህ፡ቤት፡ይኹን፡በሉ። 6፤በዚያም፡የሰላም፡ልጅ፡ቢኖር፥ሰላማችኹ፡ያድርበታል፤አለዚያም፡ይመለስላችዃል። 7፤በዚያም፡ቤት፡ከነርሱ፡ዘንድ፡ካለው፡እየበላችኹና፡እየጠጣችኹ፡ተቀመጡ፤ለሠራተኛ፡ደመ፡ወዙ፡ ይገ፟ባ፟ዋልና።ከቤት፡ወደ፡ቤት፡አትተላለፉ። 8፤ወደምትገቡባትም፡ከተማ፡ዅሉ፡ቢቀበሏችኹ፥ያቀረቡላችኹን፡ብሉ፤ 9፤በርሷም፡ያሉትን፡ድውዮችን፡ፈውሱና፦የእግዚአብሔር፡መንግሥት፡ወደ፡እናንተ፡ቀረበች፡በሏቸው። 10፤ነገር፡ግን፥ወደምትገቡባት፡ከተማ፡ዅሉ፡ባይቀበሏችኹ፥ወደ፡አደባባይዋ፡ወጥታችኹ። 11፤ከከተማችኹ፡የተጣበቀብንን፡ትቢያ፡እንኳን፡እናራግፍላችዃለን፤የእግዚአብሔር፡መንግሥት፡ግን፡ወደ፡ እናንተ፡እንደ፡ቀረበች፡ይህን፡ዕወቁ፡በሉ። 12፤እላችዃለኹ፥በዚያን፡ቀን፡ከዚያች፡ከተማ፡ይልቅ፡ለሰዶም፡ይቀልላታል። 13፤ወዮልሽ፡ኮራዚን፥ወዮልሽ፡ቤተ፡ሳይዳ፤በእናንተ፡የተደረገው፡ተኣምራት፡በጢሮስና፡በሲዶና፡ተደርጎ፡ ቢኾን፥ማቅ፡ለብሰው፡በዐመድም፡ተቀምጠው፡ከብዙ፡ጊዜ፡በፊት፡ንስሓ፡በገቡ፡ነበር። 14፤ነገር፡ግን፥በፍርድ፡ከእናንተ፡ይልቅ፡ለጢሮስና፡ለሲዶና፡ይቀልላቸዋል። 15፤አንቺም፡ቅፍርናሖም፥እስከ፡ሰማይ፡ከፍ፡አልሽን፧ወደ፡ሲኦል፡ትወርጃለሽ። 16፤የሚሰማችኹ፡እኔን፡ይሰማል፥እናንተንም፡የጣለ፡እኔን፡ይጥላል፤እኔንም፡የጣለ፡የላከኝን፡ይጥላል። 17፤ሰብዓውም፡በደስታ፡ተመልሰው፦ጌታ፡ሆይ፥አጋንንት፡ስንኳ፡በስምኽ፡ተገዝተውልናል፡አሉት። 18፤እንዲህም፡አላቸው፡ሰይጣንን፡እንደ፡መብረቅ፡ከሰማይ፡ሲወድቅ፡አየኹ። 19፤እንሆ፥እባቡንና፡ጊንጡን፡ትረግጡ፡ዘንድ፥በጠላትም፡ኀይል፡ዅሉ፡ላይ፡ሥልጣን፡ ሰጥቻችዃለኹ፥የሚጐዳችኹም፡ምንም፡የለም። 20፤ነገር፡ግን፥መናፍስት፡ስለ፡ተገዙላችኹ፡በዚህ፡ደስ፡አይበላችኹ፥ስማችኹ፡ግን፡በሰማያት፡ሰለ፡ተጻፈ፡ ደስ፡ይበላችኹ። 21፤በዚያን፡ሰዓት፡ኢየሱስ፡በመንፈስ፡ቅዱስ፡ሐሤት፡አደረገና፦የሰማይና፡የምድር፡ጌታ፡አባት፡ ሆይ፥ይህን፡ከጥበበኛዎችና፡ከአስተዋዮች፡ሰውረኽ፡ለሕፃናት፡ስለ፡ገለጥኽላቸው፥አመሰግናለኹ፤አዎን፡አባት፡ ሆይ፥ፈቃድኽ፡በፊትኽ፡እንዲህ፡ኾኗልና። 22፤ዅሉ፡ከአባቴ፡ዘንድ፡ተሰጥቶኛል፥ወልድንም፡ማን፡እንደ፡ኾነ፡ከአብ፡በቀር፡የሚያውቅ፡ የለም፥አብንም፡ማን፡እንደ፡ኾነ፡ከወልድ፡በቀር፡ወልድም፡ሊገልጥለት፡ከሚፈቅድ፡በቀር፡የሚያውቅ፡የለም፡አለ። 23፤ወደ፡ደቀ፡መዛሙርቱም፡ዘወር፡ብሎ፡ለብቻቸው፦የምታዩትን፡የሚያዩ፡ዐይኖች፡ብፁዓን፡ናቸው። 24፤እላችዃለኹና፥እናንተ፡የምታዩትን፡ብዙዎች፡ነቢያትና፡ነገሥታት፡ሊያዩ፡ወደዱ፡ አላዩምም፥የምትሰሙትንም፡ሊሰሙ፡ወደ፟ው፡አልሰሙም፡አለ። 25፤እንሆም፥አንድ፡ሕግ፡ዐዋቂ፡ሊፈትነው፡ተነሥቶ፦መምህር፡ሆይ፥የዘለዓለምን፡ሕይወት፡እንድወርስ፡ምን፡ላድርግ፧አለው። 26፤ርሱም፡በሕግ፡የተጻፈው፡ምንድር፡ነው፧እንዴትስ፡ታነባለኽ፧አለው። 27፤ርሱም፡መልሶ፦ጌታ፡አምላክኽን፡በፍጹም፡ልብኽ፡በፍጹም፡ነፍስኽም፡በፍጹም፡ኀይልኽም፡በፍጹም፡ ዐሳብኽም፡ውደድ፥ባልንጀራኽንም፡እንደ፡ራስኽ፡ውደድ፡አለው። 28፤ኢየሱስም፦እውነት፡መለስኽ፤ይህን፡አድርግ፡በሕይወትም፡ትኖራለኽ፡አለው። 29፤ርሱ፡ግን፡ራሱን፡ሊያጸድቅ፡ወዶ፟፡ኢየሱስን፦ባልንጀራዬስ፡ማን፡ነው፧አለው። 30፤ኢየሱስም፡መልሶ፡እንዲህ፡አለ፦አንድ፡ሰው፡ከኢየሩሳሌም፡ወደ፡ኢያሪኮ፡ወረደ፡በወንበዴዎችም፡እጅ፡ ወደቀ፤እነርሱም፡ደግሞ፡ገፈፉት፡ደበደቡትም፡በሕይወትና፡በሞት፡መካከልም፡ትተውት፡ኼዱ። 31፤ድንገትም፡አንድ፡ካህን፡በዚያ፡መንገድ፡ወረደ፥አይቶትም፡ገለል፡ብሎ፡ዐለፈ። 32፤እንዲሁም፡ደግሞ፡አንድ፡ሌዋዊ፡ወደዚያ፡ስፍራ፡መጣና፡አይቶት፥ገለል፡ብሎ፡ዐለፈ። 33፤አንድ፡ሳምራዊ፡ግን፡ሲኼድ፡ወደ፡ርሱ፡መጣ፥አይቶትም፡ዐዘነለት፤ 34፤ቀርቦም፡ዘይትና፡የወይን፡ጠጅ፡በቍስሎቹ፡ላይ፡አፍሶ፟፡አሰራቸው፤በራሱ፡አህያም፡ላይ፡አስቀምጦት፡ ወደእንግዳዎች፡ማደሪያ፡ወሰደው፥ጠበቀውም። 35፤በማግስቱም፡ኹለት፡ዲናር፡አውጥቶ፡ለባለቤቱ፡ሰጠና፦ጠብቀው፥ከዚህም፡በላይ፡የምትከስረውን፡ዅሉ፡ እኔ፡ስመለስ፡እከፍልኻለኹ፡አለው። 36፤እንግዲህ፡ከነዚህ፡ከሦስቱ፡በወንበዴዎች፡እጅ፡ለወደቀው፡ባልንጀራ፡የኾነው፡ማንኛው፡ይመስልኻል፧ 37፤ርሱም፦ምሕረት፡ያደረገለትአለ። ኢየሱስም:ኺድ፥አንተም፡እንዲሁ፡አድርግ፡አለው። 38፤ሲኼዱም፡ርሱ፡ወደ፡አንዲት፡መንደር፡ገባ፤ማርታ፡የተባለች፡አንዲት፡ሴትም፡በቤቷ፡ተቀበለችው። 39፤ለርሷም፡ማርያም፡የምትባል፡እኅት፡ነበረቻት፥ርሷም፡ደግሞ፡ቃሉን፡ልትሰማ፡በኢየሱስ፡እግር፡አጠገብ፡ ተቀምጣ፡ነበር። 40፤ማርታ፡ግን፡አገልግሎት፡ስለ፡በዛባት፡ባከነች፤ቀርባም፦ጌታ፡ሆይ፥እኔ፡እንድሠራ፡እኅቴ፡ብቻዬን፡ ስትተወኝ፡አይገድኽምን፧እንኪያስ፡እንድታግዘኝ፡ንገራት፡አለችው። 41፤ኢየሱስም፡መልሶ፦ማርታ፥ማርታ፥በብዙ፡ነገር፡ትጨነቂያለሽ፡ትታወኪማለሽ፥ 42፤የሚያስፈልገው፡ግን፡ጥቂት፡ወይም፡አንድ፡ነገር፡ነው፤ማርያምም፡መልካም፡ዕድልን፡መርጣለች፡ ከርሷም፡አይወሰድባትም፡አላት።

ምዕራፍ ፲፩

1፤ርሱም፡ባንድ፡ስፍራ፡ይጸልይ፡ነበር፥በጨረሰም፡ጊዜ፡ከደቀ፡መዛሙርቱ፡አንዱ፦ጌታ፡ሆይ፥ዮሐንስ፡ ደቀ፡መዛሙርቱን፡እንዳስተማረ፡እንጸልይ፡ዘንድ፡አስተምረን፡አለው። 2፤አላቸውም፦ስትጸልዩ፡እንዲህ፡በሉ፦

በሰማያት፡የምትኖር፡አባታችን፡ሆይ፤ስምኽ፡ይቀደስ፤መንግሥትኽ፡ትምጣ፤ፈቃድኽ፡በሰማይ፡እንደ፡ኾነች፡እንዲሁ፡በምድር፡ትኹን፤3፤የዕለት፡እንጀራችንን፡ዕለት፡ዕለት፡ስጠን፤4፤ኀጢአታችንንም፡ይቅር፡በለን፥እኛ፡ደግሞ፡የበደሉንን፡ዅሉ፡ይቅር ብለናልና፤ከክፉ፡አድነን፡እንጂ፡ወደ፡ፈተና፡አታግባን።

5፤እንዲህም፡አላቸው፦ከእናንተ፡ማናቸውም፡ወዳጅ፡ያለው፥በእኩል፡ሌሊትስ፡ወደ፡ርሱ፡ኼዶ፦ወዳጄ፡ ሆይ፥ሦስት፡እንጀራ፡አበድረኝ፥ 6፤አንድ፡ወዳጄ፡ከመንገድ፡ወደ፡እኔ፡መጥቶ፡የማቀርብለት፡የለኝምና፡ይላልን፧ 7፤ያም፡ከውስጥ፡መልሶ፦አታድክመኝ፤አኹን፡ደጁ፡ተቈልፏል፡ልጆቼም፡ከእኔ፡ጋራ፡በዐልጋ፡ላይ፡ አሉ፤ተነሥቼ፡ልሰጥኽ፡አልችልም፡ይላልን፧ 8፤እላችዃለኹ፥ወዳጅ፡ስለ፡ኾነ፡ተነሥቶ፡ባይሰጠው፡እንኳ፥ስለ፡ንዝነዛው፡ተነሥቶ፡የሚፈልገውን፡ዅሉ፡ ይሰጠዋል። 9፤ እኔም እላችዃለኹ፥ለምኑ፥ይሰጣችኹ ማል፤ፈልጉ፥ታገኙማላችኹ፤መዝጊያን፡ አንኳኩ፥ይከፍትላችኹማል። 10፤የሚለምን፡ዅሉ፡ይቀበላልና፥የሚፈልግም፡ያገኛል፥መዝጊያውንም፡ለሚያንኳኳው፡ይከፈትለታል። 11፤አባት፡ከኾናችኹ፡ከእናንተ፡ከማንኛችኹም፡ልጁ፡እንጀራ፡ቢለምነው፥ርሱም፡ድንጋይ፡ይሰጠዋልን፧ዓሣ፡ ደግሞ፡ቢለምነው፡በዓሣ፡ፋንታ፡እባብ፡ይሰጠዋልን፧ 12፤ወይስ፡ዕንቍላል፡ቢለምነው፡ጊንጥ፡ይሰጠዋልን፧ 13፤እንኪያስ፡እናንተ፡ክፉዎች፡ስትኾኑ፡ለልጆቻችኹ፡መልካም፡ስጦታ፡መስጠት፡ካወቃችኹ፥በሰማይ፡ ያለው፡አባት፡ለሚለምኑት፡እንዴት፡አብልጦ፡መንፈስ፡ቅዱስን፡ይሰጣቸው፧ 14፤ዲዳውንም፡ጋኔን፡ያወጣ፡ነበር፤ጋኔኑም፡ከወጣ፡በዃላ፡ዲዳው፡ተናገረ፡ሕዝቡም፡ተደነቁ፤ 15፤ነገር፡ግን፥ከነርሱ፡አንዳንዱ፦በብዔል፡ዜቡል፡በአጋንንት፡አለቃ፡አጋንንትን፡ያወጣል፡አሉ። 16፤ሌላዎችም፡ሲፈትኑት፡ከሰማይ፡ምልክት፡ከርሱ፡ይፈልጉ፡ነበር። 17፤ርሱ፡ግን፡ዐሳባቸውን፡ዐውቆ፡እንዲህ፡አላቸው፦ርስ፡በርሷ፡የምትለያይ፡መንግሥት፡ዅሉ፡ ትጠፋለች፤ቤትም፡በቤት፡ላይ፡ይወድቃል። 18፤እኔ፡አጋንንትን፡በብዔል፡ዜቡል፡እንዳወጣ፡ትላላችኹና፡ሰይጣን፡ደግሞ፡ርስ፡በርሱ፡ከተለያየ፡ መንግሥቱ፡እንዴት፡ትቆማለች፧ 19፤እኔስ፡በብዔል፡ዜቡል፡አጋንንትን፡የማወጣ፡ከኾንኹ፥ልጆቻችኹ፡በማን፡ያወጧቸዋል፧ስለዚህ፡እነርሱ፡ ፈራጆች፡ይኾኑባችዃል። 20፤እኔ፡ግን፡በእግዚአብሔር፡ጣት፡አጋንንትን፡የማወጣ፡ከኾንኹ፥እንግዲህ፡የእግዚአብሔር፡መንግሥት፡ ወደ፡እናንተ፡ደርሳለች። 21፤ኀይለኛ፡ሰው፡ጋሻና፡ጦር፡ይዞ፡የራሱን፡ግቢ፡ቢጠብቅ፥ያለው፡ገንዘቡ፡በሰላም፡ይኾናል፤ 22፤ከርሱ፡ይልቅ፡የሚበረታ፡መጥቶ፡ሲያሸንፈው፡ግን፥ታምኖበት፡የነበረውን፡ጋሻና፡ጦር፡ይወስድበታል፡ ምርኮውንም፡ያካፍላል። 23፤ከእኔ፡ጋራ፡ያልኾነ፡ይቃወመኛል፥ከእኔ፡ጋራም፡የማያከማች፡ይበትናል። 24፤ርኩስ፡መንፈስ፡ከሰው፡በወጣ፡ጊዜ፡ዕረፍትን፡እየፈለገ፡ውሃ፡በሌለበት፡ቦታ፡ ያልፋል፤ባያገኝም፦ወደወጣኹበት፡ቤቴ፡እመለሳለኹ፡ይላል፤ 25፤ሲመጣም፡ተጠርጎ፡አጊጦም፡ያገኘዋል። 26፤ከዚያ፡ወዲያ፡ይኼድና፡ከርሱ፡የከፉትን፡ሌላዎችን፡ሰባት፡አጋንንት፡ከርሱ፡ጋራ፡ይይዛል፥ገብተውም፡ በዚያ፡ይኖራሉ፤ለዚያም፡ሰው፡ከፊተኛው፡ይልቅ፡የዃለኛው፡ይብስበታል። 27፤ይህንም፡ሲናገር፥ከሕዝቡ፡አንዲት፡ሴት፡ድምፇን፡ከፍ፡አድርጋ፦የተሸከመችኽ፡ማሕፀንና፡ የጠባኻቸው፡ጡቶች፡ብፁዓን፡ናቸው፡አለችው። 28፤ርሱ፡ግን፦አዎን፥ብፁዓንስ፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ሰምተው፡የሚጠብቁት፡ናቸው፡አለ። 29፤ብዙ፡ሕዝብም፡በተሰበሰቡ፡ጊዜ፡እንዲህ፡ይል፡ዠመር፦ይህ፡ትውልድ፡ክፉ፡ነው፤ምልክት፡ ይፈልጋል፥ከነቢዩም፡ከዮናስ፡ምልክት፡በቀር፡ምልክት፡አይሰጠውም። 30፤ዮናስ፡ለነነዌ፡ሰዎች፡ምልክት፡እንደ፡ኾናቸው፥እንዲሁ፡ደግሞ፡የሰው፡ልጅ፡ለዚህ፡ትውልድ፡ምልክት፡ ይኾናል። 31፤ንግሥተ፡አዜብ፡በፍርድ፡ከዚህ፡ትውልድ፡ሰዎች፡ጋራ፡ተነሥታ፡ትፈርድባቸዋለች፤የሰሎሞንን፡ጥበብ፡ ለመስማት፡ከምድር፡ዳር፡መጥታለችና፥እንሆም፥ከሰሎሞን፡የሚበልጥ፡ከዚህ፡አለ። 32፤የነነዌ፡ሰዎች፡በፍርድ፡ከዚህ፡ትውልድ፡ጋራ፡ተነሥተው፡ይፈርዱበታል፤በዮናስ፡ስብከት፡ንስሓ፡ ገብተዋልና፥እንሆም፥ከዮናስ፡የሚበልጥ፡ከዚህ፡አለ። 33፤መብራትንም፡አብርቶ፡በስውር፡ወይም፡በእንቅብ፡በታች፡የሚያኖረው፡የለም፥የሚገቡ፡ሰዎች፡ብርሃኑን፡ እንዲያዩ፡በመቅረዝ፡ላይ፡ያኖረዋል፡እንጂ። 34፤የሰውነትኽ፡መብራት፡ዐይንኽ፡ናት።ዐይንኽ፡ጤናማ፡በኾነች፡ጊዜ፡ሰውነትኽ፡ዅሉ፡ደግሞ፡ብሩህ፡ ይኾናል።ዐይንኽ፡ታማሚ፡በኾነች፡ጊዜ፡ግን፡ሰውነትኽ፡ደግሞ፡የጨለመ፡ይኾናል። 35፤እንግዲህ፡ባንተ፡ያለው፡ብርሃን፡ጨለማ፡እንዳይኾን፡ተመልከት። 36፤እንግዲህ፡ሰውነትኽ፡ዅሉ፡የጨለማ፡ቍራጭ፡የሌለበት፡ብሩህ፡ቢኾን፥መብራት፡በደመቀ፡ብርሃን፡ እንደሚያበራልኽ፡በጭራሽ፡ብሩህ፡ይኾናል። 37፤ይህንንም፡ሲናገር፡አንድ፡ፈሪሳዊ፡ከርሱ፡ጋራ፡ምሳ፡ይበላ፡ዘንድ፡ለመነው፡ገብቶም፡ተቀመጠ። 38፤ከምሳም፡በፊት፡አስቀድሞ፡እንዳልታጠበ፡ባየው፡ጊዜ፥ፈሪሳዊው፡ተደነቀ። 39፤ጌታም፡እንዲህ፡አለው፦አኹን፡እናንተ፡ፈሪሳውያን፡የጽዋውንና፡የወጭቱን፡ውጭ፡ ታጠራላችኹ፥ውስጣችኹ፡ግን፡ቅሚያና፡ክፋት፡ሞልቶበታል፡ 40፤እናንት፡ደንቈሮዎች፥የውጩን፡የፈጠረ፡የውስጡን፡ደግሞ፡አልፈጠረምን፧ 41፤ነገር፡ግን፥በውስጥ፡ያለውን፡ምጽዋት፡አድርጋችኹ፡ስጡ፥እንሆም፥ዅሉ፡ንጹሕ፡ይኾንላችዃል። 42፤ነገር፡ግን፥እናንተ፡ፈሪሳውያን፥ከአዝሙድና፡ከጤና፡አዳም፡ከአትክልትም፡ዅሉ፡ዓሥራት፡ ስለምታወጡ፥ፍርድንና፡እግዚአብሔርን፡መውደድ፡ስለምትተላለፉ፥ወዮላችኹ፤ነገር፡ግን፥ሌላውን፡ሳትተዉ፡ ይህን፡ልታደርጉት፡ይገ፟ባ፟ችኹ፡ነበር። 43፤እናንተ፡ፈሪሳውያን፥በምኵራብ፡የከበሬታ፡ወንበር፡በገበያም፡ሰላምታ፡ስለምትወዱ፥ወዮላችኹ። 44፤እናንተ፡ግብዞች፡ጻፊዎችና፡ፈሪሳውያን፥ሰዎች፡ሳያውቁ፡በላዩ፡የሚኼዱበት፡የተሰወረ፡መቃብር፡ስለምትመስሉ፥ወዮላችኹ። 45፤ከሕግ፡ዐዋቂዎችም፡አንዱ፡መልሶ፦መምህር፡ሆይ፥ይህን፡ማለትኽ፡እኛን፡ደግሞ፡መስደብኽ፡ነው፡ አለው። 46፤ርሱም፡እንዲህ፡አለ፦እናንተ፡ደግሞ፡ሕግ፡ዐዋቂዎች፥አስቸጋሪ፡ሸክም፡ለሰዎች፡ ስለምታሸክሙ፥ራሳችኹም፡በአንዲት፡ጣታችኹ፡ስንኳ፡ሸክሙን፡ስለማትነኩት፥ወዮላችኹ። 47፤አባቶቻችኹ፡የገደሏቸውን፡የነቢያትን፡መቃብር፡ስለምትሠሩ፥ወዮላችኹ። 48፤እንግዲህ፡ለአባቶቻችኹ፡ሥራ፡ትመሰክራላችኹ፡ትስማማላችኹም፤እነርሱ፡ገድለዋቸዋልና፥እናንተም፡ መቃብራቸውን፡ትሠራላችኹ። 49፤ስለዚህ፡ደግሞ፥የእግዚአብሔር፡ጥበብ፡እንዲህ፡አለች፦ወደ፡እነርሱ፡ነቢያትንና፡ሐዋርያትን፡ እልካለኹ፥ከነርሱም፡ይገድላሉ፥ያሳድዱማል፥ 50፤ዓለም፡ከተፈጠረ፡ዠምሮ፡የፈሰሰው፡የነቢያት፡ዅሉ፡ደም፥ 51፤ከአቤል፡ደም፡ዠምሮ፡በመሠዊያውና፡በቤተ፡መቅደስ፡መካከል፡እስከ፡ጠፋው፥እስከ፡ዘካርያስ፡ደም፡ ድረስ፥ከዚህ፡ትውልድ፡እንዲፈለግ፡አዎን፡እላችዃለኹ፥ከዚህ፡ትውልድ፡ይፈለጋል። 52፤እናንተ፡ሕግ፡ዐዋቂዎች፥የዕውቀትን፡መክፈቻ፡ስለ፡ወሰዳችኹ፥ወዮላችኹ፡ራሳችኹ፡አልገባችኹም፡ የሚገቡትንም፡ከለከላችኹ። 53-54፤ይህንም፡ሲናገራቸው፥ጻፊዎችና፡ፈሪሳውያን፡በአፉ፡የተናገረውን፡ሊነጥቁ፡ሲያደቡ፥እጅግ፡ ይቃወሙና፡ስለ፡ብዙ፡ነገር፡እንዲናገር፡ያነሣሡ፡ዠመር።

ምዕራፍ ፲፪

1፤በዚያን፡ጊዜ፡የሕዝብ፡አእላፍ፡ርስ፡በርሳቸው፡እስኪረጋገጡ፡ድረስ፡ተሰብስበው፡ሳሉ፥ለደቀ፡ መዛሙርቱ፡እንዲህ፡ይል፡ዠመር።አስቀድማችኹ፡ከፈሪሳውያን፡ርሾ፡ተጠበቁ፥ርሱም፡ግብዝነት፡ነው። 2፤ነገር፡ግን፥የማይገለጥ፡የተከደነ፥የማይታወቅም፡የተሰወረ፡ምንም፡የለም። 3፤ስለዚህ፥በጨለማ፡የምትናገሩት፡ዅሉ፡በብርሃን፡ይሰማል፥በዕልፍኝም፡ውስጥ፡በዦሮ፡የምትናገሩት፡በሰገነት፡ላይ፡ይሰበካል። 4፤ለእናንተም፡ለወዳጆቼ፡እላችዃለኹ፥ሥጋን፡የሚገድሉትን፡በዃላም፡አንድ፡ስንኳ፡የሚበልጥ፡ሊያደርጉ፡ የማይችሉትን፡አትፍሩ። 5፤እኔ፡ግን፡የምትፈሩትን፡አሳያችዃለኹ፤ከገደለ፡በዃላ፡ወደ፡ገሃነም፡ለመጣል፡ሥልጣን፡ያለውን፡ ፍሩ።አዎን፡እላችዃለኹ፥ርሱን፡ፍሩ። 6፤ዐምስት፡ድንቢጦች፡በዐሥር፡ሳንቲም፡ይሸጡ፡የለምን፧ከነርሱም፡አንዲቱ፡ስንኳ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ አትረሳም። 7፤ነገር፡ግን፥የእናንተ፡የራሳችኹ፡ጠጕር፡ዅሉ፡እንኳ፡የተቈጠረ፡ነው፤እንግዲያስ፡አትፍሩ፡ከብዙ፡ ድንቢጦች፡ትበልጣላችኹ። 8፤እላችኹማለኹ፥በሰው፡ፊት፡የሚመሰክርልኝ፡ዅሉ፥የሰው፡ልጅ፡ደግሞ፡በእግዚአብሔር፡መላእክት፡ ፊት፡ይመሰክርለታል፤ 9፤በሰውም፡ፊት፡የሚክደኝ፡በእግዚአብሔር፡መላእክት፡ፊት፡ይካዳል። 10፤በሰው፡ልጅም፡ላይ፡ቃል፡የሚናገር፡ዅሉ፡ይሰረይለታል፤መንፈስ፡ቅዱስን፡የሚሰድብ፡ግን፡አይሰረይለትም። 11፤ወደ፡ምኵራቦችና፡ወደ፡መኳንንቶችም፡ወደ፡ገዢዎችም፡ሲጐትቷችኹ፥እንዴት፡ወይም፡ምን፡ እንድትመልሱ፡ወይም፡እንድትናገሩ፡አትጨነቁ፤ 12፤መንፈስ፡ቅዱስ፡በዚያች፡ሰዓት፡ልትናገሩ፡የሚገ፟ባ፟ችኹን፡ያስተምራችዃልና። 13፤ከሕዝቡም፡አንድ፡ሰው፦መምህር፡ሆይ፥ርስቱን፡ከእኔ፡ጋራ፡እንዲካፈል፡ለወንድሜ፡ንገረው፡አለው። 14፤ርሱም፦አንተ፡ሰው፥ፈራጅና፡አካፋይ፡በላያችኹ፡እንድኾን፡ማን፡ሾመኝ፧አለው። 15፤የሰው፡ሕይወት፡በገንዘቡ፡ብዛት፡አይደለምና፡ተጠንቀቁ፥ከመጐምዠትም፡ዅሉ፡ተጠበቁ፡አላቸው። 16፤ምሳሌም፡ነገራቸው፡እንዲህ፡ሲል፦አንድ፡ባለጠጋ፡ሰው፡ዕርሻ፡እጅግ፡ፍሬያም፡ኾነችለት። 17፤ርሱም፦ፍሬዬን፡የማከማችበት፡ስፍራ፡ዐጥቻለኹና፡ምን፡ላድርግ፧ብሎ፡በልቡ፡ዐሰበ። 18፤እንዲህ፡አደርጋለኹ፤ጐተራዬን፡አፍርሼ፡ሌላ፡የሚበልጥ፡እሠራለኹ፥በዚያም፡ፍሬዬንና፡በረከቴን፡ ዅሉ፡አከማቻለኹ፤ 19፤ነፍሴንም፦አንቺ፡ነፍሴ፥ለብዙ፡ዘመን፡የሚቀር፡ብዙ፡በረከት፡አለሽ፤ዕረፊ፥ብዪ፥ጠጪ፥ደስ፡ ይበልሽ፡እላታለኹ፡አለ። 20፤እግዚአብሔር፡ግን፦አንተ፡ሰነፍ፥በዚች፡ሌሊት፡ነፍስኽን፡ከአንተ፡ሊወስዷት፡ይፈልጓታል፤ይህስ፡ የሰበሰብኸው፡ለማን፡ይኾናል፧አለው። 21፤ለራሱ፡ገንዘብ፡የሚያከማች፥በእግዚአብሔር፡ዘንድም፡ባለጠጋ፡ያልኾነ፡እንዲህ፡ነው። 22፤ለደቀ፡መዛሙርቱም፡እንዲህ፡አለ፦ስለዚህ፡እላችዃለኹ፥ለነፍሳችኹ፡በምትበሉት፡ወይም፡ለሰውነታችኹ፡በምትለብሱት፡አትጨነቁ። 23፤ነፍስ፡ከመብል፡ሰውነትም፡ከልብስ፡ይበልጣልና። 24፤ቍራዎችን፡ተመልከቱ፤አይዘሩም፡አያጭዱምም፥ዕቃ፡ቤትም፡ወይም፡ጐተራ፡የላቸውም፥እግዚአብሔርም፡ይመግባቸዋል፤እናንተስ፡ከወፎች፡እንዴት፡ትበልጣላችኹ፧ 25፤ከእናንተ፡ተጨንቆ፡በቁመቱ፡ላይ፡አንድ፡ክንድ፡መጨመር፡የሚችል፡ማን፡ነው፧ 26፤እንግዲህ፡ትንሹን፡ነገር፡ስንኳ፡የማትችሉ፡ከኾናችኹ፥ስለ፡ምን፡በሌላ፡ትጨነቃላችኹ፧ 27፤አበባዎችን፡እንዴት፡እንዲያድጉ፡ተመልከቱ፤አይደክሙም፡አይፈትሉምም፤ነገር፡ ግን፥እላችዃለኹ፥ሰሎሞንስ፡እንኳ፡በክብሩ፡ዅሉ፡ከነዚህ፡እንደ፡አንዲቱ፡አለበሰም። 28፤እግዚአብሔር፡ግን፡ዛሬ፡ያለውን፡ነገም፡ወደ፡እቶን፡የሚጣለውን፡በሜዳ፡የኾነውን፡ሣር፡እንዲህ፡ የሚያለብሰው፡ከኾነ፥እናንተ፡እምነት፡የጐደላችኹ፥እናንተንማ፡ይልቁን፡እንዴት፧ 29፤እናንተም፡የምትበሉትን፡የምትጠጡትንም፡አትፈልጉ፥አታወላውሉም፤ 30፤ይህንስ፡ዅሉ፡በዓለም፡ያሉ፡አሕዛብ፡ይፈልጉታልና፤የእናንተም፡አባት፡ይህ፡እንዲያስፈልጋችኹ፡ ያውቃል። 31፤ዳሩ፡ግን፡መንግሥቱን፡ፈልጉ፡ይህም፡ዅሉ፡ይጨመርላችዃል። 32፤አንተ፡ታናሽ፡መንጋ፥መንግሥትን፡ሊሰጣችኹ፡የአባታችኹ፡በጎ፡ፈቃድ፡ነውና፥አትፍሩ። 33፤ያላችኹን፡ሽጡ፡ምጽዋትም፡ስጡ፤ሌባ፡በማይቀርብበት፡ብልም፡በማያጠፋበት፡በሰማያት፡የማያልቅ፡ መዝገብ፡የሚኾኑትን፡የማያረጁትንም፡ኰረጆዎች፡ለራሳችኹ፡አድርጉ፤ 34፤መዝገባችኹ፡ባለበት፡ልባችኹ፡ደግሞ፡በዚያ፡ይኾናልና። 35፤ወገባችኹ፡የታጠቀ፡መብራታችኹም፡የበራ፡ይኹን፤ 36፤እናንተም፡ጌታቸው፡መጥቶ፡ደጁን፡ሲያንኳኳ፡ወዲያው፡እንዲከፍቱለት፡ከሰርግ፡እስኪመለስ፡ድረስ፡ የሚጠብቁ፡ሰዎችን፡ምሰሉ፡ 37፤ጌታቸው፡በመጣ፡ጊዜ፡ሲተጉ፡የሚያገኛቸው፡እነዚያ፡ባሪያዎች፡ብፁዓን፡ናቸው፤እውነት፡ እላችዃለኹ፥ታጥቆ፡በማእዱ፡ያስቀምጣቸዋል፡ቀርቦም፡ያገለግላቸዋል። 38፤ከሌሊቱም፡በኹለተኛው፡ወይም፡በሦስተኛው፡ክፍል፡መጥቶ፡እንዲሁ፡ቢያገኛቸው፥እነዚያ፡ባሪያዎች፡ ብፁዓን፡ናቸው። 39፤ይህን፡ግን፡ዕወቁ፡ባለቤት፡በምን፡ሰዓት፡ሌባ፡እንዲመጣ፡ቢያውቅ፡ኖሮ፥በነቃ፥ቤቱም፡እንዲቈፈር፡ ባልፈቀደም፡ነበር። 40፤እናንተ፡ደግሞ፡ተዘጋጅታችኹ፡ኑሩ፥የሰው፡ልጅ፡በማታስቡበት፡ሰዓት፡ይመጣልና። 41፤ጴጥሮስም፦ጌታ፡ሆይ፥ይህን፡ምሳሌ፡ለእኛ፡ወይስ፡ደግሞ፡ለዅሉ፡ትናገራለኽን፧አለው። 42፤ጌታም፡አለ፦እንኪያስ፡ም38፤ከሌሊቱም፡በኹለተኛው፡ወይም፡በሦስተኛው፡ክፍል፡መጥቶ፡እንዲሁ፡ቢያገኛቸው፥እነዚያ፡ባሪያዎች፡ ብፁዓን፡ናቸው። 39፤ይህን፡ግን፡ዕወቁ፡ባለቤት፡በምን፡ሰዓት፡ሌባ፡እንዲመጣ፡ቢያውቅ፡ኖሮ፥በነቃ፥ቤቱም፡እንዲቈፈር፡ ባልፈቀደም፡ነበር። 40፤እናንተ፡ደግሞ፡ተዘጋጅታችኹ፡ኑሩ፥የሰው፡ልጅ፡በማታስቡበት፡ሰዓት፡ይመጣልና። 41፤ጴጥሮስም፦ጌታ፡ሆይ፥ይህን፡ምሳሌ፡ለእኛ፡ወይስ፡ደግሞ፡ለዅሉ፡ትናገራለኽን፧አለው። 42፤ጌታም፡አለ፦እንኪያስ፡ምግባቸውን፡በጊዜው፡ይሰጣቸው፡ዘንድ፡ጌታው፡በቤተ፡ሰዎቹ፡ላይ፡ የሚሾመው፡ታማኝና፡ልባም፡መጋቢ፡ማን፡ነው፧ 43፤ጌታው፡መጥቶ፡እንዲህ፡ሲያደርግ፡የሚያገኘው፡ያ፡ባሪያ፡ብፁዕ፡ነው። 44፤እውነት፡እላችዃለኹ፥ባለው፡ዅሉ፡ላይ፡ይሾመዋል። 45፤ያ፡ባሪያ፡ግን፦ጌታዬ፡እስኪመጣ፡ይዘገያል፡ብሎ፡በልቡ፡ቢያስብ፡ሎሌዎችንና፡ገረዶችንም፡ይመታ፡ ይበላም፡ይጠጣም፡ይሰክርም፡ዘንድ፡ቢዠምር፥ 46፤የዚያ፡ባሪያ፡ጌታ፡ባልጠበቃት፡ቀን፡ባላወቃትም፡ሰዓት፡ይመጣል፥ከኹለትም፡ይሰነጥቀዋል፡ዕድሉንም፡ ከማይታመኑ፡ጋራ፡ያደርጋል። 47፤የጌታውንም፡ፈቃድ፡ዐውቆ፡ያልተዘጋጀ፡እንደ፡ፈቃዱም፡ያላደረገ፡ያ፡ባሪያ፡እጅግ፡ይገረፋል፤ 48፤ያላወቀ፡ግን፥መገረፍ፡የሚገ፟ባ፟ውንም፡ያደረገ፡ጥቂት፡ይገረፋል።ብዙም፡ከተሰጠው፡ሰው፡ዅሉ፡ከርሱ፡ብዙ፡ይፈለግበታል፥ብዙ፡ዐደራም፡ከተሰጠው፡ከርሱ፡አብዝተው፡ይሹበታል። 49፤በምድር፡ላይ፡እሳት፡ልጥል፡መጣኹ፥አኹንም፡የነደደ፡ከኾነ፡ዘንድ፡ምን፡እፈልጋለኹ፧ 50፤ነገር፡ግን፥የምጠመቃት፡ጥምቀት፡አለችኝ፥እስክትፈጸምም፡ድረስ፡እንዴት፡እጨነቃለኹ፧ 51፤በምድር፡ላይ፡ሰላምንም፡ለመስጠት፡የመጣኹ፡ይመስላችዃልን፧እላችዃለኹ፥አይደለም፥መለያየትን፡ እንጂ። 52፤ካኹን፡ዠምሮ፡በአንዲት፡ቤት፡ዐምስት፡ሰዎች፡ይኖራሉና፤ሦስቱም፡በኹለቱ፡ላይ፡ኹለቱም፡በሦስቱ፡ ላይ፡ተነሥተው፡ይለያያሉ። 53፤አባት፡በልጁ፡ላይ፡ልጅም፡በአባቱ፡ላይ፥እናት፡በልጇ፡ላይ፡ልጇም፡በእናቷ፡ላይ፥ዐማት፡በምራቷ፡ ላይ፡ምራትም፡በአማቷ፡ላይ፡ተነሥተው፡ይለያያሉ። 54፤ደግሞም፡ሕዝቡን፡እንዲህ፡አለ፦ደመና፡ከምዕራብ፡ሲወጣ፡ባያችኹ፡ጊዜ፥ወዲያው።ዝናብ፡ይመጣል፡ ትላላችኹ፥እንዲሁም፡ይኾናል፤ 55፤በአዜብም፡ነፋስ፡ሲነፍስ፦ትኵሳት፡ይኾናል፡ትላላችኹ፥ይኾንማል። 56፤እናንት፡ግብዞች፥የምድሩንና፡የሰማዩን፡ፊት፡ልትመረምሩ፡ታውቃላችኹ፥ነገር፡ግን፥ይህን፡ዘመን፡ የማትመረምሩ፡እንዴት፡ነው፧ 57፤ራሳችኹ፡ደግሞ፡ጽድቅን፡የማትፈርዱ፡ስለ፡ምን፡ነው፧ 58፤ከባላጋራኽ፡ጋራ፡ወደ፡ሹም፡ብትኼድ፥ወደ፡ዳኛ፡እንዳይጐትትኽ፡ዳኛውም፡ለሎሌው፡አሳልፎ፡ እንዳይሰጥኽ፡ሎሌውም፡በወህኒ፡እንዳይጥልኽ፥ገና፡በመንገድ፡ሳለኽ፡ከባላጋራኽ፡እንድትታረቅ፡ትጋ። 59፤እልኻለኹ፥የመጨረሻዋን፡ግማሽ፡ሳንቲም፡እስክትከፍል፡ድረስ፡ከዚያ፡ከቶ፡አትወጣም።

ምዕራፍ ፲፫

1፤በዚያን፡ጊዜም፡ሰዎች፡መጥተው፡ጲላጦስ፡ደማቸውን፡ከመሥዋዕታቸው፡ጋራ፡ስላደባለቀው፡ስለገሊላ፡ ሰዎች፡አወሩለት። 2፤ኢየሱስም፡መልሶ፡እንዲህ፡አላቸው፦እነዚህ፡የገሊላ፡ሰዎች፡ይህ፡ስለ፡ደረሰባቸው፥ከገሊላ፡ሰዎች፡ ዅሉ፡ይልቅ፡ኀጢአተኛዎች፡የኾኑ፡ይመስሏችዃልን፧ 3፤እላችዃለኹ፥አይደለም፤ነገር፡ግን፥ንስሓ፡ባትገቡ፡ዅላችኹ፡እንዲሁ፡ትጠፋላችኹ። 4፤ወይስ፡በሰሌሆም፡ግንቡ፡የወደቀባቸውና፡የገደላቸው፡እነዚያ፡ዐሥራ፡ስምንት፡ሰዎች፡በኢየሩሳሌም፡ ከሚኖሩት፡ዅሉ፡ይልቅ፡በደለኛዎች፡ይመስሏችዃልን፧አይደለም፥እላችዃለኹ፤ 5፤ነገር፡ግን፥ንስሓ፡ባትገቡ፡ዅላችኹ፡እንደዚሁ፡ትጠፋላችኹ። 6፤ይህንም፡ምሳሌ፡አለ፦ላንድ፡ሰው፡በወይኑ፡አትክልት፡የተተከለች፡በለስ፡ነበረችው፥ፍሬም፡ሊፈልግባት፡ መጥቶ፡ምንም፡አላገኘም። 7፤የወይን፡አትክልት፡ሠራተኛውንም፦እንሆ፥ከዚች፡በለስ፡ፍሬ፡ልፈልግ፡ሦስት፡ዓመት፡እየመጣኹ፡ ምንም፡አላገኘኹም፤ቍረጣት፤ስለ፡ምን፡ደግሞ፡መሬቱን፡ታጐሳቍላለች፧አለው። 8፤ርሱ፡ግን፡መልሶ፦ጌታ፡ሆይ፥ዙሪያዋን፡እስክኰተኵትላትና፡ፋንድያ፡እስካፈስላት፡ድረስ፡በዚች፡ዓመት፡ ደግሞ፡ተዋት። 9፤ወደ፡ፊትም፡ብታፈራ፥ደኅና፡ነው፤ያለዚያ፡ግን፡ትቈርጣታለኽ፡አለው። 10፤በሰንበትም፡ባንድ፡ምኵራብ፡ያስተምር፡ነበር። 11፤እንሆም፥ከዐሥራ፡ስምንት፡ዓመት፡ዠምሮ፡የድካም፡መንፈስ፡ያደረባት፡ሴት፡ነበረች፥ርሷም፡ጐባጣ፡ ነበረች፥ቀንታም፡ልትቆም፡ከቶ፡አልተቻላትም። 12፤ኢየሱስም፡ባያት፡ጊዜ፡ጠራትና፦አንቺ፡ሴት፥ከድካምሽ፡ተፈተ፟ሻል፡አላት፥እጁንም፡ጫነባት፤ 13፤ያን፡ጊዜም፡ቀጥ፡አለች፥እግዚአብሔርንም፡አመሰገነች። 14፤የምኵራብ፡አለቃ፡ግን፡ኢየሱስ፡በሰንበት፡ስለ፡ፈወሰ፡ተቈጥቶ፡መለሰና፡ሕዝቡን፦ሊሠራባቸው፡ የሚገ፟ባ፟፡ስድስት፡ቀኖች፡አሉ፤እንግዲህ፡በእነርሱ፡መጥታችኹ፡ተፈወሱ፡እንጂ፡በሰንበት፡አይደለም፡አለ። 15፤ጌታም፡መልሶ፦እናንተ፡ግብዞች፥ከእናንተ፡እያንዳንዱ፡በሰንበት፡በሬውን፡ወይስ፡አህያውን፡ከግርግሙ፡ ፈቶ፟፡ውሃ፡ሊያጠጣው፡ይወስደው፡የለምን፧ 16፤ይህችም፡የአብርሃም፡ልጅ፡ኾና፡ከዐሥራ፡ስምንት፡ዓመት፡ዠምሮ፡ሰይጣን፡ያሰራት፡በሰንበት፡ቀን፡ ከዚህ፡እስራት፡ልትፈታ፡አይገ፟ባ፟ምን፧አለው። 17፤ይህንም፡ሲናገር፡ሳለ፡የተቃወሙት፡ዅሉ፡ዐፈሩ፤ከርሱም፡በተደረገው፡ድንቅ፡ዅሉ፡ሕዝቡ፡ዅሉ፡ደስ፡ አላቸው። 18፤ርሱም፦የእግዚአብሔር፡መንግሥት፡ምን፡ትመስላለች፥በምንስ፡አስመስላታለኹ፧ 19፤ሰው፡ወስዶ፡በአትክልቱ፡የጣላትን፡የሰናፍጭ፡ቅንጣት፡ትመስላለች፤አደገችም፡ታላቅ፡ዛፍም፡ ኾነች፥የሰማይ፡ወፎችም፡በቅርንጫፎቿ፡ሰፈሩ፡አለ። 20፤ደግሞም፥የእግዚአብሔርን፡መንግሥት፡በምን፡አስመስላታለኹ፧ 21፤ሴት፡ወስዳ፡ዅሉ፡እስኪቦካ፡ድረስ፡በሦስት፡መስፈሪያ፡ዱቄት፡የሸሸገችውን፡ርሾ፡ትመስላለች፡አለ። 22፤ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ሲኼድ፡ከተማዎችንና፡መንደሮችን፡እያስተማረ፡ያልፍ፡ነበር። 23፤አንድ፡ሰውም፦ጌታ፡ሆይ፥የሚድኑ፡ጥቂቶች፡ናቸውን፧አለው።ርሱም፡እንዲህ፡አላቸው፦ 24፤በጠበበው፡በር፡ለመግባት፡ተጋደሉ፤እላችዃለኹና፥ብዙዎች፡ሊገቡ፡ይፈልጋሉ፡አይችሉምም። 25፤ባለቤቱ፡ተነሥቶ፡በሩን፡ከቈለፈ፡በዃላ፥እናንተ፡በውጭ፡ቆማችኹ፦ጌታ፡ሆይ፥ጌታ፡ሆይ፥ክፈትልን፡ እያላችኹ፡በሩን፡ልታንኳኩ፡ትዠምራላችኹ፡ርሱም፡መልሶ፦ከወዴት፡እንደ፡ኾናችኹ፡አላውቃችኹም፡ ይላችዃል። 26፤በዚያን፡ጊዜም፦በፊትኽ፡በላን፡ጠጣንም፡በአደባባያችንም፡አስተማርኽ፡ልትሉ፡ትዠምራላችኹ፤ 27፤ርሱም፦እላችዃለኹ፥ከወዴት፡እንደ፡ኾናችኹ፡አላውቃችኹም፤ዅላችኹ፡ዐመፀኛዎች፥ከእኔ፡ራቁ፡ ይላችዃል። 28፤አብርሃምንና፡ይሥሐቅን፡ያዕቆብንም፡ነቢያትንም፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡መንግሥት፡ባያችኹ፡ ጊዜ፥እናንተ፡ግን፡ወደ፡ውጭ፡ተጥላችኹ፡ስትቀሩ፥በዚያ፡ልቅሶና፡ጥርስ፡ማፋጨት፡ይኾናል። 29፤ከምሥራቅና፡ከምዕራብም፡ከሰሜንና፡ከደቡብም፡ይመጣሉ፥በእግዚአብሔርም፡መንግሥት፡በማእዱ፡ ይቀመጣሉ። 30፤እንሆም፥ከዃለኛዎች፡ፊተኛዎች፡የሚኾኑ፡አሉ፥ከፊተኛዎችም፡ዃለኛዎች፡የሚኾኑ፡አሉ። 31፤በዚያን፡ሰዓት፡ከፈሪሳውያን፡አንዳንዱ፡ቀርበው፦ሄሮድስ፡ሊገድልኽ፡ይወዳልና፥ከዚህ፡ውጣና፡ኺድ፡ አሉት። 32፤እንዲህም፡አላቸው፦ኼዳችኹ፡ለዚያች፡ቀበሮ፦እንሆ፥ዛሬና፡ነገ፡አጋንንትን፡አወጣለኹ፡ በሽተኛዎችንም፡እፈውሳለኹ፥በሦስተኛውም፡ቀን፡እፈጸማለኹ፡በሏት። 33፤ዳሩ፡ግን፡ነቢይ፡ከኢየሩሳሌም፡ውጭ፡ይጠፋ፡ዘንድ፡አይገ፟ባ፟ውምና፥ዛሬና፡ነገ፣ከነገ፡በስቲያም፡ልኼድ፡ ያስፈልገኛል። 34፤ኢየሩሳሌም፥ኢየሩሳሌም፥ነቢያትን፡የምትገድል፡ወደ፡ርሷ፡የተላኩትንም፡የምትወግር፥ዶሮ፡ጫጩቶቿን፡ በክንፎቿ፡በታች፡እንደምትሰበስብ፡ልጆችሽን፡እሰበስብ፡ዘንድ፡ስንት፡ጊዜ፡ወደድኹ፥እናንተም፡ አልወደዳችኹም። 35፤እንሆ፥ቤታችኹ፡የተፈታ፡ኾኖ፡ይቀርላችዃል።እላችዃለኹም፦በጌታ፡ስም፡የሚመጣ፡የተባረከ፡ነው፡ እስክትሉ፡ድረስ፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አታዩኝም።

ምዕራፍ ፲፬

1፤በሰንበትም፡ከፈሪሳውያን፡አለቃዎች፡ወደ፡አንዱ፡ቤት፡እንጀራ፡ሊበላ፡በገባ፡ጊዜ፡እነርሱ፡ይጠባበቁት፡ ነበር። 2፤እንሆም፥ሆዱ፡የተነፋ፡ሰው፡በፊቱ፡ነበረ። 3፤ኢየሱስም፡መልሶ፦በሰንበት፡መፈወስ፡ተፈቅዷልን፡ወይስ፡አልተፈቀደም፧ብሎ፡ለሕግ፡ዐዋቂዎችና፡ ለፈሪሳውያን፡ተናገረ። 4፤እነርሱ፡ግን፡ዝም፡አሉ።ይዞም፡ፈወሰውና፡አሰናበተው። 5፤ከእናንተ፡አህያው፡ወይስ፡በሬው፡በጕድጓድ፡ቢወድቅ፡በሰንበት፡ወዲያው፡የማያወጣው፡ማን፡ ነው፧አላቸው። 6፤ስለዚህ፡ነገርም፡ሊመልሱለት፡አልተቻላቸውም። 7፤የታደሙትንም፡የከበሬታ፡ስፍራ፡እንደ፡መረጡ፡ተመልክቶ፡ምሳሌ፡ነገራቸው፡እንዲህ፡ሲል፦ 8፤ማንም፡ለሰርግ፡ቢጠራኽ፡በከበሬታ፡ስፍራ፡አትቀመጥ፤ምናልባት፡ከአንተ፡ይልቅ፡የከበረ፡ተጠርቶ፡ ይኾናልና፥አንተን፡ርሱንም፡የጠራ፡መጥቶ፦ 9፤ለዚህ፡ስፍራ፡ተውለት፡ይልኻል፥በዚያን፡ጊዜም፡እያፈርኽ፡በዝቅተኛው፡ስፍራ፡ልትኾን፡ትዠምራለኽ። 10፤ነገር፡ግን፥በተጠራኽ፡ጊዜ፥የጠራኽ፡መጥቶ፦ወዳጄ፡ሆይ፥ወደ፡ላይ፡ውጣ፡እንዲልኽ፥ኼደኽ፡ በዝቅተኛው፡ስፍራ፡ተቀመጥ፤ያን፡ጊዜም፡ከአንተ፡ጋራ፡በተቀመጡት፡ዅሉ፡ፊት፡ክብር፡ይኾንልኻል። 11፤ራሱን፡ከፍ፡የሚያደርግ፡ዅሉ፡ይዋረዳልና፥ራሱንም፡የሚያዋርድ፡ከፍ፡ይላል። 12፤የጠራውንም፡ደግሞ፡እንዲህ፡አለው፦ምሳ፡ወይም፡እራት፡ባደረግኽ፡ጊዜ፥እነርሱ፡ደግሞ፡በተራቸው፡ ምናልባት፡እንዳይጠሩኽ፡ብድራትም፡እንዳይመልሱልኽ፥ወዳጆችኽንና፡ወንድሞችኽን፡ዘመዶችኽንም፡ ባለጠጋዎች፡ጎረቤቶችኽንም፡አትጥራ። 13፤ነገር፡ግን፥ግብዣ፡ባደረግኽ፡ጊዜ፡ድኻዎችንና፡ጕንድሾችን፡ዐንካሳዎችንም፡ዕውሮችንም፡ጥራ፤ 14፤የሚመልሱት፡ብድራት፡የላቸውምና፡ብፁዕ፡ትኾናለኽ፤በጻድቃን፡ትንሣኤ፡ይመለስልኻልና። 15፤ከተቀመጡትም፡አንዱ፡ይህን፡ሰምቶ፦በእግዚአብሔር፡መንግሥት፡እንጀራ፡የሚበላ፡ብፁዕ፡ነው፡ አለው። 16፤ርሱ፡ግን፡እንዲህ፡አለው፦አንድ፡ሰው፡ታላቅ፡እራት፡አድርጎ፡ብዙዎችን፡ጠራ፤ 17፤በእራትም፡ሰዓት፡የታደሙትን፦አኹን፡ተዘጋጅቷልና፥ኑ፡እንዲላቸው፡ባሪያውን፡ላከ። 18፤ዅላቸውም፡በአንድነት፡ያመካኙ፡ዠመር።የፊተኛው፦መሬት፡ገዝቻለኹ፡ወጥቼም፡ላየው፡በግድ፡ ያስፈልገኛል፤ይቅር፡እንድትለኝ፡እለምንኻለኹ፡አለው። 19፤ሌላውም፦ዐምስት፡ጥምድ፡በሬዎች፡ገዝቻለኹ፡ልፈትናቸውም፡እኼዳለኹ፤ይቅር፡እንድትለኝ፡ እለምንኻለኹ፡አለው። 20፤ሌላውም፦ሚስት፡አግብቻለኹ፡ስለዚህም፡ልመጣ፡አልችልም፡አለው። 21፤ባሪያውም፡ደርሶ፡ይህን፡ለጌታው፡ነገረው።በዚያን፡ጊዜ፡ባለቤቱ፡ተቈጥቶ፡ባሪያውን፦ወደከተማ፡ ጐዳናና፡ወደ፡ስላች፡ፈጥነኽ፡ውጣ፡ድኻዎችንና፡ጕንድሾችን፡ዐንካሳዎችንና፡ዕውሮችንም፡ወደዚህ፡አግባ፡ አለው። 22፤ባሪያውም፦ጌታ፡ሆይ፥እንዳዘዝኸኝ፡ተደርጓል፥ገናም፡ስፍራ፡አለ፡አለው። 23፤ጌታውም፡ባሪያውን፦ቤቴ፡እንዲሞላ፡ወደ፡መንገድና፡ወደ፡ቅጥር፡ውጣና፡ይገቡ፡ዘንድ፡ግድ፡ በላቸው፤ 24፤እላችዃለኹና፥ከታደሙት፡ከነዚያ፡ሰዎች፡አንድ፡ስንኳ፡እራቴን፡አይቀምስም፡አለው። 25፤ብዙም፡ሕዝብ፡ከርሱ፡ጋራ፡ይኼዱ፡ነበር፥ዘወር፡ብሎም፡እንዲህ፡አላቸው፦ 26፤ማንም፡ወደ፡እኔ፡የሚመጣ፡ቢኖር፡አባቱንና፡እናቱን፡ሚስቱንም፡ልጆቹንም፡ወንድሞቹንም፡እኅቶቹንም፡ የራሱን፡ሕይወት፡ስንኳ፡ሳይቀር፡ባይጠላ፥ደቀ፡መዝሙሬ፡ሊኾን፡አይችልም። 27፤ማንም፡መስቀሉን፡ተሸክሞ፡በዃላዬ፡የማይመጣ፥ደቀ፡መዝሙሬ፡ሊኾን፡አይችልም። 28፤ከእናንተ፡ግንብ፡ሊሠራ፡የሚወድ፡ለመደምደሚያ፡የሚበቃ፡ያለው፡እንደ፡ኾነ፡አስቀድሞ፡ተቀምጦ፡ ከሳራውን፡የማይቈጥር፡ማን፡ነው፧ 29፤ያለዚያ፡መሠረቱን፡ቢመሠርት፥ሊደመድመውም፡ቢያቅተው፥ያዩት፡ዅሉ፦ 30፤ይህ፡ሰው፡ሊሠራ፡ዠምሮ፡ሊደመድመው፡አቃተው፡ብለው፡ሊዘብቱበት፡ይዠምራሉ። 31፤ወይም፡ሌላውን፡ንጉሥ፡በጦርነት፡ሊጋጠም፡የሚኼድ፥ከኹለት፡እልፍ፡ጋራ፡የሚመጣበትን፡ባንድ፡ እልፍ፡ሊገናኝ፡የሚችል፡እንደ፡ኾነ፡አስቀድሞ፡ተቀምጦ፡የማያስብ፡ንጉሥ፡ማን፡ነው፧ 32፤ባይኾንስ፡ሌላው፡ገና፡ሩቅ፡ሳለ፡መልክተኛዎች፡ልኮ፡ዕርቅ፡ይለምናል። 33፤እንግዲህ፡እንደዚሁ፡ማንም፡ከእናንተ፡ያለውን፡ዅሉ፡የማይተው፡ደቀ፡መዝሙሬ፡ሊኾን፡አይችልም። 34፤ጨው፡መልካም፡ነው፤ጨው፡ዐልጫ፡ቢኾን፡ግን፡በምን፡ይጣፈጣል፧ 35፤ለምድር፡ቢኾን፡ለፍግ፡መቈለያም፡ቢኾን፡አይረባም፤ወደ፡ውጭ፡ይጥሉታል።የሚሰማ፡ዦሮ፡ያለው፡ ይስማ።

ምዕራፍ ፲፭

የሉቃስ ወንጌል Luke 15 ምዕራፍ፡15፤ 1፤ቀራጮችና፡ኀጢአተኛዎችም፡ዅሉ፡ሊሰሙት፡ወደ፡ርሱ፡ይቀርቡ፡ነበር። 2፤ፈሪሳውያንና፡ጻፊዎችም፦ይህስ፡ኀጢአተኛዎችን፡ይቀበላል፡ከነርሱም፡ጋራ፡ይበላል፡ብለው፡ርስ፡ በርሳቸው፡አንጐራጐሩ። 3፤ይህንም፡ምሳሌ፡ነገራቸው፡እንዲህ፡ሲል፦ 4፤መቶ፡በግ፡ያለው፡ከነርሱም፡አንዱ፡ቢጠፋ፥ዘጠና፡ዘጠኙን፡በበረሓ፡ትቶ፡የጠፋውን፡እስኪያገኘው፡ ድረስ፡ሊፈልገው፡የማይኼድ፡ከእናንተ፡ማን፡ነው፧ 5፤ባገኘውም፡ጊዜ፡ደስ፡ብሎት፡በጫንቃው፡ይሸከመዋል፤ 6፤ወደ፡ቤትም፡በመጣ፡ጊዜ፡ወዳጆቹንና፡ጎረቤቶቹን፡በአንድነት፡ጠርቶ፦የጠፋውን፡በጌን፡አግኝቼዋለኹና፡ ከእኔ፡ጋራ፡ደስ፡ይበላችኹ፡ይላቸዋል። 7፤እላችዃለኹ፥እንዲሁ፡ንስሓ፡ከማያስፈልጋቸው፡ከዘጠና፡ዘጠኝ፡ጻድቃን፡ይልቅ፡ንስሓ፡በሚገባ፡ባንድ፡ ኀጢአተኛ፡በሰማይ፡ደስታ፡ይኾናል። 8፤ወይም፡ዐሥር፡ድሪም281፡ያላት፡አንድ፡ድሪም፡ቢጠፋባት፥መብራት፡አብርታ፡ቤቷንም፡ጠርጋ፡ እስክታገኘው፡ድረስ፡አጥብቃ፡የማትፈልግ፡ሴት፡ማን፡ናት፧ 9፤ባገኘችውም፡ጊዜ፡ወዳጆቿንና፡ጎረቤቶቿን፡በአንድነት፡ጠርታ፦የጠፋውን፡ድሪሜን፡አግኝቼዋለኹና፡ ከእኔ፡ጋራ፡ደስ፡ይበላችኹ፡ትላቸዋለች። 10፤እላችዃለኹ፥እንዲሁ፡ንስሓ፡በሚገባ፡ባንድ፡ኀጢአተኛ፡በእግዚአብሔር፡መላእክት፡ፊት፡ደስታ፡ ይኾናል። 11፤እንዲህም፡አለ፦አንድ፡ሰው፡ኹለት፡ልጆች፡ነበሩት። 12፤ከነርሱም፡ታናሹ፡አባቱን፦አባቴ፡ሆይ፥ከገንዘብኽ፡የሚደርሰኝን፡ክፍል፡ስጠኝ፡አለው።ገንዘቡንም፡ አካፈላቸው። 13፤ከጥቂት፡ቀንም፡በዃላ፡ታናሹ፡ልጅ፡ገንዘቡን፡ዅሉ፡ሰብስቦ፡ወደ፡ሩቅ፡አገር፡ኼደ፥ከዚያም፡እያባከነ፡ ገንዘቡን፡በተነ። 14፤ዅሉንም፡ከከሰረ፡በዃላ፡በዚያች፡አገር፡ጽኑ፡ራብ፡ኾነ፥ርሱም፡ይጨነቅ፡ዠመር። 15፤ኼዶም፡ከዚያች፡አገር፡ሰዎች፡ከአንዱ፡ጋራ፡ተዳበለ፥ርሱም፡ዕሪያ፡ሊያሰማራ፡ወደ፡ሜዳ፡ሰደደው። 16፤ዕሪያዎችም፡ከሚበሉት፡ዐሠር፡ሊጠግብ፡ይመኝ፡ነበር፥የሚሰጠውም፡አልነበረም። 17፤ወደ፡ልቡም፡ተመልሶ፡እንዲህ፡አለ፦እንጀራ፡የሚተርፋቸው፡የአባቴ፡ሞያተኛዎች፡ስንት፡ናቸው፧እኔ፡ ግን፡ከዚህ፡በራብ፡እጠፋለኹ። 18፤ተነሥቼም፡ወደ፡አባቴ፡እኼዳለኹና፦አባቴ፡ሆይ፥በሰማይና፡በፊትኽ፡በደልኹ፥ 19፤ወደ፡ፊትም፡ልጅኽ፡ልባል፡አይገ፟ባ፟ኝም፤ከሞያተኛዎችኽ፡እንደ፡አንዱ፡አድርገኝ፡እለዋለኹ። 20፤ተነሥቶም፡ወደ፡አባቱ፡መጣ።ርሱም፡ገና፡ሩቅ፡ሳለ፡አባቱ፡አየውና፡ዐዘነለት፥ሮጦም፡ዐንገቱን፡ ዐቀፈውና፡ሳመው። 21፤ልጁም፦አባቴ፡ሆይ፥በሰማይና፡በፊትኽ፡በደልኹ፥ወደ፡ፊትም፡ልጅኽ፡ልባል፡አይገ፟ባ፟ኝም፡አለው። 22፤አባቱ፡ግን፡ባሪያዎቹን፡አለ፦ፈጥናችኹ፡ከዅሉ፡የተሻለ፡ልብስ፡አምጡና፡አልብሱት፥ለእጁ፡ቀለበት፡ ለእግሩም፡ጫማ፡ስጡ፤ 23፤የሰባውን፡ፊሪዳ፡አምጥታችኹ፡ዕረዱት፥እንብላም፡ደስም፡ይበለን፤ 24፤ይህ፡ልጄ፡ሞቶ፡ነበርና፥ደግሞም፡ሕያው፡ኾኗል፤ጠፍቶም፡ነበር፡ተገኝቷልም።ደስም፡ይላቸው፡ ዠመር። 25፤ታላቁ፡ልጁ፡በዕርሻ፡ነበረ፤መጥቶም፡ወደ፡ቤት፡በቀረበ፡ጊዜ፡የመሰንቆና፡የዘፈን፡ድምፅ፡ሰማ፤ 26፤ከብላቴናዎችም፡አንዱን፡ጠርቶ፦ይህ፡ምንድር፡ነው፧ብሎ፡ጠየቀ። 27፤ርሱም፦ወንድምኽ፡መጥቷልና፥በደኅና፡ስላገኘው፥አባትኽ፡የሰባውን፡ፊሪዳ፡ዐረደለት፡አለው። 28፤ተቈጣም፡ሊገባም፡አልወደደም፤አባቱም፡ወጥቶ፡ለመነው። 29፤ርሱ፡ግን፡መልሶ፡አባቱን፦እንሆ፥ይህን፡ያኽል፡ዓመት፡እንደ፡ባሪያ፡ተገዝቼልኻለኹ፡ከትእዛዝኽም፡ ከቶ፡አልተላለፍኹም፤ለኔም፡ከወዳጆቼ፡ጋራ፡ደስ፡እንዲለኝ፡አንድ፡ጥቦት፡ስንኳ፡አልሰጠኸኝም፤ 30፤ነገር፡ግን፥ገንዘብኽን፡ከጋለሞታዎች፡ጋራ፡በልቶ፡ይህ፡ልጅኽ፡በመጣ፡ጊዜ፥የሰባውን፡ፊሪዳ፡ ዐረድኽለት፡አለው። 31፤ርሱ፡ግን፦ልጄ፡ሆይ፥አንተ፡ዅልጊዜ፡ከእኔ፡ጋራ፡ነኽ፥ለኔም፡የኾነ፡ዅሉ፡የአንተ፡ነው፤ 32፤ዳሩ፡ግን፡ይህ፡ወንድምኽ፡ሞቶ፡ነበረ፡ሕያው፡ስለ፡ኾነ፡ጠፍቶም፡ነበር፡ስለ፡ተገኘ፡ደስ፡እንዲለን፡ ፍሥሓም፡እንድናደርግ፡ይገ፟ባ፟ናል፡አለው። 281 ጽር.፥ድራኽሚ፡(የፋርስ፡ገንዘብ፡ስም፥የወቄት፡ወርቅ፡1/16 ኛ፤2፡ቀመት፡1፡ድሪም፡ይኾናል)።

ምዕራፍ ፲፮

1፤ደግሞም፡ለደቀ፡መዛሙርቱ፡እንዲህ፡አለ፦መጋቢ፡የነበረው፡አንድ፡ባለጠጋ፡ሰው፡ነበረ፥በርሱ፡ ዘንድ፦ይህ፡ሰው፡ያለኽን፡ይበትናል፡ብለው፡ከሰሱት። 2፤ጠርቶም፦ይህ፡የምሰማብኽ፡ምንድር፡ነው፧ወደ፡ፊት፡ለእኔ፡መጋቢ፡ልትኾን፡አትችልምና፡ የመጋቢነትኽን፡ሒሳብ፡አስረክበኝ፡አለው። 3፤መጋቢውም፡በልቡ፦ጌታዬ፡መጋቢነቱን፡ከእኔ፡ይወስዳልና፥ምን፡ላድርግ፧ለመቈፈር፡ኀይል፡ የለኝም፥መለመንም፡ዐፍራለኹ። 4፤ከመጋቢነቱ፡ብሻር፡በቤታቸው፡እንዲቀበሉኝ፡የማደርገውን፡ዐውቃለኹ፡አለ። 5፤የጌታውንም፡ባለዕዳዎች፡እያንዳንዳቸውን፡ጠርቶ፡የፊተኛውን፦ለጌታዬ፡ምን፡ያኽል፡ዕዳ፡ አለብኽ፧አለው። 6፤ርሱም፦መቶ፡ማድጋ፡ዘይት፡አለ።ደብዳቤኽን፡እንካ፡ፈጥነኽም፡ተቀምጠኽ፡ዐምሳ፡ብለኽ፡ጻፍ፡ አለው። 7፤በዃላም፡ሌላውን፦አንተስ፡ስንት፡ዕዳ፡አለብኽ፧አለው።ርሱም፦መቶ፡ጫን፡ስንዴ፡አለ።ደብዳቤኽን፡ እንካ፡ሰማንያ፡ብለኽም፡ጻፍ፡አለው። 8፤ጌታውም፡ዐመፀኛውን፡መጋቢ፡በልባምነት፡ስላደረገ፡አመሰገነው፡የዚህ፡ዓለም፡ልጆች፡ለትውልዳቸው፡ ከብርሃን፡ልጆች፡ይልቅ፡ልባሞች፡ናቸውና። 9፤እኔም፡እላችዃለኹ፥የዐመፃ፡ገንዘብ፡ሲያልቅ፡በዘለዓለም፡ቤቶች፡እንዲቀበሏችኹ፥በርሱ፡ወዳጆችን፡ ለራሳችኹ፡አድርጉ። 10፤ከዅሉ፡በሚያንስ፡የታመነ፡በብዙ፡ደግሞ፡የታመነ፡ነው፥ከዅሉ፡በሚያንስም፡የሚያምፅ፡በብዙ፡ደግሞ፡ ዐመፀኛ፡ነው። 11፤እንግዲያስ፡በዐመፃ፡ገንዘብ፡ካልታመናችኹ፥እውነተኛውን፡ገንዘብ፡ማን፡ዐደራ፡ይሰጣችዃል፧ 12፤በሌላ፡ሰው፡ገንዘብ፡ካልታመናችኹ፥የእናንተን፡ማን፡ይሰጣችዃል፧ 13፤ለኹለት፡ጌታዎች፡መገዛት፡የሚቻለው፡ባሪያ፡ማንም፡የለም፤ወይም፡አንዱን፡ይጠላልና፥ኹለተኛውንም፡ ይወዳል፥ወይም፡ወደ፡አንዱ፡ይጠጋል፡ኹለተኛውንም፡ይንቃል።ለእግዚአብሔርና፡ለገንዘብ፡መገዛት፡ አትችሉም። 14፤ገንዘብንም፡የሚወዱ፡ፈሪሳውያን፡ይህን፡ዅሉ፡ሰምተው፡ያፌዙበት፡ነበር። 15፤እንዲህም፡አላቸው፦ራሳችኹን፡በሰው፡ፊት፡የምታጸድቁ፡እናንተ፡ናችኹ፥ነገር፡ግን፥እግዚአብሔር፡ ልባችኹን፡ያውቃል፤በሰው፡ዘንድ፡የከበረ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ርኵሰት፡ነውና። 16፤ሕግና፡ነቢያት፡እስከ፡ዮሐንስ፡ነበሩ፤ከዚያ፡ዠምሮ፡የእግዚአብሔር፡መንግሥት፡ይሰበካል፤ዅሉም፡ወደ፡ ርሷ፡በኀይል፡ይገቡባታል። 17፤ነገር፡ግን፥ከሕግ፡አንዲት፡ነጥብ፡ከምትወድቅ፡ሰማይና፡ምድር፡ሊያልፍ፡ይቀላል። 18፤ሚስቱንም፡የሚፈታ፡ዅሉ፡ሌላዪቱንም፡የሚያገባ፡ያመነዝራል፥ከባሏም፡የተፈታችውን፡የሚያገባ፡ ያመነዝራል። 19፤ቀይ፡ልብስና፡ቀጭን፡የተልባ፡እግር፡የለበሰ፡አንድ፡ባለጠጋ፡ሰው፡ነበረ፥ዕለት፡ዕለትም፡እየተመቸው፡በደስታ፡ይኖር፡ነበር። 20፤አልዓዛርም፡የሚባል፡አንድ፡ድኻ፡በቍስል፡ተወርሶ፡በደጁ፡ተኝቶ፡ነበር፥ 21፤ከባለጠጋውም፡ማእድ፡ከሚወድቀው፡ፍርፋሪ፡ሊጠግብ፡ይመኝ፡ነበር፤ውሻዎች፡እንኳ፡መጥተው፡ ቍስሎቹን፡ይልሱ፡ነበር። 22፤ድኻውም፡ሞተ፥መላእክትም፡ወደአብርሃም፡ዕቅፍ፡ወሰዱት፤ባለጠጋው፡ደግሞ፡ሞተና፡ተቀበረ። 23፤በሲኦልም፡በሥቃይ፡ሳለ፡አሻቅቦ፡አብርሃምን፡በሩቅ፡አየ፡አልዓዛርንም፡በዕቅፉ። 24፤ርሱም፡እየጮኸ፦አብርሃም፡አባት፡ሆይ፥ማረኝ፥በዚህ፡ነበልባል፡እሣቀያለኹና፡የጣቱን፡ጫፍ፡በውሃ፡ ነክሮ፡ምላሴን፡እንዲያበርድልኝ፡አልዓዛርን፡ስደድልኝ፡አለ። 25፤አብርሃም፡ግን፦ልጄ፡ሆይ፥አንተ፡በሕይወትኽ፡ሳለኽ፡መልካም፡እንደ፡ተቀበልኽ፡ዐስብ፡አልዓዛርም፡ እንዲሁ፡ክፉ፤አኹን፡ግን፡ርሱ፡በዚህ፡ይጽናናል፡አንተም፡ትሣቀያለኽ። 26፤ከዚህም፡ዅሉ፡ጋራ፡ከዚህ፡ወደ፡እናንተ፡ሊያልፉ፡የሚፈልጉ፡እንዳይችሉ፥ወዲያ፡ያሉ፡ደግሞ፡ወደ፡ እኛ፡እንዳይሻገሩ፡በእኛና፡በእናንተ፡መካከል፡ታላቅ፡ገደል፡ተደርጓል፡አለ። 27፤ርሱም፦እንኪያስ፥አባት፡ሆይ፥ወዳባቴ፡ቤት፡እንድትሰደው፡እለምንኻለኹ፤ዐምስት፡ወንድሞች፡ አሉኝና፤ 28፤እነርሱ፡ደግሞ፡ወደዚህ፡ሥቃይ፡ስፍራ፡እንዳይመጡ፡ይመስክርላቸው፡አለ። 29፤አብርሃም፡ግን፦ሙሴና፡ነቢያት፡አሏቸው፤እነርሱን፡ይስሙ፡አለው። 30፤ርሱም፦አይደለም፥አብርሃም፡አባት፡ሆይ፥ነገር፡ግን፥ከሙታን፡አንዱ፡ቢኼድላቸው፡ንስሓ፡ይገባሉ፡ አለ። 31፤ሙሴንና፡ነቢያትንም፡የማይሰሙ፡ከኾነ፥ከሙታንም፡እንኳ፡አንድ፡ቢነሣ፡አያምኑም፡አለው።

ምዕራፍ ፲፯

1፤ለደቀ፡መዛሙርቱም፡እንዲህ፡አለ፦መሰናክል፡ግድ፡ሳይመጣ፡አይቀርም፥ነገር፡ግን፥መሰናክሉን፡ ለሚያመጣው፡ወዮለት፤ 2፤ከነዚህ፡ከታናናሾች፡አንዱን፡ከማሰናከል፡ይልቅ፡የወፍጮ፡ድንጋይ፡በዐንገቱ፡ታስሮ፡ወደ፡ባሕር፡ቢጣል፡ ይጠቅመው፡ነበር። 3፤ለራሳችኹ፡ተጠንቀቁ።ወንድምኽ፡ቢበድልኽ፡ገሥጸው፥ቢጸጸትም፡ይቅር፡በለው። 4፤በቀንም፡ሰባት፡ጊዜ፡እንኳ፡ቢበድልኽ፡በቀንም፡ሰባት፡ጊዜ፦ተጸጸትኹ፡እያለ፡ወዳንተ፡ቢመለስ፥ይቅር፡ በለው። 5፤ሐዋርያትም፡ጌታን፦እምነት፡ጨምርልን፡አሉት። 6፤ጌታም፡አለ፦የሰናፍጭ፡ቅንጣት፡የሚያኽል፡እምነት፡ቢኖራችኹ፥ይህን፡ሾላ፦ተነቅለኽ፡ወደ፡ባሕር፡ ተተከል፡ብትሉት፥ይታዘዝላችኹ፡ነበር። 7፤ከእናንተም፡የሚያርስ፡ወይም፡ከብትን፡የሚጠብቅ፡ባሪያ፡ያለው፥ከዕርሻ፡ሲመለስ፦ወዲያው፡ቅረብና፡ በማእዱ፡ተቀመጥ፡የሚለው፡ማን፡ነው፧ 8፤የምበላውን፡እራቴን፡አሰናዳልኝ፥እስክበላና፡እስክጠጣ፡ድረስ፡ታጥቀኽ፡አገልግለኝ፥በዃላም፡አንተ፡ ብላና፡ጠጣ፡የሚለው፡አይደለምን፧ 9፤ያንን፡ባሪያ፡ያዘዘውን፡ስላደረገ፡ያመሰግነዋልን፧ 10፤እንዲሁ፡እናንተ፡ደግሞ፡የታዘዛችኹትን፡ዅሉ፡ባደረጋችኹ፡ጊዜ፦የማንጠቅም፡ባሪያዎች፡ ነን፥ልናደርገው፡የሚገ፟ባ፟ንን፡አድርገናል፡በሉ። 11፤ወደ፡ኢየሩሳሌምም፡ሲኼድ፡በገሊላና፡በሰማርያ፡መካከል፡ዐለፈ። 12፤ወደ፡አንዲት፡መንደርም፡ሲገባ፡በሩቅ፡የቆሙት፡ዐሥር፡ለምጻሞች፡ተገናኙት፤ 13፤እነርሱም፡እየጮኹ፦ኢየሱስ፡ሆይ፥አቤቱ፥ማረን፡አሉ። 14፤አይቶም፦ኺዱ፥ራሳችኹን፡ለካህናት፡አሳዩ፡አላቸው። 15፤እንሆም፥ሲኼዱ፡ነጹ።ከነርሱም፡አንዱ፡እንደ፡ተፈወሰ፡ባየ፡ጊዜ፡በታላቅ፡ድምፅ፡እግዚአብሔርን፡ እያከበረ፡ተመለሰ፥ 16፤እያመሰገነውም፡በእግሩ፡ፊት፡በግንባሩ፡ወደቀ፤ርሱም፡ሳምራዊ፡ነበረ። 17፤ኢየሱስም፡መልሶ፦ዐሥሩ፡አልነጹምን፧ዘጠኙስ፡ወዴት፡አሉ፧ 18፤ከዚህ፡ከልዩ፡ወገን፡በቀር፡እግዚአብሔርን፡ሊያከብሩ፡የተመለሱ፡አልተገኙም፡አለ። 19፤ርሱንም፦ተነሣና፡ኺድ፤እምነትኽ፡አድኖኻል፡አለው። 20፤ፈሪሳውያንም፦የእግዚአብሔር፡መንግሥት፡መቼ፡ትመጣለች፡ብለው፡ ቢጠይቁት፥መልሶ፦የእግዚአብሔር፡መንግሥት፡በመጠባበቅ፡አትመጣም፤ 21፤ደግሞም፦እንዃት፡በዚህ፡ወይም፦እንዃት፡በዚያ፡አይሏትም።እንሆ፥የእግዚአብሔር፡መንግሥት፡ በመካከላችኹ፡ናትና፥አላቸው። 22፤ለደቀ፡መዛሙርቱም፡እንዲህ፡አለ፦ከሰው፡ልጅ፡ቀኖች፡አንዱን፡ልታዩ፡የምትመኙበት፡ወራት፡ ይመጣል፡አታዩትምም። 23፤እነርሱም፦እንሆ፥በዚህ፥ወይም፦እንሆ፥በዚያ፡ይሏችዃል፤አትኺዱ፡አትከተሏቸውም። 24፤መብረቅ፡በርቆ፡ከሰማይ፡በታች፡ካለ፡ካንድ፡አገር፡ከሰማይ፡በታች፡ወዳለው፡ወደ፡ሌላ፡አገር፡ እንደሚያበራ፥የሰው፡ልጅ፡በቀኑ፡እንዲህ፡ይኾናል። 25፤አስቀድሞ፡ግን፡ብዙ፡መከራ፡እንዲቀበል፥ከዚህም፡ትውልድ፡እንዲጣል፡ይገ፟ባ፟ዋል። 26፤በኖኅ፡ዘመንም፡እንደ፡ኾነ፥በሰው፡ልጅ፡ዘመን፡ደግሞ፡እንዲሁ፡ይኾናል። 27፤ኖኅ፡ወደ፡መርከብ፡እስከገባበት፡ቀን፡ድረስ፥ይበሉና፡ይጠጡ፡ያገቡና፡ይጋቡም፡ነበር፥የጥፋት፡ውሃም፡ መጣ፡ዅሉንም፡አጠፋ። 28፤እንዲሁ፡በሎጥ፡ዘመን፡እንደ፡ኾነ፤ይበሉ፡ይጠጡም፡ይገዙም፡ይሸጡም፡ይተክሉም፡ቤትም፡ይሠሩ፡ ነበር፤ 29፤ሎጥ፡ከሰዶም፡በወጣበት፡ቀን፡ግን፡ከሰማይ፡እሳትና፡ዲን፡ዘነበ፡ዅሉንም፡አጠፋ። 30፤የሰው፡ልጅ፡በሚገለጥበት፡ቀን፡እንዲሁ፡ይኾናል። 31፤በዚያም፡ቀን፡በሰገነት፡ያለ፡በቤቱ፡ያለውን፡ዕቃ፡ሊወስድ፡አይውረድ፥እንዲሁም፡በዕርሻ፡ያለ፡ወደ፡ ዃላው፡አይመለስ። 32፤የሎጥን፡ሚስት፡ዐስቧት። 33፤ነፍሱን፡ሊያድን፡የሚፈልግ፡ዅሉ፡ያጠፋታል፥ነፍሱንም፡የሚያጠፋ፡ዅሉ፡በሕይወት፡ይጠብቃታል። 34፤እላችዃለኹ፥በዚያች፡ሌሊት፡ኹለት፡ሰዎች፡ባንድ፡ዐልጋ፡ይኾናሉ፤አንዱ፡ይወሰዳል፡ኹለተኛውም፡ይቀራል። 35፤ኹለት፡ሴቶች፡ባንድ፡ወፍጮ፡ይፈጫሉ፤አንዲቱ፡ትወሰዳለች፡ኹለተኛዪቱም፡ትቀራለች። 36፤ኹለት፡ሰዎች፡በዕርሻ፡ይኾናሉ፤አንዱ፡ይወሰዳል፡ኹለተኛውም፡ይቀራል። 37፤መልሰውም፦ጌታ፡ሆይ፥ወዴት፡ነው፧አሉት።ርሱም፦ሥጋ፡ወዳለበት፡በዚያ፡አሞራዎች፡ይሰበሰባሉ፡ አላቸው።

ምዕራፍ ፲፰

1፤ሳይታክቱም፡ዘወትር፡ሊጸልዩ፡እንዲገባቸው፡የሚል፡ምሳሌን፡ነገራቸው፥ 2፤እንዲህ፡ሲል፦በአንዲት፡ከተማ፡እግዚአብሔርን፡የማይፈራ፡ሰውንም፡የማያፍር፡አንድ፡ዳኛ፡ነበረ። 3፤በዚያችም፡ከተማ፡አንዲት፡መበለት፡ነበረች፥ወደ፡ርሱም፡እየመጣች፦ከባላጋራዬ፡ፍረድልኝ፡ትለው፡ ነበር። 4፤ዐያሌ፡ቀንም፡አልወደደም፤ከዚህ፡በዃላ፡ግን፡በልቡ፦ምንም፡እግዚአብሔርን፡ባልፈራ፡ሰውንም፡ ባላፍር፥ 5፤ይህች፡መበለት፡ስለምታደክመኝ፡ዅልጊዜም፡እየመጣች፡እንዳታውከኝ፡እፈርድላታለኹ፡አለ። 6፤ጌታም፡አለ፦ዐመፀኛው፡ዳኛ፡ያለውን፡ስሙ። 7፤እግዚአብሔር፡እንኪያስ፡ቀንና፡ሌሊት፡ወደ፡ርሱ፡ለሚጮኹ፡ለሚታገሣቸውም፡ምርጦቹ፡ አይፈርድላቸውምን፧ 8፤እላችዃለኹ፥ፈጥኖ፡ይፈርድላቸዋል።ነገር፡ግን፥የሰው፡ልጅ፡በመጣ፡ጊዜ፡በምድር፡እምነትን፡ያገኝ፡ ይኾንን፧ 9፤ጻድቃን፡እንደ፡ኾኑ፡በራሳቸው፡ለሚታመኑና፡ሌላዎቹን፡ዅሉ፡በጣም፡ለሚንቁ፡ይህን፡ምሳሌ፡ነገራቸው፥ 10፤እንዲህ፡ሲል፦ኹለት፡ሰዎች፡ሊጸልዩ፡ወደ፡መቅደስ፡ወጡ፥አንዱ፡ፈሪሳዊ፡ኹለተኛውም፡ቀራጭ። 11፤ፈሪሳዊም፡ቆሞ፡በልቡ፡ይህን፡ሲጸልይ፦እግዚአብሔር፡ሆይ፥እንደ፡ሌላ፡ሰው፡ዅሉ፥ቀማኛዎችና፡ ዐመፀኛዎች፡አመንዝራዎችም፥ወይም፡እንደዚህ፡ቀራጭ፡ስላልኾንኹ፡አመሰግንኻለኹ፤ 12፤በየሳምንቱ፡ኹለት፡ጊዜ፡እጦማለኹ፥ከማገኘውም፡ዅሉ፡ዓሥራት፡አወጣለኹ፡አለ። 13፤ቀራጩ፡ግን፡በሩቅ፡ቆሞ፡ዐይኖቹን፡ወደ፡ሰማይ፡ሊያነሣ፡እንኳ፡አልወደደም፥ነገር፡ግን፦አምላክ፡ ሆይ፥እኔን፡ኀጢአተኛውን፡ማረኝ፡እያለ፡ደረቱን፡ይደቃ፡ነበር። 14፤እላችዃለኹ፥ከዚያ፡ይልቅ፡ይህ፡ጻድቅ፡ኾኖ፡ወደ፡ቤቱ፡ተመለሰ፤ራሱን፡ከፍ፡የሚያደርግ፡ዅሉ፡ ይዋረዳልና፥ራሱን፡ግን፡የሚያዋርድ፡ከፍ፡ይላል። 15፤እንዲዳስሳቸውም፡ሕፃናትን፡ደግሞ፡ወደ፡ርሱ፡አመጡ፤ደቀ፡መዛሙርቱም፡አይተው፡ገሠጿቸው። 16፤ኢየሱስ፡ግን፡ሕፃናትን፡ወደ፡ርሱ፡ጠርቶ፦ሕፃናት፡ወደ፡እኔ፡ይመጡ፡ዘንድ፡ተዉአቸው፡ አትከልክሏቸውም፤የእግዚአብሔር፡መንግሥት፡እንደ፡እነዚህ፡ላሉት፡ናትና። 17፤እውነት፡እላችዃለኹ፥የእግዚአብሔርን፡መንግሥት፡እንደ፡ሕፃን፡የማይቀበላት፡ዅሉ፡ከቶ፡አይገባባትም፡ አለ። 18፤ከአለቃዎችም፡አንዱ፦ቸር፡መምህር፥የዘለዓለምን፡ሕይወት፡እንድወርስ፡ምን፡ላድርግ፧ብሎ፡ጠየቀው። 19፤ኢየሱስም፦ስለ፡ምን፡ቸር፡ትለኛለኽ፧ከአንዱ፡ከእግዚአብሔር፡በቀር፡ቸር፡ማንም፡የለም። 20፤ትእዛዛቱን፡ታውቃለኽ፥አታመንዝር፥አትግደል፥አትስረቅ፥በሐሰት፡አትመስክር፥አባትኽንና፡እናትኽን፡ አክብር፡አለው። 21፤ርሱም፦ይህን፡ዅሉ፡ከሕፃንነቴ፡ዠምሬ፡ጠብቄያለኹ፡አለ። 22፤ኢየሱስም፡ይህን፡ሰምቶ፦አንዲት፡ገና፡ቀርታኻለች፤ያለኽን፡ዅሉ፡ሽጠኽ፡ለድኻዎች፡ስጥ፥በሰማይም፡ መዝገብ፡ታገኛለኽ፥መጥተኽም፡ተከተለኝ፡አለው። 23፤ርሱ፡ግን፡ይህን፡ሰምቶ፡እጅግ፡ባለጠጋ፡ነበርና፥ብዙ፡ዐዘነ። 24፤ኢየሱስም፡ብዙ፡እንዳዘነ፡አይቶ፦ገንዘብ፡ላላቸው፡ወደእግዚአብሔር፡መንግሥት፡መግባት፡እንዴት፡ ጭንቅ፡ይኾናል። 25፤ባለጠጋ፡ወደእግዚአብሔር፡መንግሥት፡ከሚገባ፡ይልቅ፡ግመል፡በመርፌ፡ቀዳዳ፡ሊገባ፡ይቀላል፡አለ። 26፤የሰሙትም፦እንግዲህ፡ማን፡ሊድን፡ይችላል፧አሉ። 27፤ርሱ፡ግን፦በሰው፡ዘንድ፡የማይቻል፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ይቻላል፡አለ። 28፤ጴጥሮስም፦እንሆ፥እኛ፡ዅሉን፡ትተን፡ተከተልንኽ፡አለ። 29፤ርሱም፦እውነት፡እላችዃለኹ፥ስለእግዚአብሔር፡መንግሥት፡ቤትን፡ወይም፡ወላጆችን፡ወይም፡ ወንድሞችን፡ወይም፡ሚስትን፡ወይም፡ልጆችን፡የተወ፥ 30፤በዚህ፡ዘመን፡ብዙ፡ዕጥፍ፡በሚመጣውም፡ዓለም፡የዘለዓለምን፡ሕይወት፡የማይቀበል፡ማንም፡የለም፡ አላቸው። 31፤ዐሥራ፡ኹለቱንም፡ወደ፡ርሱ፡አቅርቦ፡እንዲህ፡አላቸው:እንሆ፥ወደ፡ኢየሩሳሌም፡እንወጣለን፥ስለሰው፡ ልጅም፡በነቢያት፡የተጻፈው፡ዅሉ፡ይፈጸማል። 32፤ለአሕዛብ፡አሳልፈው፡ይሰጡታልና፥ይዘብቱበትማል፡ያንገላቱትማል፡ይተፉበትማል፤ 33፤ከገረፉትም፡በዃላ፡ይገድሉታል፥በሦስተኛውም፡ቀን፡ይነሣል። 34፤እነርሱም፡ከዚህ፡ነገር፡ምንም፡አላስተዋሉም፥ይህም፡ቃል፡ተሰውሮባቸው፡ነበር፥የተናገረውንም፡ አላወቁም። 35፤ወደ፡ኢያሪኮም፡በቀረበ፡ጊዜ፡አንድ፡ዕውር፡እየለመነ፡በመንገድ፡ዳር፡ተቀምጦ፡ነበር። 36፤ሕዝብም፡ሲያልፍ፡ሰምቶ፦ይህ፡ምንድር፡ነው፧ብሎ፡ጠየቀ። 37፤እነርሱም፦የናዝሬቱ፡ኢየሱስ፡ያልፋል፡ብለው፡አወሩለት። 38፤ርሱም፦የዳዊት፡ልጅ፥ኢየሱስ፡ሆይ፥ማረኝ፡እያለ፡ጮኸ። 39፤በስተፊት፡ይኼዱ፡የነበሩትም፡ዝም፡እንዲል፡ገሠጹት፤ርሱ፡ግን፦የዳዊት፡ልጅ፡ሆይ፥ማረኝ፡እያለ፡ አብዝቶ፡ጮኸ። 40፤ኢየሱስም፡ቆሞ፡ወደ፡ርሱ፡እንዲያመጡት፡አዘዘ።በቀረበም፡ጊዜ፦ምን፡ላደርግልኽ፡ትወዳለኽ፧ብሎ፡ ጠየቀው። 41፤ርሱም፦ጌታ፡ሆይ፥አይ፡ዘንድ፡ነው፡አለው። 42፤ኢየሱስም፦እይ፤እምነትኽ፡አድኖኻል፡አለው። 43፤በዚያን፡ጊዜም፡አየ፥እግዚአብሔርም፡እያከበረ፡ተከተለው።ሕዝቡም፡ዅሉ፡አይተው፡እግዚአብሔርን፡ አመሰገኑ።

ምዕራፍ ፲፱

1-2 ወደ ኢያሪኮም ገብቶ ያልፍ ነበር። እነሆም ዘኬዎስ የሚባል ሰው፥ እርሱም የቀራጮች አለቃ ነበረ፥ ባለ ጠጋም ነበረ።

3 ኢየሱስንም የትኛው እንደ ሆነ ሊያይ ይፈልግ ነበር፤ ቁመቱም አጭር ነበረና ስለ ሕዝቡ ብዛት አቃተው።

4 በዚያችም መንገድ ያልፍ ዘንድ አለውና ያየው ዘንድ ወደ ፊት ሮጦ በአንድ ሾላ ላይ ወጣ።

5 ኢየሱስም ወደዚያ ስፍራ በደረሰ ጊዜ፥ አሻቅቦ አየና፦ ዘኬዎስ ሆይ፥ ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛልና ፈጥነህ ውረድ አለው።

6 ፈጥኖም ወረደ በደስታም ተቀበለው።

7 ሁሉም አይተው፦ከኃጢአተኛ ሰው ጋር ሊውል ገባ ብለው አንጐራጐሩ።

8 ዘኬዎስ ግን ቆሞ ጌታን፦ ጌታ ሆይ፥ ካለኝ ሁሉ እኵሌታውን ለድሆች እሰጣለሁ፤ ማንንም በሐሰት ከስሼ እንደ ሆንሁ አራት እጥፍ እመልሳለሁ አለው።

9 ኢየሱስም፦ እርሱ ደግሞ የአብርሃም ልጅ ነውና ዛሬ ለዚህ ቤት መዳን ሆኖለታል፤

10 የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአለና አለው።

11 እነርሱም ይህን ሲሰሙ፥ ወደ ኢየሩሳሌም መቅረቡ ስለ ሆነ የእግዚአብሔርም መንግሥት ፈጥኖ ሊገለጥ እንዳለው ስለ መሰላቸው ምሳሌ ጭምር ተናገረ።

12 ስለዚህም እንዲህ አላቸው፦ አንድ መኰንን ለራሱ መንግሥትን ይዞ ሊመለሰ ወደ ሩቅ አገር ሄደ።

13 አሥር ባሪያዎችንም ጠርቶ አሥር ምናን ሰጣቸውና፦ እስክመጣ ድረስ ነግዱ አላቸው።

14 የአገሩ ሰዎች ግን ይጠሉት ነበርና፦ ይህ በላያችን ሊነግሥ አንወድም ብለው በኋላው መልክተኞችን ላኩ።

15 መንግሥትንም ይዞ በተመለሰ ጊዜ፥ ገንዘብ የሰጣቸውን እነዚህን ባሪያዎች ነግደው ምን ያህል እንዳተረፉ ያውቅ ዘንድ እንዲጠሩለት አዘዘ።

16 የፊተኛውም ደርሶ፦ ጌታ ሆይ፥ ምናንህ አሥር ምናን አተረፈ አለው።

17 እርሱም፦ መልካም፥ አንተ በጎ ባሪያ፥ በጥቂት የታመንህ ስለ ሆንህ በአሥር ከተማዎች ላይ ሥልጣን ይሁንልህ አለው።

18 ሁለተኛውም መጥቶ፦ ጌታ ሆይ፥ ምናንህ አምስት ምናን አተረፈ አለው።

19 ይህንም ደግሞ፦ አንተም በአምስት ከተማዎች ላይ ሁን አለው።

20 ሌላውም መጥቶ፦ ጌታ ሆይ፥ በጨርቅ ጠቅልዬ የጠበቅኋት ምናንህ እነሆ፤

21 ፈርቼሃለሁና፥ ጨካኝ ሰው ስለ ሆንህ፤ ያላኖርኸውን ትወስዳለህ ያልዘራኸውንም ታጭዳለህ አለው።

22 እርሱም፦ አንተ ክፉ ባሪያ፥ አፍህ በተናገረው እፈርድብሃለሁ። እኔ ያላኖርሁትን የምወስድና ያልዘራሁትን የማጭድ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንሁ አወቅህ፤ ምን ነው ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ያልሰጠኸው?

23 እኔም መጥቼ ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር አለው።

24 በዚያም ቆመው የነበሩትን፦ ምናኑን ውሰዱበት አሥሩ ምናን ላለውም ስጡት አላቸው።

25 እርሱም፦ ጌታ ሆይ፥ አሥር ምናን አለው አሉት።

26 እላችኋለሁ፥ ላለው ሁሉ ይሰጠዋል፥ ከሌለው ግን ያው ያለው ስንኳ ይወሰድበታል።

27 ነገር ግን እነዚያን በላያቸው ልነግሥ ያልወደዱትን ጠላቶቼን ወደዚህ አምጡአቸው በፊቴም እረዱአቸው።

28 ይህንም ከተናገረ በኋላ፥ ወደ ኢየሩሳሌም ሲወጣ ይቀድማቸው ነበር።

29 ደብረ ዘይትም በሚባል ተራራ አጠገብ ወዳሉት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረበ ጊዜ፥ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ላከና፦

30 በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ ወደ እርስዋም ገብታችሁ ከሰው ማንም ገና ያልተቀመጠበት ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁ፥ ፈትታችሁም አምጡት።

31 ማንም፦ ስለ ምን ትፈቱታላችሁ? ብሎ ቢጠይቃችሁ፥ እንዲሁ፦ ለጌታ ያስፈልገዋል በሉ አላቸው።

32 የተላኩትም ሄደው እንዳላቸው አገኙ።

33 እነርሱም ውርንጫውን ሲፈቱ ጌቶቹ፦ ውርንጫውን ስለ ምን ትፈቱታላችሁ? አሉአቸውም

34 እነርሱም፦ ለጌታ ያስፈልገዋል አሉ።

35 ወደ ኢየሱስም አመጡት፥ በውርንጫውም ላይ ልብሳቸውን ጭነው ኢየሱስን አስቀመጡት።

36 ሲሄድም ልብሳቸውን በመንገድ ያነጥፉ ነበር።

37 ወደ ደብረ ዘይት ቍልቍለትም አሁን በቀረበ ጊዜ፥ ደቀ መዛሙርቱ ሁላቸው ደስ እያላቸው ተአምራትን ሁሉ ስላዩ በታላቅ ድምፅ እግዚአብሔርን ሊያመሰግኑ ጀምረው።

38 በጌታ ስም የሚመጣ ንጉሥ የተባረከ ነው፤ በሰማይ ሰላም በአርያምም ክብር አሉ።

39 ከሕዝብም መካከል ከፈሪሳውያን አንዳንዱ፦ መምህር ሆይ፥ ደቀ መዛሙርትህን ገሥጻቸው አሉት።

40 መልሶም፦ እላችኋለሁ፥ እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉ አላቸው።

41 ሲቀርብም ከተማይቱን አይቶ አለቀሰላት፥

42 እንዲህ እያለ፦ ለሰላምሽ የሚሆነውን በዚህ ቀን አንቺስ ስንኳ ብታውቂ፤ አሁን ግን ከዓይንሽ ተሰውሮአል።

43 ወራት ይመጣብሻልና፥ ጠላቶችሽም ቅጥር ይቀጥሩብሻል ይከቡሻልም በየበኵሉም ያስጨንቁሻል፤

44 አንቺንም በአንቺም ውስጥ የሚኖሩትን ልጆችሽን ወደ ታች ይጥላሉ፥ በአንቺ ውስጥም ድንጋይ በድንጋይ ላይ አይተዉም፥ የመጐብኘትሽን ዘመን አላወቅሽምና።

45 ወደ መቅደስም ገብቶ በእርሱ የሚሸጡትን የሚገዙትንም ያወጣ ጀመር፤

46 እርሱም፦ ቤቴ የጸሎት ቤት ይሆናል ተብሎ ተጽፎአል፤ እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት አላቸው።

47 ዕለት ዕለትም በመቅደስ ያስተምር ነበር፤ ነገር ግን የካህናት አለቆችና ጻፎች የሕዝቡ ታላላቆችም ሊገድሉት ይፈልጉ ነበር፥

48 የሚያደርጉበትንም አጡ፤ ሕዝቡ ሁሉ ሲሰሙት ተንጠልጥለውበት ነበርና።

ምዕራፍ ፳

1፤አንድ፡ቀንም፡ሕዝቡን፡በመቅደስ፡ሲያስተምር፡ወንጌልንም፡ሲሰብክላቸው፥የካህናት፡አለቃዎችና፡ጻፊዎች፡ ከሽማግሌዎች፡ጋራ፡ወደ፡ርሱ፡ቀረቡና፦ 2፤እስኪ፡ንገረን፤እነዚህን፡በምን፡ሥልጣን፡ታደርጋለኽ፡ወይስ፡ይህን፡ሥልጣን፡የሰጠኽ፡ማን፡ ነው፧ብለው፡ተናገሩት። 3፤መልሶም፦እኔ፡ደግሞ፡አንዲት፡ነገር፡እጠይቃችዃለኹ፥እናንተም፡ንገሩኝ፤ 4፤የዮሐንስ፡ጥምቀት፡ከሰማይ፡ነበረችን፡ወይስ፡ከሰው፧አላቸው። 5፤ርስ፡በርሳቸውም፡ሲነጋገሩ፦ከሰማይ፡ብንል፦ስለ፡ምን፡አላመናችኹበትም፧ይለናል፤ 6፤ከሰው፡ብንል፡ግን፡ሕዝቡ፡ዅሉ፡ይወግሩናል፤ዮሐንስ፡ነቢይ፡እንደ፡ነበረ፡ዅሉ፡ያምኑ፡ነበርና፥አሉ። 7፤መልሰውም፦ከወዴት፡እንደ፡ኾነ፡አናውቅም፡አሉት። 8፤ኢየሱስም፦እኔም፡በምን፡ሥልጣን፡እነዚህን፡እንዳደርግ፡አልነግራችኹም፡አላቸው። 9፤ይህንም፡ምሳሌ፡ለሕዝቡ፡ይላቸው፡ዠመር፦አንድ፡ሰው፡የወይን፡አትክልት፡ተከለ፡ለገበሬዎችም፡ አከራይቶ፡ለብዙ፡ዘመን፡ወደ፡ሌላ፡አገር፡ኼደ። 10፤በጊዜውም፡ከወይኑ፡አትክልት፡ፍሬ፡እንዲሰጡት፡አንድ፡ባሪያ፡ወደ፡ገበሬዎች፡ላከ፤ገበሬዎቹ፡ግን፡ ደበደቡት፡ባዶውንም፡ሰደዱት። 11፤ጨምሮም፡ሌላውን፡ባሪያ፡ላከ፤እነርሱም፡ያን፡ደግሞ፡ደበደቡት፡አዋርደውም፡ባዶውን፡ሰደዱት። 12፤ጨምሮም፡ሦስተኛውን፡ላከ፤እነርሱም፡ይህን፡ደግሞ፡አቍስለው፡አወጡት። 13፤የወይኑም፡አትክልት፡ጌታ፦ምን፡ላድርግ፧የምወደ፟ውን፡ልጄን፡እልካለኹ፤ምናልባት፡ርሱን፡አይተው፡ ያፍሩታል፡አለ። 14፤ገበሬዎቹ፡ግን፡አይተውት፡ርስ፡በርሳቸው፡ሲነጋገሩ፦ወራሹ፡ይህ፡ነው፤ርስቱ፡ለእኛ፡እንዲኾን፡ኑ፡ እንግደለው፡አሉ። 15፤ከወይኑም፡አትክልት፡ወደ፡ውጭ፡አውጥተው፡ገደሉት።እንግዲህ፡የወይኑ፡አትክልት፡ጌታ፡ምን፡ ያደርጋቸዋል፧ 16፤ይመጣል፡እነዚህንም፡ገበሬዎች፡ያጠፋል፥የወይኑንም፡አትክልት፡ለሌላዎች፡ይሰጣል። ይህንም፡በሰሙ፡ ጊዜ፦ይህስ፡አይኹን፡አሉ። 17፤ርሱ፡ግን፡ወደ፡እነርሱ፡ተመልክቶ፦እንግዲህ፦ግንበኛዎች፡የናቁት፡ድንጋይ፡ርሱ፡የማእዘን፡ራስ፡ ኾነ፡ተብሎ፡የተጻፈው፡ይህ፡ምንድር፡ነው፧ 18፤በዚያም፡ድንጋይ፡ላይ፡የሚወድቅ፡ዅሉ፡ይቀጠቀጣል፤የሚወድቅበትን፡ዅሉ፡ግን፡ይፈጨዋል፡አለ። 19፤የካህናት፡አለቃዎችና፡ጻፊዎችም፡ይህን፡ምሳሌ፡በእነርሱ፡ላይ፡እንደ፡ተናገረ፡ዐውቀው፡በዚያች፡ሰዓት፡ እጃቸውን፡ሊጭኑበት፡ፈለጉ፥ነገር፡ግን፥ሕዝቡን፡ፈሩ። 20፤ሲጠባበቁም፡ወደገዢ፡ግዛትና፡ሥልጣን፡አሳልፈው፡እንዲሰጡት፡ጻድቃን፡መስለው፡በቃሉ፡ የሚያጠምዱትን፡ሸማቂዎች፡ሰደዱበት። 21፤ጠይቀውም፦መምህር፡ሆይ፥እውነትን፡እንድትናገርና፡እንድታስተምር፡ለሰው፡ፊትም፡እንዳታደላ፡ እናውቃለን፥በእውነት፡የእግዚአብሔርን፡መንገድ፡ታስተምራለኽ፡እንጂ፤ 22፤ለቄሳር፡ግብር፡ልንሰጥ፡ተፈቅዷልን፧ወይስ፡አልተፈቀደም፧አሉት። 23፤ርሱ፡ግን፡ተንኰላቸውንም፡ተመልክቶ፦ስለ፡ምን፡ትፈትኑኛላችኹ፧አንድ፡ዲናር፡አሳዩኝ፤ 24፤መልኩ፡ጽሕፈቱስ፡የማን፡ነው፧አላቸው።መልሰውም፦የቄሳር፡ነው፡አሉት። 25፤ርሱም፦እንኪያስ፡የቄሳርን፡ለቄሳር፡የእግዚአብሔርንም፡ለእግዚአብሔር፡አስረክቡ፡አላቸው። 26፤በሕዝቡም፡ፊት፡በቃሉ፡ሊያጠምዱት፡አልቻሉም፡በመልሱም፡እየተደነቁ፡ዝም፡አሉ። 27፤ትንሣኤ፡ሙታንንም፡የሚክዱ፡ከሰዱቃውያን፡አንዳንዶቹ፡ቀርበው፡ጠየቁት፥ 28፤እንዲህ፡ሲሉ፦መምህር፡ሆይ፥ሙሴ፦ሚስት፡ያለችው፡የአንድ፡ሰው፡ወንድም፡ልጅ፡ሳይወልድ፡ ቢሞት፥ወንድሙ፡ሚስቱን፡አግብቶ፡ለወንድሙ፡ዘር፡ይተካ፡ብሎ፡ጻፈልን። 29፤እንግዲያስ፡ሰባት፡ወንድማማች፡ነበሩ፤የፊተኛውም፡ሚስት፡አግብቶ፡ልጅ፡ሳይወልድ፡ሞተ፤ 30-31፤ኹለተኛውም፡አገባት፥ሦስተኛውም፥እንዲሁም፡ሰባቱ፡ደግሞ፡ልጅ፡ሳይተዉ፡ሞቱ። 32፤ከዅሉም፡በዃላ፡ሴቲቱ፡ደግሞ፡ሞተች። 33፤እንግዲህ፡ሰባቱ፡አግብተዋታልና፥ሴቲቱ፡በትንሣኤ፡ከነርሱ፡ለማንኛቸው፡ሚስት፡ትኾናለች፧ 34፤ኢየሱስም፡መልሶ፡እንዲህ፡አላቸው፦የዚህ፡ዓለም፡ልጆች፡ያገባሉ፡ይጋባሉም፥ 35፤ያን፡ዓለምና፡ከሙታን፡ትንሣኤ፡ሊያገኙ፡የሚገ፟ባ፟ቸው፡እነዚያ፡ግን፡አያገቡም፡አይጋቡምም፥እንደ፡ መላእክት፡ናቸውና፥ 36፤ሊሞቱም፡ወደ፡ፊት፡አይቻላቸውም፥የትንሣኤም፡ልጆች፡ስለ፡ኾኑ፡የእግዚአብሔር፡ልጆች፡ናቸው። 37፤ሙታን፡እንዲነሡ፡ግን፡ሙሴ፡ደግሞ፡በቍጥቋጦው፡ዘንድ፡ጌታን፡የአብርሃም፡አምላክ፡የይሥሐቅም፡ አምላክ፡የያዕቆብም፡አምላክ፡በማለቱ፡አስታወቀ፤ 38፤ዅሉ፡ለርሱ፡ሕያዋን፡ስለ፡ኾኑ፥የሕያዋን፡አምላክ፡ነው፡እንጂ፡የሙታን፡አይደለም። 39፤ከጻፊዎችም፡አንዳንዶቹ፡መልሰው፦መምህር፡ሆይ፥መልካም፡ተናገርኽ፡አሉት። 40፤ወደ፡ፊትም፡አንድ፡ነገር፡ስንኳ፡ሊጠይቁት፡አልደፈሩም። 41፤እንዲህም፡አላቸው፦ክርስቶስ፡የዳዊት፡ልጅ፡ነው፡እንዴት፡ይላሉ፧ 42-43፤ዳዊትም፡ራሱ፡በመዝሙራት፡መጽሐፍ፦ጌታ፡ጌታዬን፦ጠላቶችኽን፡ለእግርኽ፡መርገጫ፡ እስካደርግልኽ፡ድረስ፡በቀኜ፡ተቀመጥ፡አለው፡ይላል። 44፤እንግዲህ፡ዳዊት፦ጌታ፡ብሎ፡ይጠራዋል፥እንዴትስ፡ልጁ፡ይኾናል፧ 45፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡ሲሰሙ፡ደቀ፡መዛሙርቱን፦ 46፤ረዣዥም፡ልብስ፡ለብሰው፡መዞር፡ከሚፈልጉ፥በገበያም፡ሰላምታ፥በምኵራብም፡የከበሬታ፡ ወንበር፥በምሳም፡የከበሬታ፡ስፍራ፡ከሚወዱ፡ከጻፊዎች፡ተጠበቁ፤ 47፤የመበለቶችን፡ቤት፡የሚበሉ፡ጸሎታቸውንም፡በማስረዘም፡የሚያመካኙ፥እነዚህ፡የባሰ፡ፍርድ፡ይቀበላሉ፡አለ።

ምዕራፍ ፳፩

1 ዓይኑንም አንሥቶ መባቸውን በመዝገብ የሚጥሉ ባለ ጠጎችን አየ።

2 አንዲትም ድሀ መበለት ሁለት ሳንቲም በዚያ ስትጥል አየና፦

3 እውነት እላችኋለሁ፥ ይህች ድሀ መበለት ከሁሉ ይልቅ አብልጣ ጣለች፤

4 እነዚህ ሁሉ ከትርፋቸው ወደ እግዚአብሔር መዝገብ ጥለዋልና፤ ይህች ግን ከጕድለትዋ የነበራትን ትዳርዋን ሁሉ ጣለች አለ።

5 አንዳንዶቹም ስለ መቅደስ በመልካም ድንጋይና በተሰጠው ሽልማት እንዳጌጠ ሲነጋገሩ፦ ይህማ የምታዩት ሁሉ፥

6 ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ የማይቀርበት ዘመን ይመጣል አለ።

7 እነርሱም፦ መምህር ሆይ፥ እንግዲህ ይህ መቼ ይሆናል? ይህስ ይሆን ዘንድ እንዳለው ምልክቱ ምንድር ነው? ብለው ጠየቁት።

8 እንዲህም አለ፦ እንዳትስቱ ተጠንቀቁ፤ ብዙዎች፦ እኔ ነኝ፥ ዘመኑም ቀርቦአል እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ እነርሱን ተከትላችሁ አትሂዱ።

9 ጦርንና ሁከትንም በሰማችሁ ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህ አስቀድሞ ይሆን ዘንድ ግድ ነውና፥ ነገር ግን መጨረሻው ወዲያው አይሆንም።

10 በዚያን ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣል፤

11 ታላቅም የምድር መናወጥና በልዩ ልዩ ስፍራ ቸነፈር ራብም ይሆናል፤ የሚያስፈራም ነገር ከሰማይም ታላቅ ምልክት ይሆናል።

12 ከዚህም ሁሉ በፊት እጃቸውን በላያችሁ ይጭናሉ ያሳድዱአችሁማል፤ ስለ ስሜም ወደ ምኵራብና ወደ ወኅኒ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ ወደ ነገሥታትና ወደ ገዥዎችም ይወስዱአችኋል፤

13 ይህም ለምስክርነት ይሆንላችኋል።

14 ስለዚህ እንዴት እንድትመልሱ አስቀድማችሁ እንዳታስቡ በልባችሁ አኑሩት፤

15 ወደረኞቻችሁ ሁሉ ሊቃወሙና ሊከራከሩ የማይችሉትን አፍና ጥበብ እሰጣችኋለሁና።

16 ወላጆችም ስንኳ ወንድሞችም ዘመዶችም ወዳጆችም አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ ከእናንተም አንዳንዱን ይገድላሉ፤

17 በሁሉም ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።

18 ከራሳችሁም አንዲት ጠጉር ስንኳ አትጠፋም፤

19 በመታገሣችሁም ነፍሳችሁን ታገኛላችሁ።

20 ኢየሩሳሌም ግን በጭፍራ ተከባ ስታዩ በዚያን ጊዜ ጥፋትዋ እንደ ቀረበ እወቁ።

21 የዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራራዎች ይሽሹ፥ በመካከልዋም ያሉ ከእርስዋ ፈቀቅ ይበሉ፥ በገጠር ያሉም ወደ እርስዋ አይግቡ፤

22 የተጻፈው ሁሉ እንዲፈጸም ይህ የበቀል ጊዜ ነውና።

23 በዚያን ወራት ለእርጕዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው፤ ታላቅ ችግር በምድር ላይ፥ በዚህም ሕዝብ ላይ ቍጣ ይሆናልና፤

24 በሰይፍ ስለትም ይወድቃሉ፤ ወደ አሕዛብ ሁሉም ይማረካሉ፤ የአሕዛብም ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።

25 በፀሐይና በጨረቃም በከዋክብትም ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ ከባሕሩና ከሞገዱም ድምፅ የተነሣ እያመነቱ ይጨነቃሉ፤

26 ሰዎችም ከፍርሃትና በዓለም የሚመጣበትን ከመጠበቅ የተነሣ ይደክማሉ፤ የሰማያት ኃይላት ይናወጣሉና።

27 በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በኃይልና በብዙ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል።

28 ይህም ሊሆን ሲጀምር ቤዛችሁ ቀርቦአልና አሻቅባችሁ ራሳችሁን አንሡ።

29 ምሳሌንም ነገራቸው እንዲህ ሲል፦ በለስንና ዛፎችን ሁሉ እዩ፤

30 ሲያቈጠቍጡ ተመልክታችሁ በጋ አሁን እንደ ቀረበ ራሳችሁ ታውቃላችሁ።

31 እንዲሁ ደግሞ እናንተ ይህ ሁሉ መሆኑን ስታዩ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ ቀረበች እወቁ።

32 እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም።

33 ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም።

34 ነገር ግን ልባችሁ በመጠጥ ብዛትና በስካር ስለ ትዳርም በማሰብ እንዳይከብድ፥ ያ ቀንም በድንገት እንዳይመጣባችሁ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤

35 በምድር ሁሉ ላይ በሚቀመጡ ሁሉ እንደ ወጥመድ ይደርስባቸዋልና።

36 እንግዲህ ሊመጣ ካለው ከዚህ ሁሉ ለማምለጥ፥ በሰው ልጅም ፊት ለመቆም እንድትችሉ ስትጸልዩ ሁል ጊዜ ትጉ።

37 ዕለት ዕለትም በመቅደስ ያስተምር ነበር፥ ሌሊት ግን ደብረ ዘይት ወደምትባል ተራራ ወጥቶ ያድር ነበር።

38 ሕዝቡም ሁሉ ይሰሙት ዘንድ ማልደው በመቅደስ ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።

ምዕራፍ ፳፪

1፤ፋሲካም፡የሚባለው፡የቂጣ፡በዓል፡ቀረበ። 2፤የካህናት፡አለቃዎችና፡ጻፊዎችም፡እንዴት፡እንዲያጠፉት፡ይፈልጉ፡ነበር፤ሕዝቡን፡ይፈሩ፡ነበርና። 3፤ሰይጣንም፡ከዐሥራ፡ኹለቱ፡ቍጥር፡አንዱ፡በነበረው፡የአስቆሮቱ፡በሚባለው፡በይሁዳ፡ገባ፤ 4፤ኼዶም፡እንዴት፡አሳልፎ፡እንዲሰጣቸው፡ከካህናት፡አለቃዎችና፡ከመቅደስ፡አዛዦች፡ጋራ፡ተነጋገረ። 5፤እነርሱም፡ደስ፡አላቸው፥ገንዘብም፡ሊሰጡት፡ተዋዋሉ። 6፤ዕሺም፡አለ፥ሕዝብም፡በሌለበት፡አሳልፎ፡እንዲሰጣቸው፡ምቹ፡ጊዜ፡ይፈልግ፡ነበር። 7፤ፋሲካንም፡ሊያርዱበት፡የሚገ፟ባ፟ው፡የቂጣ፡በዓል፡ደረሰ፤ 8፤ጴጥሮስንና፡ዮሐንስንም፦ፋሲካን፡እንድንበላ፡ኼዳችኹ፡አዘጋጁልን፡ብሎ፡ላካቸው። 9፤እነርሱም፦ወዴት፡እናዘጋጅ፡ዘንድ፡ትወዳለኽ፧አሉት። 10፤ርሱም፡አላቸው፦እንሆ፥ወደ፡ከተማ፡ስትገቡ፡ማድጋ፡ውሃ፡የተሸከመ፡ሰው፡ ይገናኛችዃል፤ወደሚገባበት፡ቤት፡ተከተሉት፤ 11፤ለባለቤቱም፦መምህሩ፦ከደቀ፡መዛሙርቴ፡ጋራ፡ፋሲካን፡የምበላበት፡የእንግዳ፡ቤት፡ክፍል፡ወዴት፡ ነው፧ይልኻል፡በሉት፤ 12፤ያም፡በደርብ፡ላይ፡ያለውን፡የተነጠፈ፡ታላቅ፡አዳራሽ፡ያሳያችዃል፤በዚያም፡አሰናዱልን። 13፤ኼደውም፡እንዳላቸው፡አገኙና፡ፋሲካን፡አሰናዱ። 14፤ሰዓቱም፡በደረሰ፡ጊዜ፡ከዐሥራ፡ኹለቱ፡ሐዋርያት፡ጋራ፡በማእዱ፡ተቀመጠ። 15፤ርሱም፦ከመከራዬ፡በፊት፡ከእናንተ፡ጋራ፡ይህን፡ፋሲካ፡ልበላ፡እጅግ፡እመኝ፡ነበር፤

"ፀሎተ ሐሙስ" ክርስቶስ የመጨረሻውን ራት ከደቀመዝሙሮቹ ጋር ሲበላ

16፤እላችዃለኹና፥በእግዚአብሔር፡መንግሥት፡እስኪፈጸም፡ድረስ፥ወደ፡ፊት፡ከዚህ፡አልበላም፡አላቸው። 17፤ጽዋንም፡ተቀበለ፡አመስግኖም፦ይህን፡እንካችኹ፥በመካከላችኹም፡ተካፈሉት፤ 18፤እላችዃለኹና፥የእግዚአብሔር፡መንግሥት፡እስክትመጣ፡ድረስ፡ካኹን፡ዠምሮ፡ከወይኑ፡ፍሬ፡ አልጠጣም፡አለ። 19፤እንጀራንም፡አንሥቶ፡አመሰገነ፡ቈርሶም፡ሰጣቸውና፦ስለ፡እናንተ፡የሚሰጠው፡ሥጋዬ፡ይህ፡ነው፤ይህን፡ ለመታሰቢያዬ፡አድርጉት፡አለ። 20፤እንዲሁም፡ከእራት፡በዃላ፡ጽዋውን፡አንሥቶ፡እንዲህ፡አለ፦ይህ፡ጽዋ፡ስለ፡እናንተ፡በሚፈሰው፡በደሜ፡ የሚኾን፡ዐዲስ፡ኪዳን፡ነው። 21፤ነገር፡ግን፥አሳልፎ፡የሚሰጠኝ፡እጅ፥እንሆ፥በማእዱ፡ከእኔ፡ጋራ፡ናት። 22፤የሰው፡ልጅስ፡እንደተወሰነው፡ይኼዳል፥ነገር፡ግን፥ዐልፎ፡ለሚሰጥበት፡ለዚያ፡ሰው፡ወዮለት። 23፤ከነርሱም፡ይህን፡ሊያደርግ፡ያለው፡ማን፡እንደ፡ኾነ፡ርስ፡በርሳቸው፡ይጠያየቁ፡ዠመር። 24፤ደግሞም፡ማናቸውም፡ታላቅ፡ኾኖ፡እንዲቈጠር፡በመካከላቸው፡ክርክር፡ኾነ። 25፤እንዲህም፡አላቸው፦የአሕዛብ፡ነገሥታት፡ይገዟቸዋል፥በላያቸውም፡የሚሠለጥኑት፡ቸርነት፡አድራጊዎች፡ ይባላሉ። 26፤እናንተ፡ግን፡እንዲህ፡አትኹኑ፤ነገር፡ግን፥ከእናንተ፡ታላቅ፡የኾነ፡በመካከላችኹ፡እንደ፡ ታናሽ፥የሚገዛም፡እንደሚያገለግል፡ይኹን። 27፤በማእዱ፡የተቀመጠ፡ወይስ፡የሚያገለግል፡ማናቸው፡ታላቅ፡ነው፧የተቀመጠው፡አይደለምን፧እኔ፡ግን፡ በመካከላችኹ፡እንደሚያገለግል፡ነኝ። 28፤ነገር፡ግን፥እናንተ፡በፈተናዎቼ፡ከእኔ፡ጋራ፡ጸንታችኹ፡የኖራችኹ፡ናችኹ፤ 29-30፤አባቴ፡እኔን፡እንደ፡ሾመኝ፡እኔ፡ደግሞ፡በመንግሥቴ፡ከማእዴ፡ትበሉና፡ትጠጡ፡ዘንድ፥በዐሥራ፡ ኹለቱ፡በእስራኤል፡ነገድ፡ስትፈርዱ፡በዙፋኖች፡ትቀመጡ፡ዘንድ፡ለመንግሥት፡እሾማችዃለኹ። 31፤ጌታም፦ስምዖን፡ስምዖን፡ሆይ፥እንሆ፥ሰይጣን፡እንደ፡ስንዴ፡ሊያበጥራችኹ፡ለመነ፤ 32፤እኔ፡ግን፡እምነትኽ፡እንዳይጠፋ፡ስለ፡አንተ፡አማለድኹ፤አንተም፡በተመለስኽ፡ጊዜ፡ወንድሞችኽን፡አጽና፡አለ። 33፤ርሱም፦ጌታ፡ሆይ፥ወደ፡ወህኒም፡ወደ፡ሞትም፡ከአንተ፡ጋራ፡ለመኼድ፡የተዘጋጀኹ፡ነኝ፡አለው። 34፤ርሱ፡ግን፦ጴጥሮስ፡ሆይ፥እልኻለኹ፥እንዳታውቀኝ፡ሦስት፡ጊዜ፡እስክትክደኝ፡ድረስ፡ዛሬ፡ዶሮ፡ አይጮኽም፡አለው። 35፤ደግሞም፦ያለኰረጆና፡ያለከረጢት፡ያለጫማም፡በላክዃችኹ፡ጊዜ፥አንዳች፡ ጐደለባችኹን፧አላቸው።እነርሱም፦አንዳች፡እንኳ፡አሉ። 36፤ርሱም፦አኹን፡ግን፡ኰረጆ፡ያለው፡ከርሱ፡ጋራ፡ይውሰድ፥ከረጢትም፡ያለው፡እንዲሁ፤የሌለውም፡ ልብሱን፡ሽጦ፡ሰይፍ፡ይግዛ። 37፤እላችዃለኹና፥ይህ፦ከዐመፀኛዎች፡ጋራ፡ተቈጠረ፡ተብሎ፡የተጻፈው፡በእኔ፡ሊፈጸም፡ግድ፡ ነው፤አዎን፥ስለ፡እኔ፡የሚኾነው፡አኹን፡ይፈጸማልና፥አላቸው። 38፤እነርሱም፦ጌታ፡ሆይ፥እንሆ፥በዚህ፡ኹለት፡ሰይፎች፡አሉ፡አሉት።ርሱም፦ይበቃል፡አላቸው። 39፤ወጥቶም፡እንደ፡ልማዱ፡ወደ፡ደብረ፡ዘይት፡ኼደ፤ደቀ፡መዛሙርቱም፡ደግሞ፡ተከተሉት። 40፤ወደ፡ስፍራውም፡ደርሶ፦ወደ፡ፈተና፡እንዳትገቡ፡ጸልዩ፡አላቸው። 41፤ከነርሱም፡የድንጋይ፡ውርወራ፡የሚያኽል፡ራቀ፥ተንበርክኮም፦አባት፡ሆይ፥ 42፤ብትፈቅድ፡ይህችን፡ጽዋ፡ከእኔ፡ውሰድ፤ነገር፡ግን፥የእኔ፡ፈቃድ፡አይኹን፡የአንተ፡እንጂ፡እያለ፡ ይጸልይ፡ነበር። 43፤ከሰማይም፡መጥቶ፡የሚያበረታ፡መልአክ፡ታየው። 44፤በፍርሀትም፡ሲጣጣር፡አጽንቶ፡ይጸልይ፡ነበር፤ወዙም፡በምድር፡ላይ፡እንደሚወርድ፡እንደ፡ደም፡ ነጠብጣብ፡ነበረ። 45፤ከጸሎትም፡ተነሥቶ፡ወደ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡መጣና፡ከሐዘን፡የተነሣ፡ተኝተው፡ሲያገኛቸው። 46፤ስለ፡ምን፡ትተኛላችኹ፧ወደ፡ፈተና፡እንዳትገቡ፡ተነሥታችኹ፡ጸልዩ፡አላቸው። 47፤ገናም፡ሲናገር፥እንሆ፥ሰዎች፡መጡ፤ከዐሥራ፡ኹለቱ፡አንዱም፡ይሁዳ፡የሚባለው፡ይቀድማቸው፡ ነበር፥ሊስመውም፡ወደ፡ኢየሱስ፡ቀረበ።

ይሁዳ ክርስቶስን ለማስያዝ ከፈሪሳውያን ጋር

48፤ኢየሱስ፡ግን፦ይሁዳ፡ሆይ፥በመሳም፡የሰውን፡ልጅ፡አሳልፈኽ፡ትሰጣለኽን፧አለው። 49፤በዙሪያውም፡የነበሩት፡የሚኾነውን፡ባዩ፡ጊዜ፦ጌታ፡ሆይ፥በሰይፍ፡እንምታቸውን፧አሉት። 50፤ከነርሱም፡አንዱ፡የሊቀ፡ካህናቱን፡ባሪያ፡መቶ፟፡ቀኝ፡ዦሮውን፡ቈረጠው። 51፤ኢየሱስ፡ግን፡መልሶ፦ይህንስ፡ፍቀዱ፡አለ፤ዦሮውንም፡ዳሶ፟፡ፈወሰው። 52፤ኢየሱስም፡ወደ፡ርሱ፡ለመጡበት፡ለካህናት፡አለቃዎችና፡ለመቅደስ፡አዛዦች፡ ለሽማግሌዎችም፦ወንበዴን፡እንደምትይዙ፡ሰይፍና፡ጐመድ፡ይዛችኹ፡ወጣችኹን፧ 53፤በመቅደስ፡ዕለት፡ዕለት፡ከእናንተ፡ጋራ፡ስኾን፡እጆቻችኹን፡አልዘረጋችኹብኝም፤ይህ፡ግን፡ጊዜያችኹና፡ የጨለማው፡ሥልጣን፡ነው፡አላቸው። 54፤ይዘውም፡ወሰዱት፡ወደሊቀ፡ካህናት፡ቤትም፡አገቡት፤ጴጥሮስም፡ርቆ፡ይከተለው፡ነበር። 55፤በግቢ፡መካከልም፡እሳት፡አንድደው፡በአንድነት፡ተቀምጠው፡ሳሉ፡ጴጥሮስ፡በመካከላቸው፡ተቀመጠ። 56፤በብርሃኑም፡በኩል፡ተቀምጦ፡ሳለ፡አንዲት፡ገረድ፡አየችውና፡ትኵር፡ብላ፦ይህ፡ደግሞ፡ከርሱ፡ጋራ፡ ነበረ፡አለች። 57፤ርሱ፡ግን፦አንቺ፡ሴት፥አላውቀውም፡ብሎ፡ካደ። 58፤ከጥቂት፡ጊዜም፡በዃላ፡ሌላው፡አይቶት፦አንተ፡ደግሞ፡ከነርሱ፡ወገን፡ነኽ፡አለው።ጴጥሮስ፡ ግን፦አንተ፡ሰው፥እኔ፡አይደለኹም፡አለ። 59፤አንድ፡ሰዓትም፡የሚያኽል፡ቈይቶ፡ሌላው፡አስረግጦ፦ርሱ፡የገሊላ፡ሰው፡ነውና፥በእውነት፡ይህ፡ ደግሞ፡ከርሱ፡ጋራ፡ነበረ፡አለ። 60፤ጴጥሮስ፡ግን፦አንተ፡ሰው፥የምትለውን፡አላውቅም፡አለ።ያን፡ጊዜም፡ገና፡ሲናገር፡ዶሮ፡ጮኸ። 61፤ጌታም፡ዘወር፡ብሎ፡ጴጥሮስን፡ተመለከተው፤ጴጥሮስም፦ዛሬ፡ዶሮ፡ሳይጮኽ፡ሦስት፡ጊዜ፡ትክደኛለኽ፡ እንዳለው፡የጌታ፡ቃል፡ትዝ፡አለው። 62፤ጴጥሮስም፡ወደ፡ውጭ፡ወጥቶ፡ምርር፡ብሎ፡አለቀሰ። 63፤ኢየሱስንም፡የያዙት፡ሰዎች፡ይዘብቱበትና፡ይደበድቡት፡ነበር፤ 64፤ሸፍነውም፡ፊቱን፡ይመቱት፡ነበርና፦በጥፊ፡የመታኽ፡ማን፡ነው፧ትንቢት፡ተናገር፡እያሉ፡ይጠይቁት፡ነበር። 65፤ሌላም፡ብዙ፡ነገር፡እየተሳደቡ፡በርሱ፡ላይ፡ይናገሩ፡ነበር። 66፤በነጋም፡ጊዜ፡የሕዝቡ፡ሽማግሌዎችና፡የካህናት፡አለቃዎች፡ጻፊዎችም፡ተሰብስበው፡ወደሸንጓቸው፡ ወሰዱትና፡ 67፤ክርስቶስ፡አንተ፡ነኽን፧ንገረን፡አሉት።ርሱ፡ግን፡እንዲህ፡አላቸው፦ብነግራችኹ፡አታምኑም፤ 68፤ብጠይቅም፡አትመልሱልኝም፡አትፈቱኝምም። 69፤ነገር፡ግን፥ካኹን፡ዠምሮ፡የሰው፡ልጅ፡በእግዚአብሔር፡ኀይል፡ቀኝ፡ይቀመጣል። 70፤ዅላቸውም፦እንግዲያስ፡አንተ፡የእግዚአብሔር፡ልጅ፡ነኽን፧አሉት።ርሱም፦እኔ፡እንደ፡ኾንኹ፡ እናንተ፡ትላላችኹ፡አላቸው። 71፤እነርሱም፦ራሳችን፡ከአፉ፡ሰምተናልና፥ከእንግዲህ፡ወዲህ፡ምን፡ምስክር፡ያስፈልገናል፧አሉ።

ምዕራፍ ፳፫

1፤ዅሉም፡በሞላው፡ተነሥተው፡ወደ፡ጲላጦስ፡ወሰዱትና፦ 2፤ይህ፡ሕዝባችንን፡ሲያጣምም፡ለቄሳርም፡ግብር፡እንዳይሰጥ፡ሲከለክል፡ደግሞም፦እኔ፡ክርስቶስ፡ንጉሥ፡ ነኝ፡ሲል፡አገኘነው፡ብለው፡ይከሱት፡ዠመር። 3፤ጲላጦስም፦አንተ፡የአይሁድ፡ንጉሥ፡ነኽን፧ብሎ፡ጠየቀው።ርሱም፡መልሶ፦አንተ፡አልኽ፡አለው። 4፤ጲላጦስም፡ለካህናት፡አለቃዎችና፡ለሕዝቡ፦በዚህ፡ሰው፡አንድ፡በደል፡ስንኳ፡አላገኘኹበትም፡አለ። 5፤እነርሱ፡ግን፡አጽንተው፦ከገሊላ፡ዠምሮ፡እስከዚህ፡ድረስ፡በይሁዳ፡ዅሉ፡እያስተማረ፡ሕዝቡን፡ያውካል፡ አሉ። 6፤ጲላጦስ፡ግን፦ገሊላ፡ሲሉ፡በሰማ፡ጊዜ፦የገሊላ፡ሰው፡ነውን፧ብሎ፡ጠየቀ፤ 7፤ከሄሮድስም፡ግዛት፡እንደ፡ኾነ፡ባወቀ፡ጊዜ፡ወደ፡ሄሮድስ፡ሰደደው፤ርሱ፡ደግሞ፡በዚያ፡ጊዜ፡ በኢየሩሳሌም፡ነበረና። 8፤ሄሮድስም፡ኢየሱስን፡ባየው፡ጊዜ፡እጅግ፡ደስ፡አለው፤ስለ፡ርሱ፡ስለ፡ሰማ፡ከብዙ፡ጊዜ፡ዠምሮ፡ ሊያየው፡ይመኝ፡ነበርና፥ምልክትም፡ሲያደርግ፡ሊያይ፡ተስፋ፡ያደርግ፡ነበር። 9፤በብዙ፡ቃልም፡ጠየቀው፤ርሱ፡ግን፡አንድ፡ስንኳ፡አልመለሰለትም። 10፤የካህናት፡አለቃዎችና፡ጻፊዎችም፡አጽንተው፡ሲከሱት፡ቆመው፡ነበር። 11፤ሄሮድስም፡ከሰራዊቱ፡ጋራ፡ናቀው፡ዘበተበትም፥የጌጥ፡ልብስም፡አልብሶ፡ወደ፡ጲላጦስ፡መልሶ፡ሰደደው። 12፤ሄሮድስና፡ጲላጦስም፡በዚያን፡ቀን፡ርስ፡በርሳቸው፡ወዳጆች፡ኾኑ፥ቀድሞ፡በመካከላቸው፡ጥል፡ነበረና። 13፤ጲላጦስም፥የካህናትን፡አለቃዎችና፡መኳንንትን፡ሕዝቡንም፡በአንድነት፡ጠርቶ፡እንዲህ፡አላቸው። 14፤ሕዝቡን፡ያጣምማል፡ብላችኹ፡ይህን፡ሰው፡ወደ፡እኔ፡አመጣችኹት፤እንሆም፥በፊታችኹ፡መርምሬ፡ ከምትከሱበት፡ነገር፡አንድ፡በደል፡ስንኳ፡በዚህ፡ሰው፡አላገኘኹበትም። 15፤ሄሮድስም፡ደግሞ፡ምንም፡አላገኘም፤ወደ፡እኛ፡መልሶታልና፤እንሆም፥ለሞት፡የሚያደርሰው፡ምንም፡ አላደረገም፤ 16-17፤እንግዲያስ፡ቀጥቼ፡እፈታዋለኹ።በበዓሉ፡አንድ፡ይፈታላቸው፡ዘንድ፡ግድ፡ነበረና። 18፤ዅላቸውም፡በአንድነት፦ይህን፡አስወግድ፥በርባንንም፡ፍታልን፡እያሉ፡ጮኹ፤ 19፤ርሱም፡ሁከትን፡በከተማ፡አንሥቶ፡ሰውን፡ስለ፡ገደለ፡በወህኒ፡ታስሮ፡ነበር። 20፤ጲላጦስም፡ኢየሱስን፡ሊፈታ፡ወዶ፟፡ዳግመኛ፡ተናገራቸው፤ 21፤ነገር፡ግን፥እነርሱ፦ስቀለው፡ስቀለው፡እያሉ፡ይጮኹ፡ነበር። 22፤ሦስተኛም፦ምን፡ነው፧ያደረገውስ፡ክፋት፡ምንድር፡ነው፧ለሞት፡የሚያደርሰው፡በደል፡ አላገኘኹበትም፤ስለዚህ፥ቀጥቼ፡እፈታዋለኹ፡አላቸው። 23፤እነርሱ፡ግን፡እንዲሰቀል፡በታላቅ፡ድምፅ፡አጽንተው፡ለመኑት።የእነርሱ፡ጩኸትና፡የካህናት፡አለቃዎችም፡ ቃል፡በረታ። 24፤ጲላጦስም፡ልመናቸው፡እንዲኾንላቸው፡ፈረደበት። 25፤ያንን፡የለመኑትንም፥ስለ፡ሁከት፡ሰውንም፡ስለ፡መግደል፡በወህኒ፡ታስሮ፡የነበረውን፡ አስፈታላቸው፥ኢየሱስን፡ግን፡ለፈቃዳቸው፡አሳልፎ፡ሰጠው። 26፤በወሰዱትም፡ጊዜ፡ስምዖን፡የተባለ፡የቀሬናን፡ሰው፡ከገጠር፡ሲመጣ፡ይዘው፡ከኢየሱስ፡በዃላ፡መስቀሉን፡ እንዲሸከም፡ጫኑበት። 27፤ዋይ፡ዋይ፡ከሚሉና፡ሙሾ፡ከሚያወጡ፡ሴቶችና፡ከሕዝቡ፡እጅግ፡ብዙዎች፡ተከተሉት። 28-29፤ኢየሱስ፡ግን፡ወደ፡እነርሱ፡ዘወር፡ብሎ፡እንዲህ፡አለ፦እናንተ፡የኢየሩሳሌም፡ልጆች፥ለኔስ፡ አታልቅሱልኝ፤ዳሩ፡ግን፦መካኖችና፡ያልወለዱ፡ማሕፀኖች፡ያላጠቡ፡ጡቶችም፡ብፁዓን፡ናቸው፡የሚሉበት፡ ጊዜ፥እንሆ፥ይመጣልና፥ለራሳችኹና፡ለልጆቻችኹ፡አልቅሱ። 30፤በዚያን፡ጊዜ፡ተራራዎችን፦በላያችን፡ውደቁ፥ኰረብታዎችንም፦ሰውሩን፡ይሉ፡ዘንድ፡ይዠምራሉ፤ 31፤በርጥብ፡ዕንጨት፡እንዲህ፡የሚያደርጉ፡ከኾኑ፥በደረቀውስ፡እንዴት፡ይኾን፧ 32፤ሌላዎችንም፡ኹለት፡ክፉ፡አድራጊዎች፡ደግሞ፡ከርሱ፡ጋራ፡ይገድሉ፡ዘንድ፡ወሰዱ። 33፤ቀራንዮም፡ወደሚባል፡ስፍራ፡በደረሱ፡ጊዜ፥በዚያ፡ርሱን፡ክፉ፡አድራጊዎቹንም፡አንዱን፡በቀኝ፡ ኹለተኛውንም፡በግራ፡ሰቀሉ። 34፤ኢየሱስም፦አባት፡ሆይ፥የሚያደርጉትን፡አያውቁምና፡ይቅር፡በላቸው፡አለ።ልብሱንም፡ተካፍለው፡ዕጣ፡ ተጣጣሉበት። 35፤ሕዝቡም፡ቆመው፡ይመለከቱ፡ነበር።መኳንንቱም፡ደግሞ፦ሌላዎችን፡አዳነ፤ርሱ፡በእግዚአብሔር፡ የተመረጠው፡ክርስቶስ፡ከኾነ፥ራሱን፡ያድን፡እያሉ፡ያፌዙበት፡ነበር። 36፤ጭፍራዎችም፡ደግሞ፡ወደ፡ርሱ፡ቀርበው፡ሖምጣጤም፡አምጥተው፦ 37፤አንተስ፡የአይሁድ፡ንጉሥ፡ከኾንኽ፥ራስኽን፡አድን፡እያሉ፡ይዘብቱበት፡ነበር፦ 38፤ይህ፡የአይሁድ፡ንጉሥ፡ነው፡ተብሎ፡በግሪክና፡በሮማይስጥ፡በዕብራይስጥም፡ፊደል፡የተጻፈ፡ጽሕፈት፡ ደግሞ፡በርሱ፡ላይ፡ነበረ። 39፤ከተሰቀሉት፡ከክፉ፡አድራጊዎቹም፡አንዱ፦አንተስ፡ክርስቶስ፡አይደለኽምን፧ራስኽንም፡እኛንም፡አድን፡ ብሎ፡ሰደበው። 40፤ኹለተኛው፡ግን፡መልሶ፦አንተ፡እንደዚህ፡ባለ፡ፍርድ፡ሳለኽ፡እግዚአብሔርን፡ከቶ፡አትፈራውምን፧ 41፤ስላደረግነውም፡የሚገ፟ባ፟ንን፡እንቀበላለንና፡በእኛስ፡እውነተኛ፡ፍርድ፡ነው፤ይህ፡ግን፡ምንም፡ክፋት፡ አላደረገም፡ብሎ፡ገሠጸው። 42፤ኢየሱስንም፦ጌታ፡ሆይ፥በመንግሥትኽ፡በመጣኽ፡ጊዜ፡ዐስበኝ፡አለው። 43፤ኢየሱስም፦እውነት፡እልኻለኹ፥ዛሬ፡ከእኔ፡ጋራ፡በገነት፡ትኾናለኽ፡አለው።

የክርስቶስ መጨረሻ ቃሎች በመስቀል ላይ ሆኖ፣በተጨማሪ ዮሐ.ም፲፱፤ቁ.፳፮ ይመልከቱ

44፤ስድስት፡ሰዓትም፡ያኽል፡ነበረ፥ጨለማም፡እስከ፡ዘጠኝ፡ሰዓት፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ኾነ፥ፀሓይም፡ ጨለመ፥ 45፤የቤተ፡መቅደስም፡መጋረጃ፡ከመካከሉ፡ተቀደደ። 46፤ኢየሱስም፡በታላቅ፡ድምፅ፡ጮኾ፦አባት፡ሆይ፥ነፍሴን፡በእጅኽ፡ዐደራ፡እሰጣለኹ፡አለ።ይህንም፡ብሎ፡ ነፍሱን፡ሰጠ። 47፤የመቶ፡አለቃውም፡የኾነውን፡ነገር፡ባየ፡ጊዜ፦ይህ፡ሰው፡በእውነት፡ጻድቅ፡ነበረ፡ብሎ፡ እግዚአብሔርን፡አከበረ። 48፤ይህንም፡ለማየት፡ተከማችተው፡የነበሩ፡ሕዝብ፡ዅሉ፥የኾነውን፡ባዩ፡ጊዜ፥ደረታቸውን፡እየደቁ፡ ተመለሱ። 49፤የሚያውቁቱ፡ግን፡ዅሉ፡ከገሊላ፡የተከተሉት፡ሴቶችም፡ይህን፡እያዩ፡በሩቅ፡ቆመው፡ነበር። 50፤እንሆም፥በጎና፡ጻድቅ፡ሰው፡የሸንጎ፡አማካሪም፡የኾነ፡ዮሴፍ፡የሚባል፡ሰው፡ነበረ፤ 51፤ይህም፡በምክራቸውና፡በሥራቸው፡አልተባበረም፡ነበር፤አርማትያስም፡ከምትባል፡ከአይሁድ፡ከተማ፡ኾኖ፡ ርሱ፡ደግሞ፡የእግዚአብሔርን፡መንግሥት፡ይጠባበቅ፡ነበር። 52፤ይኸውም፡ወደ፡ጲላጦስ፡ቀርቦ፡የኢየሱስን፡ሥጋ፡ለመነው፤ 53፤አውርዶም፡በተልባ፡እግር፡ልብስ፡ከፈነው፥ማንም፡ገና፡ባልተቀበረበት፡ከአለትም፡በተወቀረ፡መቃብር፡ አኖረው። 54፤የመዘጋጀት፡ቀንም፡ነበረ፤ሰንበትም፡ሊዠምር፡ነበረ። 55፤ከገሊላም፡ከርሱ፡ጋራ፡የመጡት፡ሴቶች፡ተከትለው፡መቃብሩን፡ሥጋውንም፡እንዴት፡እንዳኖሩት፡አዩ። 56፤ተመልሰውም፡ሽቱና፡ቅባት፡አዘጋጁ።በሰንበትም፡እንደ፡ትእዛዙ፡ዐረፉ።

ምዕራፍ ፳፬

1፤ነገር፡ግን፥ከሳምንቱ፡በመዠመሪያው፡ቀን፡ያዘጋጁትን፡ሽቱ፡ይዘው፡ከነርሱም፡ጋራ፡አንዳንዶቹ፡ወደ፡ መቃብሩ፡እጅግ፡ማልደው፡መጡ። 2፤ድንጋዩንም፡ከመቃብሩ፡ተንከባሎ፡አገኙት፥ 3፤ገብተውም፡የጌታን፡የኢየሱስን፡ሥጋ፡አላገኙም። 4፤እነርሱም፡በዚህ፡ሲያመነቱ፥እንሆ፥ኹለት፡ሰዎች፡የሚያንጸባርቅ፡ልብስ፡ለብሰው፡ወደ፡እነርሱ፡ቀረቡ፤ 5፤ፈርተውም፡ፊታቸውን፡ወደ፡ምድር፡አቀርቅረው፡ሳሉ፥እንዲህ፡አሏቸው፦ሕያውን፡ከሙታን፡መካከል፡ ስለ፡ምን፡ትፈልጋላችኹ፧ተነሥቷል፡እንጂ፡በዚህ፡የለም። 6-7፤የሰው፡ልጅ፡በኀጢአተኛዎች፡እጅ፡ዐልፎ፡ሊሰጥና፡ሊሰቀል፡በሦስተኛውም፡ቀን፡ሊነሣ፡ግድ፡ነው፡ እያለ፡ገና፡በገሊላ፡ሳለ፡ለእናንተ፡እንደ፡ተናገረ፡ዐስቡ። 8-9፤ቃሎቹንም፡ዐሰቡ፥ከመቃብሩም፡ተመልሰው፡ይህን፡ዅሉ፡ለዐሥራ፡አንዱና፡ለሌላዎች፡ዅሉ፡ ነገሯቸው። 10፤ይህንም፡ለሐዋርያት፡የነገሯቸው፡መግደላዊት፡ማርያምና፡ዮሐና፡የያዕቆብም፡እናት፡ማርያም፡ከነርሱም፡ ጋራ፡የነበሩት፡ሌላዎች፡ሴቶች፡ነበሩ። 11፤ይህም፡ቃል፡ቅዠት፡መስሎ፡ታያቸውና፡አላመኗቸውም። 12፤ጴጥሮስ፡ግን፡ተነሥቶ፡ወደ፡መቃብር፡ሮጠ፤በዚያም፡ዝቅ፡ብሎ፡ሲመለከት፡የተልባ፡እግር፡ልብስን፡ ብቻ፡አየ፤በኾነውም፡ነገር፡እየተደነቀ፡ወደ፡ቤቱ፡ኼደ። 13፤እንሆም፥ከነርሱ፡ኹለቱ፡በዚያ፡ቀን፡ከኢየሩሳሌም፡ስድሳ፡ምዕራፍ፡ያኽል፡ወደሚርቅ፡ኤማሁስ፡ወደሚባል፡መንደር፡ይኼዱ፡ነበር፤ 14፤ስለዚህም፡ስለኾነው፡ነገር፡ዅሉ፡ርስ፡በርሳቸው፡ይነጋገሩ፡ነበር። 15፤ሲነጋገሩና፡ሲመራመሩም፥ኢየሱስ፡ራሱ፡ቀርቦ፡ከነርሱ፡ጋራ፡ይኼድ፡ነበር፤ 16፤ነገር፡ግን፥እንዳያውቁት፡ዐይናቸው፡ተይዞ፡ነበር። 17፤ርሱም፦እየጠወለጋችኹ፡ስትኼዱ፥ርስ፡በርሳችኹ፡የምትነጋገሯቸው፡እነዚህ፡ነገሮች፡ምንድር፡ ናቸው፧አላቸው። 18፤ቀለዮጳ፡የሚባልም፡አንዱ፡መልሶ፦አንተ፡በኢየሩሳሌም፡እንግዳ፡ኾነኽ፡ለብቻኽ፡ትኖራለኽን፧በእነዚህ፡ ቀኖች፡በዚያ፡የኾነውን፡ነገር፡አታውቅምን፧አለው። 19፤ርሱም፦ይህ፡ምንድር፡ነው፧አላቸው።እነርሱም፡እንዲህ፡አሉት፦በእግዚአብሔርና፡በሕዝቡ፡ዅሉ፡ ፊት፡በሥራና፡በቃል፡ብርቱ፡ነቢይ፡ስለነበረው፡ስለናዝሬቱ፡ስለ፡ኢየሱስ፤ 20፤ርሱንም፡የካህናት፡አለቃዎችና፡መኳንንቶቻችን፡ለሞት፡ፍርድ፡እንዴት፡አሳልፈው፡እንደ፡ሰጡትና፡እንደ፡ሰቀሉት፡ነው። 21፤እኛ፡ግን፡እስራኤልን፡እንዲቤዥ፡ያለው፡ርሱ፡እንደ፡ኾነ፡ተስፋ፡አድርገን፡ነበር፤ደግሞም፡ከዚህ፡ ዅሉ፡ጋራ፡ይህ፡ከኾነ፡ዛሬ፡ሦስተኛው፡ቀን፡ነው። 22፤ደግሞም፡ከእኛ፡ውስጥ፡ማልደው፡ከመቃብሩ፡ዘንድ፡የነበሩት፡አንዳንድ፡ሴቶች፡አስገረሙን፤ 23፤ሥጋውንም፡ባጡ፡ጊዜ፦ሕያው፡ነው፡የሚሉ፡የመላእክትን፡ራእይ፡ደግሞ፡አየን፡ሲሉ፡መጥተው፡ ነበር። 24፤ከእኛም፡ጋራ፡ከነበሩት፡ወደ፡መቃብር፡ኼደው፡ሴቶች፡እንደ፡ተናገሩት፡ኾኖ፡አገኙት፥ርሱን፡ግን፡ አላዩትም። 25፤ርሱም፦እናንተ፡የማታስተውሉ፥ነቢያትም፡የተናገሩትን፡ዅሉ፡ልባችኹ፡ከማመን፡የዘገየ፤ 26፤ክርስቶስ፡ይህን፡መከራ፡ይቀበል፡ዘንድና፡ወደ፡ክብሩ፡ይገባ፡ዘንድ፡ይገ፟ባ፟ው፡የለምን፧አላቸው። 27፤ከሙሴና፡ከነቢያት፡ዅሉ፡ዠምሮ፡ስለ፡ርሱ፡በመጻሕፍት፡ዅሉ፡የተጻፈውን፡ተረጐመላቸው። 28፤ወደሚኼዱበትም፡መንደር፡ቀረቡ፥ርሱም፡ሩቅ፡የሚኼድ፡መሰላቸው። 29፤እነርሱ፦ከእኛ፡ጋራ፡ዕደር፥ማታ፡ቀርቧልና፥ቀኑም፡ሊመሽ፡ዠምሯል፡ብለው፡ግድ፡አሉት፤ከነርሱም፡ ጋራ፡ሊያድር፡ገባ። 30፤ከነርሱም፡ጋራ፡በማእዱ፡ተቀምጦ፡ሳለ፡እንጀራውን፡አንሥቶ፡ባረከው፥ቈርሶም፡ሰጣቸው፤ 31፤ዐይናቸውም፡ተከፈተ፥ዐወቁትም፤ርሱም፡ከነርሱ፡ተሰወረ። 32፤ርስ፡በርሳቸውም፦በመንገድ፡ሲናገረን፡መጻሕፍትንም፡ሲከፍትልን፡ልባችን፡ይቃጠልብን፡ አልነበረምን፧ተባባሉ። 33-34፤በዚያችም፡ሰዓት፡ተነሥተው፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ተመለሱ፥ዐሥራ፡አንዱና፡ከነርሱ፡ጋራ፡ የነበሩትም፦ጌታ፡በእውነት፡ተነሥቷል፡ለስምዖንም፡ታይቷል፡እያሉ፡በአንድነት፡ተሰብስበው፡አገኟቸው። 35፤እነርሱም፡በመንገድ፡የኾነውን፡እንጀራውንም፡በቈረሰ፡ጊዜ፡እንዴት፡እንደ፡ታወቀላቸው፡ተረኩላቸው። 36፤ይህንም፡ሲነጋገሩ፡ኢየሱስ፡ራሱ፡በመካከላቸው፡ቆሞ፦ሰላም፡ለእናንተ፡ይኹን፡አላቸው። 37፤ነገር፡ግን፥ደነገጡና፡ፈሩ፡መንፈስም፡ያዩ፡መሰላቸው። 38፤ርሱም፦ስለ፡ምን፡ትደነግጣላችኹ፧ስለ፡ምንስ፡ዐሳብ፡በልባችኹ፡ይነሣል፧ 39፤እኔ፡ራሴ፡እንደ፡ኾንኹ፡እጆቼንና፡እግሮቼን፡እዩ፤በእኔ፡እንደምታዩት፥መንፈስ፡ሥጋና፡ዐጥንት፡ የለውምና፡እኔን፡ዳስሳችኹ፡እዩ፡አላቸው። 40፤ይህንም፡ብሎ፡እጆቹንና፡እግሮቹን፡አሳያቸው። 41፤እነርሱም፡ከደስታ፡የተነሣ፡ገና፡ስላላመኑ፡ሲደነቁ፡ሳሉ፦በዚህ፡አንዳች፡የሚበላ፡አላችኹን፧አላቸው። 42፤እነርሱም፡ከተጠበሰ፡ዓሣ፡አንድ፡ቍራጭ፥ከማር፡ወለላም፡ሰጡት፤ 43፤ተቀብሎም፡በፊታቸው፡በላ። 44፤ርሱም፦ከእናንተ፡ጋራ፡ሳለኹ፡በሙሴ፡ሕግና፡በነቢያት፡በመዝሙራትም፡ስለ፡እኔ፡የተጻፈው፡ዅሉ፡ ይፈጸም፡ዘንድ፡ይገ፟ባ፟ል፡ብዬ፡የነገርዃችኹ፡ቃሌ፡ይህ፡ነው፡አላቸው። 45፤በዚያን፡ጊዜም፡መጻሕፍትን፡ያስተውሉ፡ዘንድ፡አእምሯቸውን፡ከፈተላቸው፤ 46፤እንዲህም፡አላቸው፦ክርስቶስ፡መከራ፡ይቀበላል፡በሦስተኛውም፡ቀን፡ከሙታን፡ይነሣል፥ 47፤በስሙም፡ንስሓና፡የኀጢአት፡ስርየት፡ከኢየሩሳሌም፡ዠምሮ፡በአሕዛብ፡ዅሉ፡ይሰበካል፡ተብሎ፡እንዲሁ፡ተጽፏል። 48፤እናንተም፡ለዚህ፡ምስክሮች፡ናችኹ። 49፤እንሆም፥አባቴ፡የሰጠውን፡ተስፋ፡እኔ፡እልክላችዃለኹ፤እናንተ፡ግን፡ከላይ፡ኀይል፡እስክትለብሱ፡ድረስ፡ በኢየሩሳሌም፡ከተማ፡ቈዩ። 50፤እስከ፡ቢታንያም፡አወጣቸው፡እጆቹንም፡አንሥቶ፡ባረካቸው። 51፤ሲባርካቸውም፡ከነርሱ፡ተለየ፡ወደ፡ሰማይም፡ዐረገ።

የጌታችን መድኀኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ ዕርገት

52፤እነርሱም፤ሰገዱለትና፡በብዙ፡ደስታ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ተመለሱ፥ 53፤ዘወትርም፡እግዚአብሔርን፡እያመሰገኑና፡እየባረኩ፡በመቅደስ፡ኖሩ።

  1. ወንጌል አንድምታ Archived ጃንዩዌሪ 8, 2019 at the Wayback Machine ይመልከቱ
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.