ዝሆን

ዝሆንባዮሎጂ ዘመድ Elephantidaeየዝሆን አስተኔ») እንዲሁም ከክፍለመደብ Proboscideaባለ ኩምቢዎች») ብቸኛው ኗሪ አባሎች ናቸው። የዝሆን መደብ 3 የተላያዩ ኗሪ ዝርያዎችን ያቀፈ ነው። እነሱም የአፍሪካ የነጭ ሳር ዝሆንየአፍሪካ የጫካ ዝሆን (እንከ ቅርብ የአፍሪካ ዝሆን ሲባል የነበረው) እና የኤዢያ ዝሆን (ወይ የህንድ ዝሆን የሚባለው) ናቸው። ከዝሆን ጭምር አንዳንድ በጥንት የጠፉት ነባር ዝርያዎች በተለይም Mammoth ማሞጥ ወይም ቀንደ መሬት በዝሆን አስተኔ ውስጥ ተመድበዋል።

?ዝሆን
በአፍሪካ የሚገኘው የዝሆን ዝርያ በሚኩሚ ብሄራዊ ፓርክ፣ ታንዛኒያ
በአፍሪካ የሚገኘው የዝሆን ዝርያ በሚኩሚ ብሄራዊ ፓርክታንዛኒያ
ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ
ስፍን: ጉንደ እንስሳ (Animalia)
ክፍለስፍን: አምደስጌ (Chordata)
ንኡስ ክፍለስፍን: ባለ አከርካሪ (Vertebrata)
መደብ: አጥቢ (Mammalia)
ክፍለመደብ: ባለ ኩምቢ (Proboscidea)
ልእለ አስተኔ: Elephantoidea
አስተኔ: Elephantidae
Gray, 1821
ንዑስ ዘመዶች (Subfamilia)

ዝሆን ማማል (ወይም ጡት አጥቢ እንስሳ) ሲሆን፣ በምድር ከሚገኙ እንሥሣት በሙሉ ግዙፉ እንሳሳ ነው። ሴት ዝሆን ከእንስሶች በሙሉ የርግዘት ግዜት ረጅሙ ሲሆን 22 ወራት ይፈጃል። አንድ ዝሆን ሲውለድ 120 ኪ.ግ. መአከለኛ ክብደት አለው። ዝሆን እስካ 70 አመታት እድሜ ሊያስቆጥር ይችላል። እስካሁን የተመዘገበው ታላቁ ዝሆን 12 000 ኪ.ግ. ያስቆጠረ ሲሆን ርዝመቱ ደግሞ 4.2 ሜ በመድረስ ከመሀከለኛው የዝሆኖች ቁመት 1 ሜትር በላይ አስቆጥረዋል።

ዝሆኖች በሚኖሩበት ስፍራ በሰው ልጆች እንቅስቃሴ ምክኒያት እየተጎዱ መጥተው ቨ እ.አ.ኤ 1.3 ሚሊዪን ይቆጠሩ የነበሩ በ 1989 ወደ 600 000 ዝቅ በለው ተገኝተዋል። ዛሬ ከ 440 000 እስከ 660 000 ሆነው ይተመናሉ።

ባለፈው ክፍለ ዘመን በእስያ አንዳንድ ዝሆኖች በኩምቢያቸው ማለፊያ ስዕል ለመሳል በቂ አዕምሮና ሥነ ውበት እንዳላቸው አሳይተዋል። ይም በበርካታ ዩቱብ ቪዴዎች ሊታይ ይቻላል። የፈጠሩት ትርዒቶች ዝሆን፣ ዛፍ፣ አበባ፣ ሣር እና በላቲን ፊደል ፊርማቸው አለባቸው።

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.