ዛዛኪኛ

ዛዛኪኛ (Zazaki, Zazaish) በምስራቅ ቱርክ አገር በዛዛ ሕዝብ የሚናገር ቋንቋ ነው። የቱርክኛ ዘመድ ሳይሆን ከፋርስኛና ከኩርድኛ ጋር በሕንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሠብና በሕንዳዊ-ኢራናዊ ንዑስ-ቤተሠብ ውስጥ ይገኛል። በተለይ የሚመስለው በስሜን ፋርስ አገር በካስፒያን ባሕር አጠገብ የሚገኘው ጊላኪኛ ነው።

የተናጋሪዎች ቁጥር ከ1.5 እስከ 2.5 ሚሊዮን እንደሚበዛ ይታመናል።

የዛዛኪኛ 3 ቀበሌኞች የሚናገሩበት ክልል

ሦስት ዋንኛ የዛዛኪኛ ቀበሌኞች አሉ:

  • ስሜን ዛዛኪኛ
  • ማዕከለኛ ዛዛኪኛ
  • ደቡብ ዛዛኪኛ

ሥነ ጽሑፍና ማሠራጫ በዛዛኪኛ

በዛዛኪኛ መጀመርያ የተጻፉት አረፍተ ነገሮች በ1842 ዓ.ም. በቋንቋ ሊቅ ፒተር ለርች የተከመቹ ነበር። ሌላ ሁለት ቁም ነገር ሰነድች አህማደ ሐሲ1891 ዓ.ም. እና ኡስማን ኤፌንዲዮ ባብጅ1925 ዓ.ም. የጻፉት ሃይማኖታዊ ጽሑፎች (ማውሊድ) በአረብኛ ፊደል ቀረቡ።

ዛዛኪኛ በላቲን አልፋቤት መጻፍ የጀመረበት ወቅት በ1970ዎቹስዊድንፈረንሳይና በጀርመን በተበተኑት ተናጋሪዎች በኩል ነበር። ከዚህ ተከትሎ አንዳንድ መጽሔትና መጽሐፍ በቱርክ አገርና በተለይ በኢስታንቡል ይታተም ጀመር። ከዚህ የተነሣ የዛዛ ወጣቶች ለእናት ቋንቋቸው አዲስ ትኩረት ይዘዋል። ከዚህ በላይ ቱርክ በአውሮፓ ኅብረት አባልነት ለማግኘት ስታስብ በሀገሩ በሚገኙ ትንንሽ ቋንቋዎች ላይ የነበሩትን ገደቦች አነሣችላቸው። ስለዚህ አሁን በቱርክ መንግሥት ማሰራጫ ድርጅት ላይ የዛዛኪኛ ቴሌቪዥንራዲዮ መደብ በየዓርቡ ተሰጥቷል።

ቃላት ከሌሎች ልሳናት ጋር ሲነጻጸር

ዛዛኪኛኩርድኛፋርስኛቱርክኛእንግሊዝኛአማርኛ
አወ aweአቭአብsuwaterውሃ
አድር adırአጊርአታሽod / ateşfireእሳት
አማየነ amaeneሃቲንአማዳንgelmekcomeመምጣት
አርደነ ardeneአኒንአቫርዳንgetirmekbringማምጣት
አሽሚ aşmiማንግማህaymoonጨረቃ
በርማዪሽ bermayışጊሪንገርየağlamacryማልቀስ
ብራ bıraቢራባራዳርkardeşbrotherወንድም
በርዝ berzቢሊንድቦላንድyüksekhighከፍተኛ
በር berደርዳርkapıdoorበር
caቺህyerplaceቦታ
ጀኒየ ceniyeዢንዛንkadınwomanሴት
ጀዊያየነ cewiyaeneዢያንዘንደጊyaşamakliveሕይወት
ቺም çımቻቭቸሽምgözeyeዓይን
ደስት destደስትዳስትelhandእጅ
ደው deweደህköyvillageመንደር
ኤርድ erdኤርድዛሚንtoprakearthምድር
ኤስቶር estorአስፕ / አስታርአስብ / ኤስቲርathorseፈረስ
ፈክ fekደቭዳሃንağızmouthአፍ
ግርድ / ፒል gırd / pilጊር / መዚንቦዞርግbüyükgreatታላቅ
ጊሽት engışte/bêçıkeአንጎሽትኤንጉስትparmakfingerጣት
ሃክ hakሄክቶሕምyumurtaeggዕንቁላል
ሄር herከርሓርeşekdonkeyአህያ
ሂረ hirêüçthreeሦስት
ሆል hewlባሽሑብiyigoodጥሩ
ሆማ homaሖዳሖዳtanrıgodአምላክ
ሁያየነ huyaeneከኒንሐንደgülmeklaughመሳቅ
ከርደነ kerdeneኪሪንካርዳንyapmakmake, doማድረግ
ከየ keyeሐነሐነህevhouseቤት
ከይ keyከንገከይne zamanwhenመቼ
ማየ maeዳዪክማዳርannemotherእናት
ማሰ maseማሂማሂbalıkfishዓሣ
መርደነ merdeneሚሪንሞርዳንölmekdieመሞት
መርዲም merdımመርማርድerkekmanሰው
ናመ nameናቭናምad / isimnameስም
ናን nanናንናንekmekbreadዳቦ
piባቭፐዳርata / babafatherአባት
ቂጅ qıcፒቹክኩቻክküçük / ufaksmallትንሽ
ራከርደነ rakerdeneቨኪሪንባዝ ካርዳንaçmakopenመክፈት
ርንድ rındekሪንድዚባgüzelbeautifulቆንጆ
ሮጅ roceሮዥሩዝgündayቀን
ሰር serሰርሳርkafaheadራስ
ሰረ serreሳልሳልseneyearአመት
ሹንድ şanኤቫርአሥርakşameveningምሽት
ሸወ şeweሸቭሻብgecenightሌሊት
ሺያየነ şiyaeneቹንራፍታንgitmekgoመሔድ
ታርክ tariታሪክታርክkaranlıkdarkጨለማ
ተርስ tersቲርስታርስkorkufearፍርሃት
vaባድrüzgarwindንፋስ
ቫሽ vaşቢሄሽአላፍotgrassሣር
ቫተነ vateneጊቲንጎፍታንsöylemeksayማለት
ቨርግ vergጉርጎርክwolfተኩላ
ቨይሻን veyşanቢርችትዕጎሮስነጊhungryረሀብ
ቭዘር vızêrዲሮውዝዱህdünyesterdayትላንት
ዋየ waeሕዊሽክሐሃርablasisterእህት
ዋስተነ waşteneሕወስትንሐስታንistemekwantመፈለግ
ወንደነ wendeneሕዋንዲንሐንዳንokumakreadማንበብ
ወርደነ werdeneሕዋሪንሖርዳንyemekfood / eatምግብ / መብላት
ወሽ weşሕወሽሖሽhoş / latiffineደኅና
ዊን goniሕውንሑንkanbloodደም
ውሳር wesarቢሃርባሃርbaharspringምንጭ
ዋሽተ waşti / waştiyeናም-ዛድደርጊስዕsözlü / nişanlıfiancéሙሽራ
ሖዝ xozሖክሑክdomuzpigዓሣማ
ያ / ነ heya / nêኤረ / ናአረ / ናevet / hayıryes / noአዎ / አይደለም
ዝዋን zıwanዚማንዛባንdillanguageቋንቋ
ዘሪ zerriዲልደልyürekheartልብ

The language differs from most Persian dialects in that it contains archaic strains of Hurrian; it has this in common with the languages Auramani (Hawrami or Gorani) and Bajelani, and these languages are put together in the Zaza-Gorani language group, but also Goran-Zazaistan by those who want emphasize their distinctness from the Kurds.

የዛዛኪኛ ጥናት

  • Paul, Ludwig. (1998) "The Position of Zazaki Among West Iranian languages" University of Hamburg,.
  • Lynn Todd, Terry. (1985) "A Grammar of Dimili" University of Michigan, Archived ኦክቶበር 9, 2006 at the Wayback Machine.
  • Gippert, Jost. (1996) "Historical Development of Zazaki" University of Frankfurt University, Archived ጁን 21, 2006 at the Wayback Machine.
  • Gajewski, Jon. (2003) "Evidentiality in Zazaki" Massachusetts Institute of Technology, Archived ሜይ 27, 2005 at the Wayback Machine.
  • Gajewski, Jon. (2004) "Zazaki Notes" Massachusetts Institute of Technology, Archived ጁላይ 9, 2011 at the Wayback Machine.
  • Larson, Richard. and Yamakido, Hiroko. (2006) "Zazaki as Double Case-Marking" Stony Brook University and University of Arizona, Archived ሴፕቴምበር 3, 2006 at the Wayback Machine.
  • Iremet, Faruk. (1996) "The difference between Zaza, Kurdish and Turkish" Stockholm, Sweden,.

ዋቢ መጻሕፍት

  • Paul, Ladwig. (1998) The Position of Zazaki Among West Iranian languages. (Classification of Zazaki Language.)
  • Bozdağ, Cem and Üngör, Uğur. Zazas and Zazaki. (Zazaki Literature.)
  • Blau, Gurani et Zaza in R. Schmitt, ed., Compendium Linguarum Iranicarum, Wiesbaden, 1989, ISBN 3-88226-413-6, pp. 336-40 (About Daylamite origin of Zaza-Guranis)
  • Lezgîn, Roşan (2009) "Among Social Kurdish Groups – General Glance at Zazas", zazaki.net

የውጭ መያያዣዎች

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.