ዛሪቁም

ዛሪቁምኡር መንግሥት ዘመን አገረ ገዥ ነበር። ከኡር ንጉሥ ሹልጊ ፵ኛው ዓመት (1926 ዓክልበ.) ጀምሮ የሱስን ኤንሲ (ከንቲባ ወይም ገዥ) ነበረ። በተከታዩ አማር-ሲን ዘመን (1918 ዓክልበ.) የአሹር ኤንሲ ሆነ። በአማር-ሲን ፭ኛው ዓመት ግን (1914 ዓክልበ.) ዛሪቁም እንደገና የሱስን ኤንሲ ወደመሆን ተዛወረ፤ በዚያ እስከ ሹ-ሲን ፬ኛው ዓመት (1906 ዓክልበ.) ቆየ።

የአሦር ነገሥታት ዝርዝር የሚባል ሰነድ ስሙን የለውም። ከ1 ፑዙር-አሹር አስቀድሞና ምናልባት ከአኪያ ቀጥሎ እንዲሳክ ይታስባል።

ቀዳሚው
አኪያ
አሹር ኤንሲ (ለኡር መንግሥት)
1918-1914 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
1 ፑዙር-አሹር
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.