ዙዙ
ዙዙ ከሥነ ቅርስ እንደሚታወቅ ከአኒታ በኋላ በካነሽ የነገሠ ንጉሥ ነበር። ይህ ምናልባት 1637-1628 ዓክልበ. ነበር። ማዕረጉ «የአሕላዚና ታላቅ ንጉሥ» ሲሆን፣ «አሕላዚና» ምናልባት ያንጊዜ የካነሽ መንግስት ስያሜ እንደ ነበር የሚል አስተያየት አለ። ስለርሱ ዘመን ግን ብዙ አይታወቅልንም።
የተገኘው ማኅተሙ የበሬ ስዕል አለበት። በመጨረሻው በካነሽ የነበረው የአሦር መንግሥት ካሩም (የንግድ ጣቢያ) በሻላቲዋራ ንጉሥ እጅ እንደ ጠፋ ይታወቃል።
የዙዙ ዋና አለቃ ወይም ሚኒስትሩ ስም ኢሽታር-ኢብራ ተባለ። በዙዙ ቤተ መንግሥት ውስጥ «ዋናው ዋንጫ ተሸካሚ» የሚል ማዕረግ የነበረው ሰው ቱዳሊያ እንደ ተባለ ሲታወቅ፣ ምናልባት ካነሽ ከጠፋ በኋላ በኬጥያውያን መንግሥት ሰነዶች ዘንድ መሥራቹ የኬጢያውያን ንጉሥ ቱዳሊያ ይሆናል የሚል አስተሳሰብ አለ። እንዲህ ቢመስልም በታሪካዊ ሰነዶች ጉድለት ምክንያት ይህ ወቅት አሁን እርግጥኛ አይደለም።
ቀዳሚው አኒታ |
የካነሽ ንጉሥ 1637-1628 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ቱድሐሊያ ? |
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.