ዓፄ በእደ ማርያም

አጼ በእደ ማርያም፲፬፻፵ ዓ.ም ደብረ ብርሃን ከአባታቸው አጼ ዘርአ ያዕቆብና እናታቸው ጺዮን ምገሴ ተወልደው ከነሐሴ ፳፮፲፬፻፷ ዓ/ም - ኅዳር ፲፲፬፻፸ ዓ/ም የነገሡ የስሎሞናዊው ሥርወ መንግሥት አባል ናቸው። ዓፄ በእደ ማርያም፤ በተወለዱ በ ሠላሳ ዓመታቸው፤ በነገሡ በአሥር ዓመታቸው ባልታወቀ ህመም ሞቱ።

ዓፄ በእደ ማርያም
ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ
ግዛት ፲፬፻፷ - ፲፬፻፸ .
ቀዳሚ ዘርአ ያዕቆብ
ተከታይ ዓፄ እስክንድር
ባለቤት ካልዩፕ
ሥርወ-መንግሥት ሰሎሞን
አባት ዘርአ ያዕቆብ
እናት ንግሥት ጽዮን ሞገሴ
የተወለዱት 1440 ዓ.ም. ደብረ ብርሃን
የተቀበሩት አትሮንስ ማርያም
ሀይማኖት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

ንጉሠ ነገሥት በእደ ማርያም ከላንቶ ይባል የነበረውን አገር አትሮንስ ማርያም ብለው ሰይመው፣ ቤተ ክርስቲያንም አሠርተው የማርያምን ታቦት አስገቡ። በዚህም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ኒኮሎ ብራንካሌዮን በተባለ የቬኒስ ሰዓሊ የድንግል ማርያምና የሕጻኑ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስል አስለው ነበር። [1]

ማገናዘቢያ

  1. መሪራስ ኤ. ኤም በላይ፣ “የጥንቷ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ታሪክ”፣ ገጽ 249 - 257


This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.