ዑዝበክኛ

ዑዝበክኛ (O'zbek tili በ, Ўзбек тили በ) በ የሆነና የ መደበኛ ቋንቋ ነው። 18.5 ሚሊዮን ተናጋሪዎች እነርሱም የ አሉት። በዚያ ላይ ከ ከና ከ ከፍተኛ ተጽእኖ ተቀብሏል።

ታሪክ

ቢያንስ ከ600 ወይም ከ700 ዓ.ም. ጀምሮ በማእከለኛ እስያ በድሮ በተገኙ በሶግድያና ባክትርያ እና ቋራዝሚያ አገሮች የሕንዳዊ-ኢራናዊ ተናጋሪዎች በየጥቂቱ የቱርክኛ ተናጋሪዎች ተተኩ። በአካባቢው መጀመርያው የቱርክ ሥርወ መንግሥት ካራቃኒድ የተባለው ጎሣ ከ9ኛው እስከ 12ኛው ምእተ አመት ድረስ ገዝቶ ነበር።

በ15ኛው እና 16ኛ ምእተ አመት የተስፋፋ የጫጋታይ ቋንቋ የዘመናዊ ዑዝበክ ወላጅ መሆኑ ይታመናል። ይህ ቋንቋ ከፋርስኛ እና ከዓረብኛ ብዙ ቃላት ተበድሮ ሲሆን ከ19ኛው ምዕተ አመት ጀምሮ ግን በተለይ ለመነጋገርያ እንጂ ለጽሕፈት እምባዛም አይጠቀም ነበር።

1913 ዓ.ም. አስቀድሞ ዑዝበክ እና ሣርት እንደ ተለያዩ የቱርክ ቀበሌኞች ይቆጠሩ ነበር። ከ1913 ወዲህ ግን የሶቭየት መንግሥት "ሣርት" የሚለው ቃል ስድብ ነውና እንግዲህ ሁለቱ ሕዝቦች ዑዝበክ ይባሉ ብሎ ዐዋጀ። ይሁንና ቀድሞ ሣርቶች ይባል የነበሩ የዑዝበክ ትውልዶች በታሪክ ዝገባ ላይ ከቶ አልነበሩም። አዲሱ የዑዝበክ ሬፑብሊክ1917 ዓ.ም. ሲፈጠር ደግሞ ብዙ ዑዝበኮች ምንም ደስ ባይሉም ይፋዊው "ዑዝበክ" የተባለው ቋንቋ የ"ሣርቶች" ቀበሌኛ ተደርጎ ነበር። ሁለቱ ቀበሌኞች እስከ ዛሬም ድረስ ጎን ለጎን በመኖር ላይ ይገኛሉ።

ጽሕፈት

ከ1917 በፊት እንደ ሌሎቹ የማእከል እስያ ቋንቋዎች በአረብኛ ፊደል ይጻፍ ነበር። ከ1917 እስከ 1932 ዓ.ም. አዲሱ ይፋዊ ዑዝበክኛ ቋንቋ የተጻፈው በላቲን ፊደል ሲሆን ከዚያ በኋላ በስታሊን ዐዋጅ በቂርሎስ ፊደል ብቻ ሆኖ ነበር። ከ1984 ዓ.ም. ወዲህ እንደገና የላቲን ፊደል ቢፈቅድም ከቂርሎሱ ጋር አንድላይ በሰፊው በመጻፉ ላይ ይገኛል። በቻይና ውስጥ የኖሩት ዑዝበክ ሕዝቦች ግን የዓረብኛ ፊደል እስካሁን ይጠቅማቸዋል።

ምሳሌ (ከተመድ መብቶች ጽሑፍ)

ላቲንቂርሎስአጠራርአማርኛ
Barcha odamlar erkin, qadr-qimmat va huquqlarda teng bo'lib tug'iladilar. Ular aql va vijdon sohibidirlar va bir-birlari ila birodarlarcha muomala qilishlari zarur. Барча одамлар эркин, қадр-қиммат ва ҳуқуқларда тенг бўлиб туғиладилар. Улар ақл ва виждон соҳибидирлар ва бир-бирлари ила биродарларча муомала қилишлари зарур. ባርቻ ኦዳምላር ዔርኪን፣ ቃድር-ቂማት ቫ ሁቁቅላርዳ ተንግ ቦሊብ ቱጊላዲላር። ኡላር አቅል ቫ ቪዥዶን ሶሂቢዲርላር ቫ ቢር-ቢርላሪ ኢላ ቢሮዳርላርቻ ሙዎማላ ቂሊሽላሪ ዛሩር። የሰው ልጅ ሁሉ ሲወለድ ነጻና በክብርና በመብትም እኩልነት ያለው ነው። የተፈጥሮ የማስተዋልና ኅሊናው ስላለው አንዱ ሌላውን በወንድማማችነት መንፈስ መመልከት ይገባዋል።


የውጭ መያያዣዎች

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.