ውሻል

ውሻል ከቦታ ቦታ ይዘውት ሊዞሩ የሚችል ተዳፋት ነው። ዋና ጥቅሙም ሁለት እቃወችን ለመለየት ወይም አንድን እቃ ለመሰንጠቅ፣ ወይም እንደ ታኮ በማገልገል ነገሮች እንዳይንቀሳቀሱ ይረዳል። ለምሳሌ መጥረቢያ የውሻል አይነት ነው፣ ለእንጨት መሰንጠቂያ የሚያገለግሉ ሌሎች እጀታ የሌላቸው ውሻሎች አሉ። ምስማርሹካ ማንኪያም እንዲሁ የውሻል ማሽን አይነቶች ናቸው።

  • አንድ ውሻል ቁመቱ አጭርና ውፍረቱ ከፍተኛ ከሆነ፣ አንድን ተግባር በፍጥነት ለመስራት ይረዳል። ሆኖም ግን ብዙ ጉልበት ይጠይቃል።
  • ውሻሉ ቁመቱ ረዘም ብሎ ውፍረቱ ሳሳ ያለ ከሆነ፣ አንድን ተግባ ለመፈጸም ብዙ ጊዜ ሲወስድ፣ ነገር ግን አንስትኛ ጉልበት ይጠይቃል።
በውሻሉ ላይ የሚያርፈው ወደታች የሚሰርጽ ጉልበት በውሻሉ አማካይነት ለሁለት ተከፍሎ ወደ ጎን የሚሰርጹ ሁለት ጉልበቶች ይከፋፈላል

የውሻል ጥቅመ-እንቅስቃሴ እንዲህ ይሰላል፡

S ፡ እንግዲህ የውሻሉ ገጽታ ርዝመት ሲሆን T ፡ ደግሞ የውሻሉ ወፍራም ክፍል ስፋት ነው።

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.