ውሃ

ውሃ (H2O) በምድር የሚበዛ ፈሳሽ ነው።ውሀ በባህሪው ሽታ.፣ ጣዕም እና ቀለም የለውም።ሕይወት ላላቸው ከሚያስፈልጉ ንጥረነገሮች መካከል አንዱ እና ዋነኛው ሲሆን የሁለት የሀይድሮጅን እና የአንድ ኦክስጂን አጸገብሮት ውሀን ያስገኛል[1]

ውሃ
ውሃ

ውሀ የመሬትን ሰፊ ክፍል የሚሸፍን ሲሆን ወደ መጠኑም የአለምን 71% ገደማ ነው[2]። በአለም ላይ ከሚገኙ ፈሳሽ ነገሮች ሁሉ ብዙ ነገሮችን ማሟሟት ስለሚችል አለም አቀፍ አሟሚ (Universal Solvent)[3] በመባል ይታወቃል።

የውሀ ባህሪያት

ውሀን በሶስት መንገዶች የሚገኝ ሲሆን እነሱም ጠጣር፣ ፈሳሽ እና ትነት ናቸው።[4] የውሀ ነጥበ ፍሌት (Boiling Point) 100 ዲግሪ ሴልሺየስ ሲሆን ነጥበ ቅልጠት ደግሞ 0 ዲግሪ ነው።

ኡደት(Cycle)

የውሃ ኡደት ማለት በሰማይ፣ በምድር ላይ እና ከምድር በታች ያለው የማያቋርጥ የውሃ እንቅስቃሴ ማለት ነው። ውሃ እየተነነ፣ እየጤዘ፣ እየዘነበ፣ እና ከምድር ውስጥ እየሰረገ ከአንድ ክፍል ወደ ሌላው ይዘዋወራል[5]። በሚዘዋወርበትም ጊዜ ከፈሳሽነት ወደ በረዶ እና ጋዝ ይለዋወጣል። በዚህም መልክ ውሃ ሲዘዋወር ውሃው ይጣራል፣ ጨው አልባ ይሆናል፣ የተለያዩ ንጥረ ነገሮችንም ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ያመላልሳል። በተጨማሪም ድንጋይን በመሸርሸር እና አፈርና አሸዋ በማዝቀጥ የዓለምን መልክዓ ምድር ይለውጣል።



የውሃ ዑደትን መምራት እና ማንቀሳቀስ የሚጀምረው ፀሐይ ነው። የባህር እና ውቅያኖሶችን ውሃ በፀሐይ አማካኝነት ሲሞቅ. ውሃው ይተናል። በሚተንበት ጊዜ ደመናዎችን ይፈጥራል። የተነነው ውሀም በጋዝ መልክ አየር ላይ ይቀመጣል። በዚህ ጊዜ ውሃው በጋዝ ጋዝ ውስጥ አንዴ ትክክለኛዎቹ ሁኔታዎች ሲከናወኑ ይከናወናል ዝናቡ. በአየር ሙቀት ላይ በመመርኮዝ ዝናብ በጠጣር (በረዶ ወይም በረዶ) ወይም በፈሳሽ መልክ (የዝናብ ጠብታዎች) ሊሆን ይችላል።[6]

ውሃው በዝናብ አማካኝነት ወደ ከፈሰሰ በኋላ ሀይቆችን፣ ወንዞችን እና ኩሬዎችን በመፍጠር ወይም በመቀላቀል ይከማቻል።ይህ ከተከሰተ ውሃው ደመና እስኪፈጠር ድረስ እንደገና በፀሃይ ጨረር አማካኝነት ወደ ትነት ወደ ሚያወጣው ውሃ ይመራል። የሃይድሮሎጂ ዑደት በዚህ መንገድ ይዘጋል።

የውሃ ኡደት በአንድ አካባቢ ላይ የአየር ንብረት መለዋወጥ ያስከትላል።ይህም የሙቀት መጠን ከፍና ዝቅ እንዲል ያደርጋል። ለምሳሌ፦ ውሃ ሲተን ኃይል ስለሚወስድ አካባቢውን ያበርዳል።

ተያያዥ ርእሶች

  1. https://chem.libretexts.org/Courses/Pacific_Union_College/Quantum_Chemistry/10%3A_Bonding_in_Polyatomic_Molecules/10.02%3A_Hybrid_Orbitals_in_Water
  2. https://www.usgs.gov/special-topics/water-science-school/science/how-much-water-there-earth#:~:text=About%2071%20percent%20of%20the,Water%20is%20never%20sitting%20still.
  3. https://www.usgs.gov/special-topics/water-science-school/science/water-qa-why-water-universal-solvent?qt-science_center_objects=0#qt-science_center_objects
  4. https://uh.edu/~jbutler/physical/chapter6notes.html
  5. የውሃ ኡደት
  6. https://www.meteorologiaenred.com/am/%E1%88%83%E1%8B%AD%E1%8B%B5%E1%88%AE%E1%88%8E%E1%8C%82%E1%8A%AB%E1%88%8D-%E1%8B%91%E1%8B%B0%E1%89%B5.html
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.