ዋንዛ
ዋንዛ (Cordia Africana) በኢትዮጵያ እንዲሁም በአፍሪካ ሁሉ የሚበቅል ግዙፍ ዛፍ ነው። ቢጫ ፍሬው ሲበስል በጣም ጣፋጭ ነው። የፍሬው ይዘት ከላይ ለስላሳና ሙሽሽ የሚል ሲሆን መሃሉ ላይ ግን የማይቆረጠም፣ ምናልባትም ያጠቃላይ ፍሬውን 3/5ኛ የያዘ ፍሬ አለ። [1]
የዋንዛ ተጨማሪ ጥቅሞች
ሌሎች አትክልቶችን፣ ለምሳሌ እንደ ቡና ያሉትን፣ ከፀሐይ ለመከላከል ይረዳል። ጥላ መከታም ይሆናል።
ቀፎን ዛፉ ላይ በማስቀመጥ፣ ንቦችን ለማርባት በጣም አይነተኛ ዛፍ ነው፤ ምክንያቱም የዛፉ አበቦች መዓዛቸው መልካም ሲሆን መልካቸውም ዓይን ይስባል (በተለይ የንቦችን አይን)።
ግንዱም ለተለያዩ የቤት እቃ መስሪያነት ይጠቅማል፣ ለቅርጻቅጽም እንዲሁ።
በ1968 ዓም በተዘገበ በአንድ ባህላዊ እምነት፣ «የሸረሪት በሽታ» የተባለ ቆዳ ችግር በሸረሪት በእንቅልፋቸው እንደ ተፈጠረ ሲሆን፣ በዚህ እምነት የዋንዛ አመድ በቅቤ ሲቀላቀል ለሕክምናው ይሆናል።[2]
በ1998 ዓም በጥላሁን ተክለሃይማኖት በተመራ ጥናት፣ በደብረ ሊባኖስ ዙሪያ ሰዎች ለ«ምች» (ትኩሳት) ይጠቀማል። በዚህ ጥናት በተሰጠው ዝግጅት፣ የዋንዛ፣ የብሳና፣ የነጭ ባሕር ዛፍ ቅጠሎች፣ እና የዳማ ከሴ ቅጠሎችም አገዶችም፣ ተቀላቅለው በውኃ ተፈልተው እንፋሎቱ በአፍንጫና በአፍ ይተንፈሳል።[3]
ለዋንዛ ተስማሚ የሆነ አየር ጠባይና መሬት
ዋንዛ ከደጋ በስተቀር ቆላና ወይና ደጋ ተስማሚው ናቸው።
የዋንዛ አስተዳደግና እንክብካቤ
በጣም በፍጥነት ያድጋል። እስክ 30 ሜትር ይደርሳል።
- "Archive copy". Archived from the original on 2015-06-13. በ2010-06-06 የተወሰደ.
- አማራ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE Archived ጁላይ 31, 2017 at the Wayback Machine March 1976 እ.ኤ.አ.
- በደብረ ሊባኖስ ዙሪያ ያለው ሕዝብ መድሃኒታዊ እጾች እውቀናና ጥቅም 1998 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ ግርማይ መድኅን፣ ያለም መኮነን፣ አዲስ አበባ ዩኒቬርሲቴ፣ አክሊሉ ለማ ተቋም