ወንጌል

ወንጌል የሚለው ቃል (ከላቲን evangelium / ኢቫንጄሊየም, ይህም ራሱ ከጥንት የግሪክ ቃል εὐαγγέλιον / ኧውጄሊዮን = አስደሳች መልዕክት) ከሚለው የተገኘ ቃል ነው። ወንጌል ለሰው ልጆች ሁሉ የሆነ መልካም የምሥራች ነው፡፡ የንስሐ፣ የመፍትሄ፣ የሰላም፣ የፍቅር፣ የተስፋ፣ የደኅንነት፣ የእርቅ፣ ከፍርድ የመዳን፣ የዘላለም ሕይወት፣ ትምህርት የሚገኝበት ቅዱስ መጽሐፍ ነው፡፡

ወንጌል
ከ፩ሺ ዓመት በላይ ዕድሜ ያለው መጽሐፍ ቅዱስ
የመዳኛ መልዕክት
ዋና ፀሐፊዎች ቅዱስ ማርቆስ
ቅዱስ ሉቃስ
ቅዱስ ዮሐንስና
ቅዱስ ማቴዎስ 
የወንጌል ሌላ ስሙ አዲስ ኪዳን

ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር መንግስት አዋጅ የሆነውን ወንጌል ለመጀመሪያ ጊዜ እሱ ራሱ እንደሰበከ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል (ማቴ.፬፡፳፫፣ ማርቆ.፩፡፲፬-፲፭)፡፡ የወንጌል ዋነኛው መልዕክት በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የሚገኝ የኃጢአት ሥርየት ነው። ሰዎች እግዚአብሔር ቁጣ እንዲተርፉ፤ኃጢአት የሚያስከፍለውን ዋጋ ለመክፈል ማለት ከሁሉ የከፋውን ሞትን ለመሻር ክርስቶስ ቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና ተወልዶ እንደ ሰው ሆኖ መሞቱን፣ መቀበሩን፣ ከሞት መነሣቱን በፈቃደኝንት ማለትም በሰላማዊ መንገድ አምኖ ማሳመን ነው (ሐዋ.፲፫፡፳፰-፴፣፴፰። ሮሜ.፫፡፳፭-፳፮፣ 1ቆሮ.፲፭፡፫-፬)።

በተለይ የዘላለማዊ ሕይወት ዕጣዬ ምንዓይነት ነው ለሚለው ጥያቄ ወንጌል ግልፅ የሆነ መልስ ይሰጣል።

የወንጌል ዋና መልእክት

የወንጌል አንኳር መልዕክት በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የሚገኝ የኃጢአት ሥርየት ነው። የድኅነት ሥራ በክርስቶስ ተፈፅሟል የአዋጁ ዋና መልዕክት ነው (ሐዋ.፪፡፴፰፣ ፭፡፴፩፣ ፲፡፵፫፣ ፲፫፡፴፰፣ ፳፮፡፲፰) ። የድኅነት ስራ በክርስቶስ ኢየሱስ ስለተከናወነ፣ ሰዎች በእርሱ እንዲያምኑ እና የዘላለምን ህይወት እንዲያገኙ የሚነገር የምስራች ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ እንደተናገረው ወንጌል በመስቀል ላይ የተከናወነውን አስደናቂ የድኅነት ስራ የማወጅ ተግባር ነው፣ “መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ..” (፩ኛቆሮ.፲፭፡፩-፬)። የክርስቶስ ሞት እና ትንሳዔ የወንጌል ማዕከል ነው። ወንጌል ለፍጥረት ሁሉ የሚታወጅ የመስቀሉ የማዳን ሥራ ነው፣ “ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው…” (፩ኛ.ጢሞ.፩፡፲፭)። ወንጌል ሰዎች ከኃጢአታቸው ንስሃ በመግባት የበደላቸውን ስርየት እንዲቀበሉ ይናገራል፣ “..በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል” (ሉቃ.፳፬፡፵፯) ።

በወንጌል የተገኘው ደኅንነት

የሰው ልጅ በመስቀል ላይ በተሰራው የድኅነት ሥራ በማመን

  • የኃጢአት ሥርየትን ያገኛል፣
  • ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ይታረቃል፣
  • እንደ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ይሆናል፣
  • የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ መንግስት ይወርሳል
  • ከእግዚአብሔር ጋር ወደ ቀደመው የፍቅር ህብረት ይመለሳል
  • በዚህ ዓለም ሲኖር የዘላለማዊ ተስፋ ያገኛል
  • የምሥራቹን ወንጌል የማወጅ መብትና ብቃትን ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል
  • በኃጢአት ምንክንያት ከሚመጣ የእግዚአብሔር ፍርድ ይድናል

ኢየሱስ ከሰበካቸው

ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከና ዘመኑ ተፈጸመ እግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ” (ማርቆ.፩፡፲፬-፲፭)። መጽሐፍ እንደሚል “በልጁ የሚያምን የዘላለም ህይወት አለው” (ዮሐ.፫፡፴፮)። በኃጢአት ምክንያት ከሚመጣ የዘላለምም ፍርድ ያመልጣል፣ “በእርሱ የሚያምን አይፈረድበትም..”(ዮሐ.፫፡፲፰)። ይሄንን የድኸነት ወንጌል ሐዋርያትም ሰብከውታል፣ “ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ መንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ” (ሐዋ.፪፡፴፰)። የጥንት ቤተክርስቲያን አባቶችም ሰብከውታል።

ወንጌል በእስልምና

“ወንጌል” የሚለው የግሪኩ ቃል “አንጀሊኦን” εὐαγγέλιον ሲሆን “የምስራች” አሊያም “መልካም ዜና” የሚል ፍቺ አለው፣ “ኢንጂል” إنجيل የሚለው የአረቢኛው ቃል “ኢወንጀሊየን” ܐܘܢܓܠܝܘܢ ከሚለው አረማይክ ቃል አቻ ሲሆን ትርጉሙ በተመሳሳይ “የምስራች” ማለት ነው፣ “ኢንጂል” የሚለው ቃል በቁርአን 12 ጊዜ ተጠቅሶ ይገኛል፤ ይህም ወንጌል ለኢሳ የተሰጠው ወህይ ነው፦ 19:30 ሕፃኑም አለ እኔ የአላህ ባሪያ ነኝ፤ መጽሐፍም *”ሰጥቶኛል”* ነቢይም አድረጎኛል። 57:27 ከዚያም በዱካዎቻቸው ላይ መልክተኞቻችንን አስከታተልን የመርየምን ልጅ ኢሳንም አስከተልን፤ *”ኢንጅልንም ሰጠነው”*፤ 5:46 *”ኢንጂልንም”* በውስጡ ቀጥታና ብርሃን ያለበት በስተፊቱ ያለችውን ተውራትንም የሚያረጋግጥ ለጥንቁቆችም መሪና ገሣጭ ሲሆን *”ሰጠነው”*።

ኢየሱስ ከራሱ ሳይሆን የላከው የሰጠውን ቃል እንደሚናገር እንጂ ከራሱ ምንም ሳይናገር ያ የተሰጠውን ቃል ለሃዋርያት እንደሳጣቸው ይናገራል፦ ዮሐንስ 12:49 እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ *”የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ”*። ዮሐንስ 17:8 *”የሰጠኸኝን ቃል”* ሰጥቻቸዋለሁና፤ እነርሱም ተቀበሉት፥

ይህም የተሰጠው ቃል የላከው የፈጣሪ ንግግር ነው፦ ዮሐንስ 17:14 እኔ *”””ቃልህን””* ሰጥቻቸዋለሁ፤ እኔም ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም አይደሉምና ዓለም ጠላቸው።” ዮሐንስ 14:24 የማይወደኝ ቃሌን አይጠብቅም፤ የምትሰሙትም ቃል *””””የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም”””*። ዮሐንስ 7፥16 ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው። *”ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም”*፤

ምክንያቱም ኢየሱስ ሲያስተምር የነበረው ከፈጣሪ እየሰማ ነበር፦ ዮሐንስ 8.40 ነገር ግን አሁን *”ከእግዚአብሔር የሰማሁትን”* እውነት የነገርኋችሁን ሰው ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤ ዮሐንስ 8.26 ዳሩ ግን የላከኝ እውነተኛ ነው እኔም *”ከእርሱ የሰማሁትን”* ይህን ለዓለም እናገራለሁ አላቸው። ዮሐንስ 5:30 እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ *”እንደ ሰማሁ”* እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና። ዮሐንስ 15:15 ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባርያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና፤ ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ፥ *”ከአባቴ የሰማሁትን”* ሁሉ ለእናንተ አስታውቄአችኋለሁና።” ዮሐንስ 12:50 ትእዛዙም የዘላለም ሕይወት እንደ ሆነች አውቃለሁ። ስለዚህ *”እኔ የምናገረውን አብ እንደ ነገረኝ እንዲሁ እናገራለሁ”*።

እግዚአብሔር ኢየሱስ የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራልና፤ ይህም ቃል የእግዚአብሔር ወንጌል ነው፤ ሕዝቡም የሚሰሙት የእግዚአብሔር ቃል ነበረ፦ ዮሐንስ 3፥34 እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራልና፤ ሉቃስ5፥1 ሕዝቡም የእግዚአብሔርን ቃል እየሰሙ ሲያስጠብቡት ሳሉ፥ እርሱ ራሱ በጌንሳሬጥ ባሕር ዳር ቆሞ ነበር፤

“ነብይ” נָבִיא ማለት በዕብራይስጥ “ተናጋሪ” ወይም “ነጋሪ” ማለት ነው፤ ነብይ ማለት የሌላ ማንነት ንግግር ተቀብሎ የሚያስተላልፍ “አፈ-ቀላጤ” ወይም “ቃል አቀባይ” ማለት ነው፤ በዚህ ስሌት ኢየሱስ ከአምላክ ሰምቶ የሚያስተላልፍ ነብይ ነው፦ ዘኍልቍ 12:6 እርሱም። ቃሌን ስሙ፤ በመካከላችሁ *“ነቢይ”* ቢኖር፥ እኔ እግዚአብሔር “በራእይ” እገለጥለታለሁ፥ ወይም “በሕልም” እናገረዋለሁ። ማቴዎስ 21፥11 ሕዝቡም። ይህ ከገሊላ ናዝሬት የመጣ *”ነቢዩ ኢየሱስ ነው”* አሉ።” ሉቃስ 24፥19 እርሱም። ይህ ምንድር ነው? አላቸው። እነርሱም እንዲህ አሉት። *በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ስለ ነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ ነው”* ። ማርቆስ 6፥4 ኢየሱስም። *ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ዘመዶቹ ከገዛ ቤቱም በቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው*።”

ታዲያ ከፈጣሪ ተሰጦት ሲያስተላልፍ የነበረው ቃል ምንድን ነው? ካልን ወንጌል ነው፤ ኢየሱስ ሲናገረው የነበረው ወንጌል እንደነበር ይናገራል፦ ሉቃ 4:17 የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች *ወንጌልን እሰብክ* ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ሉቃ4:43 እርሱ ግን። ስለዚህ *ተልኬአለሁና ለሌሎቹ ከተማዎች ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እሰብክ ዘንድ ይገባኛል* አላቸው። ማቴዎስ 4:23 ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም *ወንጌል እየሰበከ* በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዞር ነበር። ማቴዎስ 9:35 ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው *እያስተማረ፥ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ*፥ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ፥ በከተማዎችና በመንደሮች ሁሉ ይዞር ነበር። ማርቆስ 1:14 ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን *ወንጌል እየሰበከና*። ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ *በወንጌልም እመኑ* እያለ ወደ ገሊላ መጣ።

ኢየሱስ *”በወንጌል እመኑ”* ያለው የማቴዎስን፣ የማርቆስን፣ የሉቃስን፣ እና የዮሐንስን ትረካ ሳይሆን ከአላህ እንዲናገር የተሰጠውን መልእክት ነው፤ ኢየሱስ ከፈጣሪው ተሰጦት ሲናገር የነበረውን ወንጌል እኛ ሙስሊሞች እናምንበታለን። ወንጌል የኢየሱስ ወንጌል ብቻ ነው፤ የኢየሱስ ወንጌል የሚጀምረው ማስተማር ከጀመረበት ጊዜ ነው፤ ማስተማር የጀመረው በሰላሳ አመቱ ነው፦ ማርቆስ 1፥1 *”የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ”* ማርቆስ 1:14 ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን *ወንጌል እየሰበከና*። ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ *በወንጌልም እመኑ* እያለ ወደ ገሊላ መጣ። ሉቃስ 3:23 *”ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር”* ፤

ማስታወሻ፦ “ማርቆስ 1፥1 ላይ *የእግዚአብሔር ልጅ* የሚለው የግሪኩ ቀዳማይ እደ-ክታባት ላይ የለም”

ከማስተማሩ በፊት ስለ ውልደቱ እና ተልእኮውን ከጨረሰ በኃላ ስለ እርገቱ የሚያወሩት የአራቱ ወንጌላት ክፍሎች ወንጌል ሳይሆኑ በኢየሱስ ወንጌል ላይ የተጨመሩ *”የታሪክ መዝገብ”* ወይም “የትውልድ መጽሐፍ” ነው፦ ማቴዎስ 1፥1 የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ *”የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ”* ። ሉቃ1:1-4 የከበርህ ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ከመጀመሪያው በዓይን ያዩትና የቃሉ አገልጋዮች የሆኑት *እንዳስተላለፉልን*፥ በኛ ዘንድ ስለ ተፈጸመው ነገር *”ብዙዎች ታሪክን በየተራው ለማዘጋጀት ስለ ሞከሩ”*፥ እኔ ደግሞ ስለ ተማርኸው ቃል እርግጡን እንድታውቅ በጥንቃቄ ሁሉን ከመጀመሪያው ተከትዬ በየተራው *”ልጽፍልህ መልካም ሆኖ ታየኝ”*።

አላህ ከእርሱ የወረውን ይህንን እውነት በሰው ትምህርት ቅጥፈት እንደቀላቀሉት ይናገራል፦ 3:71 የመጸሐፉ ሰዎች ሆይ! *”እዉነቱን በዉሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ?”* እውንትም እናንተ የምታወቁ ስትሆኑ ለምን ትደብቃላችሁ?

“እውነት” የተባለው ከአላህ የወረደው ቃሉ ነው፦ 34:48 ፦ጌታዬ *“እውነትን ያወርዳል”*፤ ሩቅ የኾኑትን ሚስጢሮች ሁሉ ዐዋቂ ነው በላቸው።

“ውሸት” የተባለው ደግሞ መጽሐፉን በእጆቻቸው ፅፈው “ይህ ከአላህ ዘንድ ነው” ብለው የቀጠፉት ጭማሬ ነው፦ 2:79 ለነዚያም *”መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉ እና ከዚያም በእርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው”*፡፡ ለእነርሱም ከዚያ *”እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው”*፡፡ ለእነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት ኃጢኣት ወዮላቸው፡፡

ስለዚህ ለኢየሱስ የተሰጠው የመጀመሪያው ወንጌል ከሰዎች ቃል ጋር ተበርዟል፤ ከላም የታለበ ወተት በብርጭቆ ተቀምጦ ሳለ በቡና ቢቀላቅሉት የመጀመሪያው ስረ-መሰረት ስለሌለ ሙሉ ወተት ሳይሆን ማኪያቶ ይባላል፤ ከላሟ የታለበው ወተት የት ገባ? ብትባሉ መልሳችሁ ምንድን ነው መልሳችሁ ተበርዟል ነው፤ ማክያቶ ውስጥ ወተት የለም እንዴ? ብትባሉ መልሳችሁ ምንድን ነው? በቅሪት ደረጃ አለ፤ በተመሳሳይም ከአላህ ለኢየሱስ የተሰጠው ወንጌል ሳለ በሰው ቃል ቢቀላቅሉት የመጀመሪያው ስረ-መሰረት ስለሌለ ሙሉ ወንጌል ሳይሆን ብርዝ ይባላል፤ ከአላህ ለኢየሱስ የተሰጠው ወንጌል የት ገባ? ብትባሉ መልሳችሁ ምንድን ነው? መልሳችሁ ተበርዟል ነው፤ የመጸሐፉ ሰዎች ውስጥ የወንጌል ቅሪት የለም እንዴ? ብትባሉ መልሳችሁ ምንድን ነው? በቅሪት ደረጃ አለ ነው፤ ያንን በቁርአን መዝነን እንቀበለዋለን፤ ቁርአን ያንን እነርሱ ጋር ያለውን መለኮታዊ ቅሪት ሊያረጋግጥ ወርዷል፦ 4:47 እላንተ መጽሐፉ የተሰጣችሁ ሆይ! .. *”ከእናንተ ጋር ያለውን የሚያረጋግጥ”* ኾኖ ባወረድነው ቁርአን እመኑ፣ 2:41 *”ከእናንተ ጋር ያለውን የሚያረጋግጥ”* ሆኖ ባወረድኩትም ቁርአን እመኑ፡፡

የመጽሐፉ ሰዎች ጋር ያሉት ቃላት ሙሉ ለሙሉ እውነትን ነው ብለን እንደማናምን ሁሉ ሙሉ ለሙሉ ሐሰት ነው ብለን አናምንም፤ ቁርአን ከወረደበት ግብና አላማ፣ ፋይዳና ሚና አንዱ ከእነርሱ ጋር ያለውን እውነት ለማረጋገጥና ቀጥፈው የጨመሩትን ሐሰት ሊያርም ነው፤ ከእነርሱ ጋር ያለውን እውነትን ስለሚያረጋግጥ “ሙሰዲቃን” مُصَدِّقًا “አረጋጋጭ” ሲባል፤ የሰዎች ንግግሮች የገቡበትን በማረሙ ደግሞ “ሙሃይሚን” مُهَيْمِنًا “አራሚ” correcter” ወይም “ተቆጣጣሪ”supervisor” የሚል ስም አለው፦ 5:48 ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ *”አረጋጋጭ”* እና በእርሱ ላይ *”ተጠባባቂ”* ሲሆን በእውነት አወረድን፤

ሰዎች በወንጌሉ ላይ መጨምራቸው ብቻ ሳይሆን በመደበቅ የቀነሱትም ነገር አለ፤ በ 397 AD የተደረገው የካርቴጅ ጉባኤ ብዙ የወንጌል ቅሪት አፓክራፋ ብሎ ቀንሷል፤ “አፓክራፋ” ማለት “አፓክራፎስ” ἀπόκρυφος ከሚለው የግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን “ድብቅ” “ስውር” ማለት ነው፦ 5፥15 የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! *”ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው”* ሲኾን መልክተኛችን በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ ከአላህ ዘንድ ብርሃንና ገላጭ መጽሐፍ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ 2፥146 እነዚያ መጽሐፍን የሰጠናቸው ወንዶች ልጆቻቸውን እንደሚያውቁ ያውቁታል፡፡ ከእነሱም የተለዩ ክፍሎች እነርሱ የሚያወቁ ሲኾኑ *”እውነቱን በእርግጥ ይደብቃሉ”* ፡፡

ከተደበቁት ዋናው አጀንዳ የምስራቹን የምስራች ያሰኘው ኢየሱስ ስለ ነብያችን መምጣት ማብሰሩ ነው፤ አላህ ኢንጅል የሚለው ስለ ነብያችን መምጣት የሚተነብየውን ወንጌል እንደሆነ ቅቡልና እሙን ነው፦ 61፥6 የመርየም ልጅ ዒሳም፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! እኔ ከተውራት በፊቴ ያለውን የማረጋግጥ እና *”ከእኔ በኋላ በሚመጣው መልክተኛ ስሙ አሕመድ በኾነው የማበስር”* ስኾን ወደ እናንተ የተላክሁ የአላህ መልክተኛ ነኝ» ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ በግልጽ ተዓምራቶች በመጣቸውም ጊዜ «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ፡፡ 7፥157 ለእነዚያ ያንን እነርሱ ዘንድ *”በተውራትና በኢንጂል ተጽፎ የሚያገኙትን የማይጽፍና የማያነብ ነቢይ”* የኾነውን መልክተኛ የሚከተሉ ለኾኑት በእርግጥ እጽፍለታለሁ፡፡

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.