ወላይታ
ወላይታ በቀድሞ ሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት ባሁኑ ደቡብ ክልል የሚገኝ ና የራሱ የሆነ ቋንቋና ባህል ያለው ሕዝብ ሲሆን ከሲዳማ፡ ከከምባታ፡ ከሃዲያና ተመሳሳይ ቋንቋ ከሚናገሩ ከኩሎ ኮንታ ከጎፋና ጋሞ ሕዝብ ጋር ይዋሰናል። ወላይታ ህዝቡ በጣም የተደባለቀ ሲሆን በከተማ ሆነ በገጠር አከባቢ ልቆ የሚገኝ ኃይማኖት ፕሮቴስታንት ሲሆን ኦርቶዶክስና እስልምና እምነትቶች ይገኙበታል።
የወላይታ ዞን አስራ ስድስት ወረዳዎችና ስድስት ከተማ መስተዳደሮች አሉት። እነሱም፦ 1ኛ - ዳሞት ጋሌ ዋና ከተማው ቦዲቲ፡ 2ኛ -ዳሞት ወይዴ ዋና ከተማው፦ በደሳ፡ 3ኛ -ቦሎሶ ሶሬ ዋና ከተማው አረካ፡ 4ኛ -ሁምቦ ዋና ከተማው ጠበላ፡ 5ኛ - ኦፋ ዋና ከተማው ገሱባ፡ 6ኛ- ሶዶ ዙሪያ ዋና ከተማው ሶዶ፡ 7ኛ- ኪንዶ ኮይሻ ዋና ከተማው በሌ፡ 8ኛ- ቦሎሶ ቦምበ ዋና ከተማው ቦምበ እድገት፡ 9ኛ-ዳሞት ሶሬ ዋና ከተማው ጉኑኖ፡ 10ኛ- ዱጉና ፋንጎ ዋና ከተማው ቢጣና፡ 11ኛ ዳሞት ፉላሳ ዋና ከተማው ሻንቶ፡ እና 12ኛ ኪንዶ ዲዳዬ ዋና ከተማው ሀላለ፡ ባይራ ኮይሻ ዋና ከተማው በቅሎ ሰኞ፡ ካዎ ኮይሻ ዋና ከተማው ላሾ፡ አባላ አባያ ዋና ከተማው ፋራቾ፡ ሆቢቻ ባዳ ዋና ከተማው ሆቢቻ ናቸው። ከነዚህም የከተማ መስተዳደሪነት ያገኙ ከተሞች፡ ሶዶ፤ አረካ፤ ቦዲቲ፤ ገሱባ፤ ጉኑኖ እና ጠበላ ናቸው።
ወላይታ ከደቡብ ካሉት አከባቢዎች በትምህርት፡ በልማትና በማህበራዊ ሁኔታዎች ልቆ ሊገኝበት የቻለበት ሁኔታዎች ይታያል። ይህም የሆነበት ምክንያት በቀደማዊ ኃ/ስላሴ ዘመነ መንግስት ምዕራባዊያን በብዛት ገብተው የአከባቢውን ሕዝብ ከመጽሓፍ ቅዱስ ጋር የቀለም ትምህርት አጣምረው ስለሰጡ እድሉን በመጠኑም ቢሆን በመጠቀማቸውና በየጊዜው በአከባቢው የሚመደቡ አስተዳዳሪዎች ጠንካራ በመሆናቸው ነው ይባላል።
በቀድሞ ዘመን በወላይታ በርካታ ምሁራን ብቅ ብቅ ብለው ነበር። ከነዚህም ምሁራን በደቡብ ኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው ዶክተርና የጦር ጄኔራል ለመሆኑ የበቁ ብ/ጄኔራል ዶ/ር ጋጋ ኤልጆ በአብይነት ሲጠቀሱ ፦ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ካንገት በላይ ስፔሻሊስት ዶ/ር ታዲዮስ ሙንኤ; ኢትዮጵያ ካሏት ጥቂት የፕላስቲክ ቀዶ ጥገና ባለሙያዎች አንዱ የሆኑት ዶ/ር ቀለሙ ደስታ ፡አሜሪካን አገር በዩኒቨርስቲ ኦፍ ፍሎሪዳ ታዋቂ ሓኪምና ረዳት ፕሮፌስር የሆኑ ዶ/ር ይስሓቅ ዳልኬ ናቸው። Archived ኦገስት 29, 2007 at the Wayback Machine ዶ/ር ይስሓቅ በትምህርት ውጤታቸው ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ልቀው በመገኘታቸው ከአጼ ኃይለስላሴ እጅ የወርቅ ሰዓት የተሸለሙ 2ኛው የወላይታ ተወላጅ ሲሆኑ ዳዊት ጦሼ ደግሞ የመጀመሪያው ናቸው።
የወላይታ ታሪክ ሲወሳ የወላይታ የልማት ሰው በሚል የሚታወቁ ወ/ሰማዕት ስም ሁሌም አብሮ ይወሳል። ደ/ች ወ/ሰማዕት በአስተዳዳሪነት በቆዩበት በአጼ ኃ/ስላሴ ዘመነ መንግስት ብዙ የልማት ስራዎችን አከናውነዋል። ከሰሯቸው አበይት ስራዎቻቸውም ፦
- በጊዜው የነበሩትን ሰባቱንም ወረዳዎች የሚያገናኝ መንገድ አሰርተዋል።
- በሚሲዮናዊያን አማካኝነት የመጀመሪያውን የደቡብ ሆስፒታል አስገንብተዋል።
- ወላይታን ከምዕራብ ኢትዮጵያ የሚያገናኝና 90 ሜትር ርዝመት ያለውን ታሪካዊውን የኦሞ ድልድይ አሰርተዋል።
- ወጣቱ ትርፍ ጊዜውን የሚያሳልፈበትን ወወክማ የወጣቶች መንደር ከዘመናዊ በተ-መጻሕፍት ጋር አሰርተዋል።
- በሶዶ ከተማ ዘመናዊ የገበያ አዳራሽ ከማሰራታቸው ነው።
- ከይርጋለም ቀጥሎ በደቡብ የመጀመሪያውን ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አሰርተዋል።
ደ/ች ወ/ሰማዕት በወቅቱ ማንም ወጣት የሆነ መንገድ ዳር ቆሞ ሲያወራ ካዩ ይበሳጩ እንደነበርና ከመኪናቸው ወርደው ስራ እንዲሰሩ ወይም ት/ቤት እንዲሄዱ ይመክሩም እንደነበር ይነገርላቸዋል።
ደ/ች ወ/ሰማዕት በሰብዓዊ መብት ረገድ ግን ጨቋኝ: ህዝብን የማያከብር: ግብረ-ገብነት የጎደለው ሰው ነው:: ገዥ መደብ ነኝ እያለ የወላይታ አባቶቻችን ሲያሰቃይ ነበሩ:: በ ወ/ሰማዕት ተመቶ የሞቱ ወላይታ አባቶችም እንዳሉ የ ቦጋለ ዋለሉ ቤተሠብ ይናገራሉ::
ባሁኑ ጊዜ ባገር ውስጥና ከአገር ውጭ በተሳተፉበት የሙያ ዘርፍ ሁሉ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር አንቱታን የተጎናጸፉ የወላይታ ተወላጆች ብዛት በርካታ ነው።
የውጭ መያያዣ
- በዉብ ተፈጥሮው እጅግ ብዙ ጎብኚዎች እየሳበ ያለውን የወላይታ አጆራ ፏፏቴ ለማየት ይህን ይጫኑ Archived ኦገስት 31, 2014 at the Wayback Machine
ወላይታ የኢትዮጵያ ብሔር ነው።
ዶ/ር ተመስገን ላንቴራ