ኽያን
ሰኡሰረንሬ ኽያን በጥንታዊ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን የ15ኛው ሥርወ መንግሥት (ሂክሶስ) ፈርዖን ነበር። ስሙና ሕልውናው ከበርካታ ቅርስ ይታወቃል። ከግብጽ ውጭ ስሙ በክኖሦስ፣ ቀርጤስ በክደን ላይ ከቤተመንግሥት በታች ተገኘ። እንዲሁም በደቡብ ግብጽ፣ ሐቱሳሽ ሐቲና በባቢሎን አካባቢ በመገኘቱ ንግድ ወደነዚህ አገራት እንደ ላከ ይሆናል። የእርሱ ቤተመንግሥት በቅርቡ በአቫሪስ ተገኝቷል።
ሰኡሰረንሬ ኽያን | |
---|---|
የኽያን ካርቱሽ ያለበት ቅርስ | |
የግብጽ (ሂክሶስ) ፈርዖን | |
ግዛት | 1638-1602 ዓክልበ. ግ. ? |
ቀዳሚ | አፐር-አናቲ |
ተከታይ | ሻሙቄኑ |
ሥርወ-መንግሥት | 15ኛው ሥርወ መንግሥት |
በማኔቶን ልማድ እንደ ተገለጸ፣ የሂክሶስ ሦስተኛ ንጉሥ «አፓሕናን» ይባላል፣ ለ36 ወይም በሌላ ቅጂ ለ63 ዓመታት ገዛ። እነዚህ ስሞች በዘመናት ላይ ከግብጽኛ በቅብጥኛ፣ ግሪክኛና በሌሎች ልሳናት በኩል በመተረጎማቸው ቢዛቡም፣ ይህ ሦስተኛ ሂክሶስ አለቃ «አፓኽናን» እና «ኽያን» አንድ ሊሆኑ ይቻላል። ስለዚህ በግምት ዘመኑ ምናልባት 1638-1602 ዓክልበ. ያህል ሊገኝ ይቻላል።
በዮሴፉስ ቅጂ ከአፓኽናንና ከአፖፒስ በኋላ «ያናስ» የተባለ ሂክሶስ ፈርዖን ይዘረዘራል። በሥነ ቅርስ ደግሞ በአንዱ ጽላት የኽያን ልጅ ያናሢ ይጠቀሳል። ይህ ያናሢ ምናልባት አልጋ ወራሽ ቢሆንም እንደ ፈርዖን እንደ ገዛ ግን አይመስልም።
ቀዳሚው አፐር-አናቲ |
የግብፅ (ሂክሶስ) ፈርዖን 1638-1602 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ሻሙቄኑ |
ዋቢ ምንጭ
- ስለ ኽያን በ2014 እ.ኤ.አ. የወጡት ወረቀቶች (እንግሊዝኛ)
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.