ኻና አገር

ኻና አገርኤፍራጥስ ወንዝ አካባቢ በአሁኑ ሶርያ የነበረ ግዛት ነበር። ዋና ከተማው ተርቃ ነበር።

ሃና አገር በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ;1673 ዓክልበ.

ማሪ ነገሥታት በይፋ «የማሪ፣ የቱቱል እና የኻና ግዛት ንጉሥ» ይባሉ ነበር።[1]ባቢሎን ንጉሥ ሃሙራቢ ማሪን በያዘበት ጊዜ (1673 ዓክልበ.) የማሪ መንግሥት ውድቀት ነበር፤ በኋላም በባቢሎን ንጉሥ አቢ-ኤሹህ (1627-1596 ዓክልበ.) ዘመን፣ የባቢሎን ኃይል በዚያ አቅራቢያ ደክሞ ኻና ነጻ መንግሥት ሆነ። የአንድ የኻና ንጉሱ ስም «ካሽቲሊያሹ» በኋላ (ከ1507 ዓክልበ. ጀምሮ) ባቢሎኒያን የገዙት የካሣውያን ንጉሥ ስም ካሽቲሊያሽ ይመስላል፣ ስለዚህ ምናልባት ለጊዜ ካሣውያን በኻና መንግሥት ሥልጣን እንደ ነበራቸው አንዳንዴ ይታሥባል። የካና መንግሥት የቆየው በኋላ ዘመን የሚታኒ መንግሥት ግዛት እስከሆነ ድረስ ነበር።

የኻና አገር ኗሪ ብሔሮች የበግ እረኖች ነበሩ፣ ደግሞ በመከር ወራት ግዘያዊ መንደሮችን ያቁሙ ነበር። እነዚህ በተለይ አሞራውያንየያሚና ልጆች (ብኔ ያሚና)፣ የስምኣል ልጆች (ብኔ ስምኣል)፣ እና ሃቢሩ የተባሉት ብሔሮች ወይም ጎሣዎች ናቸው። ብኔ ያሚና ወይም «የደቡብ (ቀኝ) ልጆች» ከኤፍራጥስ ደቡብና ወደ ምዕራብ ወደ ያምኻድ መንግሥት የዘረጋ ክፍል ሲሆን፣ ብኔ ስምኣል ወይም «የስሜን (ግራ) ልጆች» ከኤፍራጥስ ስሜን የተገኘው ክፍል ነው።

የኻና ወይም የተርቃ ነገሥታት

  • ኢላ-ካብካቡ (- 1745 ዓክልበ. ግድም)
  • 1 ሻምሺ-አዳድ (1745-1720 ዓክልበ. ግ.)
  • ያኽዱን-ሊም (የማሪ ንጉሥ፣ 1720-1707 ዓክልበ. ግ.)
  • ሱሙ-ያማን (የማሪ ንጉሥ፣ 1707-1705 ዓክልበ. ግ.)
  • 1 ሻምሺ-አዳድ (እንደገና በአሦር መንግሥት፣ 1705-1694 ዓክልበ. ግ.)
  • ያስማህ-አዳድ (የማሪ ንጉሥ፣ 1694-1687 ዓክልበ. ግ.)
  • ዝምሪ-ሊም (የማሪ ንጉሥ፣ 1687-1673 ዓክልበ. ግ.)
  • ያፓሕ-ሹሙ (1673-1662 ዓክልበ. ግ.)
  • ኢጺ-ሹሙ-አቡ (1662-1649 ዓክልበ. ግ.)
  • ፩ ያዲሕ-አቡ (1649-1634 ዓክልበ. ግ.)
  • ሙቲ-ሑርሻና (? 1634-1621 ዓክልበ. ግ.)
  • ካሽቲሊያሹ (የካሣውያን ንጉሥ፣ 1621-1599 ዓክልበ. ግ.)
  • የባቢሎን ነገሥታት አሚ-ዲታናአሚ-ሳዱቃሳምሱ-ዲታና ገዥነት (1596-1507 ዓክልበ. ግ.)
    • ሹኑሕሩ-አሙ - አገረ ገዥ ለባቢሎን
    • አሚ-ማዳር - አገረ ገዥ ለባቢሎን
    • 2 ያዲሕ-አቡ - አገረ ገዥ ለባቢሎን
    • ፪ ዝምሪ-ሊም - አገረ ገዥ ለባቢሎን
    • ካሳፓን / ካሳፒሊ - አገረ ገዥ ለባቢሎን
  • ኩዋሪ (1507-1503 ዓክልበ. ግ.)
  • ያኡሳ እና ሐናያ (1503-1488 ዓክልበ. ግ.)
  • ሚታኒ ገዥነት፤ ቂሽ-አዱ የሚታኒ ነገሥታት ሻውሽታታርፓራታርና አገረ ገዥ ነበር። (1488-1463 ዓክልበ. ግ.)
  • ኢዲን-ካካ (1463-1443 ዓክልበ. ግ.)
  • ኢሻር-ሊም (1443-1423 ዓክልበ. ግ.)
  • ኢጊድ-ሊም (1423-1403 ዓክልበ. ግ.)
  • ኢሺሕ-ዳጋን (1403-1383 ዓክልበ. ግ.)
  • አሁኒ (1383-1363 ዓክልበ. ግ.)
  • ሐሙራፒ (1363-1343 ዓክልበ. ግ.)
  • ፓጊሩ (1343-1323 ዓክልበ. ግ.)

ዋቢ መጻሕፍት

  1. Sollberger (1973). E. Sollberger, I.E.S. Edwards, C.J. Gadd, N.G.L. Hammond. ed. History of the Middle East and the Aegean region, c. 1800-1380 B.C. (3rd ed. ed.). London: Cambridge University Press. ISBN 978-0521082303.
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.