ኮሶ
ኮሶ (Hagenia abyssinica) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።
በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር
ባብዛኛው የደጋ ዛፍ ከ2000 ሜትር ከፍታ በላይ ይገኛል።
የተክሉ ጥቅም
መልካም ማጌጫ ዛፍ ነው።
የደረቁ ሴቴ አበቦች ከሁሉ የተጠቀመው የኮሶ ጥገኛ ትል ማስወገጃ ነው። በገበያ በሰፊ ይሸጣል። የኮሶ መጠን ብርቱ ስለሆነ እንደሰውዬው ጤና ሁናቴ መጠኑ መስተካከል ኣለበት። ከልክ በላይ መጠን ቢወሰድ ሊገድል ይችላል፣ በተደጋጋሚ ቢጠቀም ዕውርነት እንደሚፈጥር ይታሠባል።[1]
- አማረ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE Archived ጁላይ 31, 2017 at the Wayback Machine March 1976 እ.ኤ.አ.
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.