ካዛክኛ

ካዛክኛ (қазақша /ቃዛቅሻ/) በካዛክስታንና በጎረቤት አገሮች በተለይም በቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክና በሞንጎሊያ በ15 ሚሊዮን ያሕል ተናጋሪዎች የሚነገር የቱርኪክ ቋንቋዎች ቤተሠብ አባል ነው። በካዛክስታን ከ1932 ዓም እስካሁን የሚጻፈው በቂርሎስ ጽሕፈት ሲሆን በቅርቡ ወደ ላቲን ጽሕፈት ለመመለስ የሚል እቅድ አለ። በቻይና ከ1956 እስከ 1976 ዓም ድረስ በላቲን ጽሕፈት ተጽፎ ከ1976 ዓም ወዲህ በአረብኛ ጽሕፈት ተጽፏል። ይህም አረብኛ ጽሕፈት ደግሞ በቀድሞው ሶቭየት ኅብረት1919 ዓም አስቀድሞ ለካዛክኛ ይጠቀም ነበር።

ካዛክኛ በተለይ የሚነገርባቸው አገራት
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.