ካዛሉ
ካዛሉ ወይም ካዛላ በአካድኛ የጥንታዊ ከተማ ስም ነበር።
በንጉሡ ካሽቱቢላ ሥር፣ ካዛላ በአካድ ንጉሥ ታላቁ ሳርጎን ላይ ያመጽ ነበር። ሳርጎን ግን «ወደ ካዛሉ ገሥግሦ ካዛሉ የፍርስራሽ ቁልል አደረገው፣ የወፍ መሥፈሪያ ቦታ ስንኳ አልቀረም።»
በላጋሽ ንጉሥ ጉዴአ ዘመን በተቀረጸው ጽላት መሠረት፣ ካዛሉ ከመስጴጦምያ ወደ ምዕራብ በማርቱ ግዛት ይገኝ ነበር። የአሁን ሊቃውንት እንደሚያምኑ ከባቢሎን 15 ኪ/ሜ. ርቀት በኤፍራጥስ ምዕራብ ዳርቻ አካባቢ ነበር። ለአጭር ጊዜ በአሞራውያን ዘመን ካዛሉ ከጎረቤቶቹ አንዳንድ አሸንፎ ይገዛ ነበር፣ ከነዚህም ውስጥ ባቢሎን በካዛሉ ተገዛ። ባቢሎን መጀመርያ ነጻነት ያገኘው (1807 ዓክልበ.) ከካዛሉ ነበር።
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.