ካርል አዶልፍ አጋርድ

ካርል አዶልፍ አጋርድ (ጥር 23 ቀን 1785 በባስታድ፣ ስዊድን - ጥር 28 ቀን 1859 በካርልስታድ ) ስዊድናዊ የእጽዋት ተመራማሪ ሲሆን በዋቅላሚዎች ላይ በትኩረት የሰራ እና በመጨረሻም የካርልስታድ ቢሾፕ ሆኖ ተሾመ።

ካርል አዶልፍ አጋርድ
ካርል አዶልፍ አጋርድ

የተወለደው

ጥር 23 ቀን 1785 በባስታድ፣ ስዊድን

የሞተው

ጥር 28 ቀን 1859 በካርልስታድ፣ስዊድን

የሚታወቀው

በእጽዋት ሥርአተ ምደባ ሥራዎቹ፣ በተለይም ሲስቴማ አልጋረም

 

የህይወት ታሪክ

እ.ኤ.አ. በ 1807 በሉንድ ዩኒቨርሲቲ የሂሳብ መምህር እንዲሆን ተሹሞ ነበር፣ በ 1812 የእጽዋት እና የተፈጥሮ ሳይንስ ፕሮፌሰር ሆኖ ተሾመ ፣ እናም በ 1817የስዊድን ሮያል ሳይንስ አካዳሚ አባል ሆኖ ተመረጠ።

እ.ኤ.አ. በ 1816 ቄስ ሆኖ ተሹሟል ፣ ሁለት አጥቢያዎችን እንደ ቅድመሁኔታ ተቀበለ እናም ከ 1817 ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት በስዊድን ፓርላማ የቄስ ክፍል ተወካይ ነበር። እ.ኤ.አ. በ1819-1820 የሉንድ ዩኒቨርሲቲ ሬክተስ ማግኒፊከስ ነበር።በ1835 የካርልስታድ ቢሾፕ ሆኖ ተሹሞ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ቆየ[1]ካርል አዶልፍ አጋርድ የጃኮብ ጆርጅ አጋርድ አባት ፣ እንዲሁም የእጽዋት ተመራማሪ ነበር።[2]

የእፅዋት ምደባ ስርዓት

ዘ ክላስስ ፕላንታረም[3] መደቦቹ እና አስተኔዎቹ የተመደቡባቸው ዘጠኝ ዋና ክፍሎች አሉት ። እነዚህም በመደብ ቁጥር ነበሩ።

  1. አኮቲሌዶኔ 1–3 (ዋቅላሚዎች፣ የድንጋይ ሽበቶች፣ ፈንገሶች)
  2. ሱዶኮቲሌዶኔ 4–7 (ሙስቾኢዲዬ፣ ትራዲዲሜ፣ ፊሊሰስ፣ ኤኩዊሴታሲዬ)
  3. ክሪፕቶኮቲሌዶኔ 8–12 (ማክሮፖዴ፣ ስፓዲሲኔ፣ ግሉሚፍሎሬ፣ ሊሊፍሎራ፣ ጂናንዳሬ)
  4. ፋኔሮኮቲሌዶኔ ኢንኮምፕሊቴ 13–16 (ሚክራንቴ፣ ኦሌራሲዬ፣ ኤፒክላሚዲዬ፣ ኮሉምናንቲሬ)
  5. ፋኔሮኮቲሌዶኔ ኮምፕሊቴ፣ ሃይፖጋይኔ፣ ሞኖፔታሌ17 ( ቱቢፍሎሬ)
  6. ፋኔሮኮቲሌዶኔ ኮምፕሊቴ፣ ሃይፖጋይኔ፣ ፖሊፔታሌ18-22 (ሴንትሪፖሬ፣ ብሬቪስቲሌ፣ ፖሊቻርፔሌ፣ ቫልቪስፖሬ፣ ኮሉምኒስፌሬ)
  7. ፋኔሮኮቲሌዶኔ ኮምፕሊቴ፣ ዲሲጋይኔ፣ ሞኖፐታሌ 23 (ቴትራስፕርሜ)
  8. ፋኔሮኮቲሌዶኔ ኮምፕሊቴ፣ ዲሲጋይኔ፣ ፖሊፐታሌ፣24–26 (ጋይኖባዛሲዬ፣ ትሪሂሊቴ፣ ሃይፖዲቻርፔ)
  9. ፋኔሮኮቲሌዶኔ ኮምፕሊቴ፣ ፖሪጋይኔ27–33 (ሰብአግሪጋቴ፣ አሪዲፎሊዬ፣ ሰኩለንቴ፣ ካሊካንቴሜ፣ ፔፖኒፌሬ፣ ኢኮሳንድሬ፣ ሌጉሚኖሴ)

ከዚያም እያንዳንዱ መደብ በርካታ ክፍለመደቦችን (አስተኔዎችን) ይይዛል። ለምሳሌ፣ ሊሊፍሎሬ 11 ክፍለመደቦችን ይዟል፤

  • ሊሊፍሎሬ
    • 43 አስፓራጂዬ
    • 44 አስፎዲሊዬ
    • 45 ኮሮናሪዬ[lower-alpha 1]
    • 46 ቬራትሪዬ
    • 47 ኮሜሊኒዬ
    • 48 ፖንቲዴሪዬ
    • 49 ዲዮስኮሪኔ
    • 50 ሄሞዶሪዬ
    • 51 አይሪዲዬ
    • 52 ናርሲሲዬ
    • 53 ብሮሚሊያሲዬ

ህትመቶች

ለፖለቲካዊ ኤኮኖሚ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ነበር፣ እናም እንደ "ቀዳሚ ሊበራል" "በስዊድን ውስጥ የትምህርት ደረጃዎችን ማሻሻል ተሳክቶለታል" [3]በተጨማሪም በሥነ መለኮት እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ጽፏል፣ ነገር ግን ዝናው በዋናነት በእጽዋት ሥራዎቹ ላይ ያተኮረ ነው።በተለይም ሲስቴማ አልጋረም፣ ስፒሽየስ አልጋረም፣ ሪቴ ኮግኒቴ፣ ክላስስ ፕላንታረም ኦን ባዮሎጂካል ክላሲፊኬሽን[4] እና ኢኮኒስ አልጋረም (1824፣ 1820–28 እና1828-35)በተሰኙት ስራዎቹ ይታወቃል።የእጽዋት መጽሃፉ ትልቁ ክፍል (2 ጥራዝ፣ ማልሞ፣ 1829–32) ወደ ጀርመንኛ ተተርጉሟል።

መለጠፊያ:ካርል አዶልፍ አጋርድ

የተመረጡ ህትመቶች ዝርዝር

  • Algarum decas prima [-quarta] /auctore Carolo Ad. Agardh
  • Dispositio algarum Sueciae /cuctore Carolo Adolfo Agardh
  • Caroli A. Agardh Synopsis algarum Scandinaviae : adjecta dispositione universali algarum
  • Adnotationes botanicae (with Swartz, Olof, Sprengel, Kurt Polycarp Joachim, and Wikström, Joh. Em)

ዋቢ ምንጮች

  1. Eriksson, Gunnar (1970). "Agardh, Carl Adolph". Dictionary of Scientific Biography. Vol. 1. New York: Charles Scribner's Sons. pp. 69–70. ISBN 0-684-10114
  2. Ripley, George; Dana, Charles A., eds. (1879). "Agardh, Karl Adolf" . The American Cyclopædia.
  3. Gilman, D. C.; Peck, H. T.; Colby, F. M., eds. (1905). "Karl Adolph Agardh". New International Encyclopedia (1st ed.). New York: Dodd, Mead.
  4. Agardh 1825
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.