ካሞስ
ካሞስ በላይኛ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (17ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት 1563-1558 ዓክልበ. አካባቢ በሂክሶስ ዘመን የገዛ ፈርዖን ነበረ።
ካሞስ | |
---|---|
የካሞስ ሬሳ ሳትን | |
የግብጽ ፈርዖን | |
ግዛት | 1563-1558 ዓክልበ. ግ. |
ቀዳሚ | ሰቀነንሬ ታዖ |
ተከታይ | 1 አሕሞስ |
ባለቤት | 2 አሖተፕ?፣ |
ሥርወ-መንግሥት | 17ኛው ሥርወ መንግሥት |
አባት | ሰቀነንሬ ታዖ |
ካሞስ ከብዙ ቅርሶች ከነጽላቶች ይታወቃል። በአንድ ጽላት ዘንድ በኩሽ መንግሥት ላይ እንደ ዘመተ፣ ከዚያ በ፫ኛው አመት ወይም በ1560 ዓክልበ. በሂክሶስ ላይ እንደ ዘመተ ይታወቃል። ስሜን ጠረፉን ከአቫሪስ 100 ማይል እስከ ቀረበ ድረስ አሰፋው እንጂ መላውን ታችኛ ግብጽ አልማረከም። ከዚያም በኋላ እንደገና በኩሽ ላይ ዘመተ፤ ወንድሙንም 1 አሕሞስን የጋርዮሽ ፈርዖን ሆኖ ሹሞት ነበር። ይህም አሕሞስ ሂክሶስን ከግብጽ ስላባረራቸው የአዲስ መንግሥት መስራች ይባላል።
ቀዳሚው ሰቀነንሬ ታዖ |
የግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን 1563-1558 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ 1 አሕሞስ |
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.