ኪቶ
ኪቶ (Quito፣ በኦፊሴሉ San Francisco de Quito /ሳን ፍራንሲስኮ ዴ ኪቶ/) የኤኳዶር ዋና ከተማ ነው።
የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨመር 2 ሚሊዮን ሆኖ ሲገመት፣ የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ (1997 ዓ.ም.) 1.5 ሚሊዮን ሆኖ ይገመታል። ከተማው 00°14′ ደቡብ ኬክሮስ እና 78°30′ ምዕራብ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።
ከጥንት ጀምሮ ከተማ በዚህ ስፍራ ነበር። የኢንካ መንግሥት ከተማውን በ1500 ዓ.ም. ገዳማ ያዙት። ነገር ግን ስፓንያውያን በደረሱበት ጊዜ በ1525 ዓ.ም፤ እንዳይማረኩት የኢንካ አለቃ ሩሚኛዊ ከተማውን ፈጽሞ አቃጠለው። ከዚያ ስፓንያውያን በ1526 ሳን ፍራንሲስኮ ዴ ኪቶ ብለውት እንደገና ሠፈሩበት። በ1533 ዓ.ም. ሥፍራው በይፋ 'ከተማ' ተብሎ ተሰየመና ከ1555 ዓ.ም. ጀምሮ ለአውራጃው መቀመጫ ሆነ።
«ኪቶ» Guápulo de Quito
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.