ከባቢ አየር
የመሬት ከባቢ አየር በመሬት ዙሪያ የሚገኝ የጋዝ ክምችት ሲሆን እውን የሆነውም በመሬት ስበት የተነሳ ነው። ይህ የጋዝ ክምችት በተለያዩ ግዜያት የተለያዩ ይዘቶች ነበሩት። በውስጡ የሚገኙት ህይወት ላላችው ነገሮች አስፈላጊ የሆኑ ነገርችም (የኦዞን ንጣፍን ጨምሮ) በየግዜው ተለዋውዋል። ከባቢ አየራችን በውስጡ 78 በመቶ ናይትሮጅን፣ 21 በመቶ ኦክስጅን፣ 0.93 በመቶ አርገን፣ 0.038 በመቶ ካርቦን ዳይኦክሳይድ የተባሉ ንጥረ ነገሮችን (ጋዞችን) በውስጡ ይዟል። አሁን ያለው ሁኔታ መሬት ለተጨማሪ 1.5 ቢሊዮን አመታት ህይወት ያላቸው ነገሮች እንዲኖሩባት ያስችላል ተብሎ ይታመናል።
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.