የኦቶማን መንግሥት
የኦቶማን መንግሥት (ኦቶማን ቱርክኛ፦ دَوْلَتِ عَلِيّهٔ عُثمَانِیّه ዴቭሌት-ኢ አሊየ-ኢ ኦስማኒየ) ከሐምሌ ፳፮ ቀን ፲፪፻፺፩ እስከ ጥቅምት ፲፰ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓ.ም. የነበረ መንግሥት ነው። በሥልጣኑ ከፍታ በ፲፮ኛው እና ፲፯ኛው ክፍለ ዘመናት የኦቶማን መንግሥት በደቡብ ምሥራቅ ኤውሮጳ፣ ደቡብ ምዕራብ እስያና ሰሜን አፍሪቃ የሚገኙ ቦታዎችን ይቆጣጠር ነበር።
ኦቶማን ቱርኮች ቱርክኛ የሚናገሩት የኦቶማን መንግሥት ህዝቦች የነበሩ ሲሆን የመንግሥቱ ወታደራዊና የባለሥልጣን የኅብረተሰብ ክፍሎች ነበሩ።
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.