ኦስትሪያ
ኦስትሪያ (ጀርመንኛ፦ Österreich /ኦስተራይኽ/) የአውሮጳ አገር ነው።
Republik Österreich |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
ብሔራዊ መዝሙር: Land der Berge, Land am Strome |
||||||
ዋና ከተማ | ቪየና | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | ጀርመንኛ | |||||
መንግሥት ፕሬዚዳንት ቻንስለር |
ሪፐብሊክ ሃይንጽ ፊሸር ቨርነር ፋይማን |
|||||
ዋና ቀናት ሐምሌ 20 ቀን 1947 (July 27, 1955 እ.ኤ.አ.) |
የተቋቋመ |
|||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) ውሀ (%) |
83,871 (115ኛ) 1.7 |
|||||
የሕዝብ ብዛት የ2018 እ.ኤ.አ. ግምት |
8.822.267 (93ኛ) |
|||||
ገንዘብ | ዩሮ (€) | |||||
የሰዓት ክልል | UTC +1 | |||||
የስልክ መግቢያ | +43 | |||||
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ | .at |
ስም
ከ«ኦስትሪያ» በቀር የአገሩ ስያሜ በአማርኛ ደግሞ ኦትሪሽ እና ነምሳ ተብሎዋል። «ኦስትሪያ» የእንግሊዝኛ አጠራር የሚያሕል ሲሆን ከሮማይስጥ /አውስትሪያ/ የሚመጣ ነው። «ኦትሪሽ» የፈረንሳይኛ አጠራር ያንጸባርቃል፣ እሱም ደግሞ ከኗሪው ስም «ኦስተራይኽ» የመጣ ነው። የ«ኦስተራይኽ» ትርጓሜ በጀርመንኛ ማለት «ምሥራቃዊ ግዛት» ነው። ይህም የአገሩ ስም ከ988 ዓ.ም. ጀምሮ ሆኗል።
«ነምሳ» የሚለው ስያሜ ከአረብኛ «አን-ንምሳ» የደረሰ ሲሆን ይህም በድሮ ቱርክኛ «ነምጸ» በኩል ከስላቪክ ቋንቋዎች «ነምሲ» የተነሣ ነው። በስላቪክ ቋንቋዎች ግን፣ «ነምሲ» ማለት «ጀርመናዊ» ነው። የኦቶማን ቱርኮች የጠቀሙት ለጎረቤታቸው ጀርመናዊ መንግሥት ለኦስትሪያ-ሀንጋሪ ነበር። ከዚህ በላይ በመጀመርያ በስላቪክ ቋንቋዎች «ነምሲ» ማለት «ድዳ» ሲሆን በጊዜ ላይ «ስላቭኛ የማይናገር» ለማለት ስለ ሆነ የጀርመናውያን መጠሪያ ሆኖ ነበር።
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.