እሪያ
እሪያ ወይም እፘ (ሮማይስጥ፦ Sus scrofa /ሱስ ስክሮፋ/፣ ግዕዝ፦ ሕንዚር) የዐሣማ ዓይነት የሆነ አውሬ ነው። ለማዳ ዐሣማ (S. scrofa domesticus) ከዚሁ ዝርያ መጣ።
?እሪያ | ||||||||||||||
---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|
ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ | ||||||||||||||
| ||||||||||||||
Sus scrofa | ||||||||||||||
የሚገኝባቸው አገሮች በማዕከለኛ አውሮጳ፣ በሜዲቴራኔያን አካባቢ፣ በስሜን አፍሪቃ ተራሮችም፣ በእስያ እስከ ኢንዶኔዝያ ድረስ ያጠቅልላል። ዛሬ በኢትዮጵያ ባይገኝም እሪያ በአፍሪቃ ውስጥ የሚኖር የከርከሮ (Phacochoerus africanus) ዘመድ ነው። በተጨማሪ ታላቅ የጫካ እሪያ (Hylochoerus meinertzhageni) የሚባለው ጸጉራም የአሣማ አስተኔ አባል በጥቂት መጠን በኢትዮጵያ ውስጥ ይገኛል።
እሪያዎች እስከ 200 ኪሎግራም ድረስ ክብደት ሊያድጉ እርዝመታቸውም እስከ 1.8 ሜትር ድረስ ሊሆኑ ይቻላል። አደጋ ቢደርስባቸው እጅግ ጥለኛዎች ሆነው በረጅም ጥርሳቸው ጉዳት ለማድረግ ችሎታ አላቸው። ነገር ግን ይህ እምባዛም ሲደረግ አብዛኛው ጊዜ እንስት እሪያ ግልገሎችዋን አስጠብቃ ለመከላከል ሲያስፈልጋት ብቻ ይሆናል።
ከእሪያ እና ከዐሣማ መካከል ያለው ልዩነት እሪያ በጫካ ውስጥ የሚገኝ አውሬ ሲሆን ዐሣማ ግን ሰው ልጅ የለመደ ማለት ነው። ዐሳማዎችም አምልጠው ወደ ጫካ ሲመለሱ እንደገና እሪያዎች ቶሎ ይሆናሉ። የእሪያ ቆዳ ባቀመቀመ ጽጉር ይሸፈናል። አውራ እሪያ ብቻ እንደ ከርከሮ የረዠመ ጥርስ አለበት።
የእሪያ መንጋ ቁጥር በተለመደ 20 እንስሶች ያህል ሲሆን ከ50 በላይ ያሉበት ስብሰባ ታይቶ ያውቃል። በተለመደ አንድ መንጋ 2 ወይም ሦስት እንስቶችና ግልገሎቻቸው ብቻ ናቸው። አውራዎቹ በብዛት ለብቻቸው እንጂ ከመፀው መርቢያ ወራት በስተቀር በመንጋው ውስጥ አይገኙም። የሚወልዱበት ወራት ጸደይ ሲሆን በተለመደ አምስት ግልገሎች ይወለዳሉ። እስከ 13 ድረስ ግን ሲቀፈቀፉ ታውቋል።
በብዛት እርያዎች የሌሊት እንስሶች ናቸው። ከማታ እስከ ንጋቱ ድረስ መኖ አሰብስበው በሌሊትም በመዓልትም ያርፋሉ። ምክንያቱም የሚያድኑዋቸው በተለይ በቀን የሚሄዱት ናቸው። እርያዎች ያገኙትን ማንኛውንም ነገር ያሕል ለምሳሌ ለውዝ፣ እንጆሪ፣ የበሰበሰ ሥጋ፣ ስሮች፣ ቆሻሻ፣ ነፍሳት፣ እንሽላሊት የመሰሉትን ትንንሽ ፍጡሮችና የአጋዘን ወይም የበግ ግልገሎች ሳይቀር ይበላሉ።
በአንዳንድ አገር ባሕል ስጋቸው ስለሚበላ ብቻ ሳይሆን ደግሞ በነሱ ምክንያት በሰብል ወይም በእርሻ የሚደረገውን ጉዳት ለመቀነስ ነው የሚያደኑዋቸው።
በታሪካዊ ልማድ የእርያ ማደን በልዩ ጦር አይነት ይፈጸም ነበር። የተናደደው እሪያ የተወጋ ገላ በጦሩ በኩል በመግፋት አዳኙን እንዳያጠቃ በረጅም እጀታ ላይ ባሻገር የገጠመ አገዳ ክፍል ነበረበት። የአዳኞቹ ውሾች እንኳን የቆዳ ጥሩር ለብሰው ነበር።
በፋርስ የእርያ አዳኝ ሌላ ዘዴ ይጠቀሙ ነበር። ከሕንድ አገር ዝሆን አምጥተው እርያዎቹን አባርረው በረግረግ ውስጥ ይከቡዋቸው ነበር። ይህን የመሰለ ትርዒት በገደል ድንጋይ ጎን ላይ በፋርስ ተቀርጾ ይገኛል።
በግሪክና በአይርላንድ አፈታሪክ ስለ እርያ ማደን ያሉ ተረቶች አሉ። በኖርስ አረመኔ እምነት አማልክታቸው ለማዳ እሪያዎች ነበሯቸው። እንዲሁም በሕንድ እምነት የቪሽኑ ሦስተኛ ትንሳኤ እሪያ ነበር። በፋርስም ስለጉብዝናው ይከበር ነበር። ደግሞ እርያ ለእንግሊዝ ንጉስ 3 ሪቻርድ ምልክት ነበር። እሪያ የእሪያም ራስ በአውሮጳ የጋሻ ስእል ስርዐት (አርማ) ብዙ ጊዜ ይታያሉ።
ባንዳንድ አገሮች የእሪያ ጽጉር ባለፈው ዘመን ለጥርስ መፋቂያ ይጠቅም ነበር። ነገር ግን ይህ ለንጽሕና የተሻለው ነገር አልነበረም።
የውጭ መያያዣ
- የኗሪ እሪያዎች ቦታ በጀርመን ባሁኑኑ ሰዓት በወብ-ካሜራ ይታያል። Archived ማርች 31, 2007 at the Wayback Machine
- ስመ አንሰሳ በኣበራ ሞላ Archived ጃንዩዌሪ 7, 2012 at the Wayback Machine