እንስሳ
ስነ ሕይወታዊ ክፍፍሎች
በሥነ ሕይወት ጥናት ዘንድ፣ እንስሳ አንድ የሕይወት ስፍን ሲሆን 34 ክፍለስፍኖች በውስጡ ይመደባሉ። ከነዚህም መካከል፣ ብዙዎቹ ጥቃቅን ትሎች ወይም ትል መሳይ አይነቶች ናቸው።
- ሰፍነግ Porifera 7700 ዝርዮች (የባሕር እንስሳ)
- ዝርግ ቀዲም Placozoa 1 ዝርያ (የባሕር ደቂቅ ዘአካል)
- ሚዶ ማርመላታ Ctenophora 150 ዝርዮች (የባሕር እንስሳ)
- የዛጎል ድንጋይ ክፍለስፍን Cnidaria 11,000 ዝርዮች (የባሕር እንስሶች፣ ማርመላታ ዓሳ ያጠቅልላል)
- ሆድ የለሽ Xenacoelomorpha 100 ዝርዮች (የባሕር ደቂቅ ዘአካል)
- ቀጥታ ዋናተኛ Orthonectida 26 ዝርዮች (የባሕር ደቂቅ ዘአካል፤ የዛጎል ለበስ፣ የሾህ ለበስ ወይም የትል ተውሳክ ነው)
- ጥፍጥፍ ትል Platyhelminthes 25,000 ዝርዮች (የውሃ ወይም የተውሳክ ትል እንደ ኮሶ)
- ሽፋሽፍታም ትል Gastrotricha 690 ዝርዮች (የባሕር ደቂቅ ዘአካል)
- ሽክርክር እንስሳ Rotifera 2000 (የባሕር ደቂቅ ዘአካል)
- እሾህ-ራስ ትል Acanthocephala 1100 (ደቂቅ ዘአካል፣ በተለይ የሸርጣንና የሸርጣን-በል ዳክዬ ሆድ ተውሳክ)
- መንጋጭላ ትል Gnathostomulida 100 (የባሕር ደቂቅ ዘአካል)
- ጥቃቅን መንጋጭላ ትል Micrognathozoa 1 (በግሪንላንድ የተገኘ ደቂቅ ዘአካል)
- ፍላጻ ትል Chaetognatha 100 (ትንሽ የባሕር ትል)
- የጐርምጥ ተውሳክ Cycliophora 3 (በጐርምጥ አፍ ዙሪያ ተቀምጦ ትርፍ ምግቡን የሚበላ)
- ባለአንጓ ትሎች Annelida 17,000 (የባሕርና የምድር፣ አልቅት ያጠቅልላል)
- የስምንት-እግር ኩላሊት ተውሳክ Rhombozoa 100 (በስምንት-እግር ኩላሊት ውስጥ የሚገኝ)
- ጥብጣብ ትል Nemertea 1200 (የባሕር ትል)
- ኮቴ ትል Phoronida 11 (ትንሽ የባሕር እንስሳ)
- የፋኖስ ዛጎል Brachiopoda 300-500 (ትንሽ የባሕር እንስሳ)
- ዛጎል ለበስ Mollusca 112,000 (ባሕርና ምድር፤ ቀንድ አውጣ፣ ስምንት-እግር፣ ኦይስተር ወዘት.)
- ኦቾሎኒ ትል Sipuncula 144-320 (የባሕር ትል)
- ዋንጫ ትል Entoprocta 150 (የባሕር ደቂቅ ዘአካል)
- ሳርንስት እንስሳ Bryozoa 5000 (የባሕር ደቂቅ ዘአካል)
- የጭቃ ደራጎን Kinorhyncha 150 (የባሕር ወለል ደቂቅ ዘአካል)
- ጥርግ ራስ Loricifera 122 (የባሕር ወለል ደቂቅ ዘአካል)
- ቁላ ትል Priapulida 20 (የባሕር ትል)
- ጭራ ትል Nematomorpha 320 (የውሃ ትል፣ እጭ የጋጥመ-ብዙ ተውሳክ ነው)
- ድቡልቡል ትል Nematoda 25,000-1,000,000 (የትም ቦታ የሚገኝ ጥቃቅን ትል ወይም ወስፋት)
- ወላንሳ ትል Onychophora 200 (ትንሽ የምድር ትል፣ በገሞጂዎች የሚገኝ)
- የውሃ ድብ Tardigrada 1000 (ደቂቅ ዘአካል፣ በውሃ ሁሉ የሚገኝ)
- ጋጥመ-ብዙ Arthropoda 1,200,000 (ሦስት አጽቄ፣ ሸረሪት፣ አምሳ እግር፣ ሺ እግር፣ ሸርጣን፣ ጐርምጥ ወዘተ.)
- ሾህ ለበስ Echinodermata 7000 (የባሕር እንስሶች፣ ኮከብ አሳ ወዘተ.)
- የበሉጥ ዘር ትል Hemichordata 100 (የባሕር ትል)
- አምደስጌ Chordata 100,000 (ባለ አከርካሪ ሁሉ - አሳ፣ አምፊናል፣ ተሳቢ እንስሳ፣ አዕዋፍ፣ ጡት አጥቢ)
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.