እሽመ-ዳጋን (ኢሲን)
እሽመ-ዳጋን ከ1850 እስከ 1833 ዓክልበ. ግድም ድረስ (ኡልትራ አጭር አቆጣጠር) ከኢሲን ሥርወ መንግሥት የሱመር ንጉሥ ነበር። ማዕረጉ በይፋ «የኡር፣ የሱመርና የአካድ ንጉሥ» ነበረ።
የሱመር ነገሥታት ዝርዝር እሽመ-ዳጋን ለ፳ (ወይም ለ፲፰) ዓመታት እንደ ገዛ ሲለን፣ ፲፯ የዓመት ስሞች ብቻ ለእርሱ ይታወቃሉ። ስሞቹ ለአረመኔ ጣኦታቱ ሥርዓት ጌጣጌጥ ወይም ሕንጻዎች ስለ መሥራቱ ናቸው እንጂ ምንም ዘመቻ ወይም ፖለቲካዊ ጉዳይ አይዘግቡም። [1] ኢሽመ-ዳጋን ኒፑርን ከአሞራውያን ወደ ሱመር መንግሥት አስመለሰ።
ቀዳሚው ኢዲን-ዳጋን |
የኢሲንና የሱመር ንጉሥ 1850-1833 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ሊፒት-እሽታር |
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.