እስልምና


እስልምና (/ˈɪslɑːm/; አረብኛ: الإسلام, በላቲን: al-’Islām [ɪsˈlaːm] (listen),  "ለ [አምላክ]መገዛት ወይም መተናነስ ") አሀዳዊ ኢብራሂማዊ እምነት ነው, በዋናነት ቁርአንን ማእከል ያደረገ እምነት ነው , ቁርአን ሀይማኖታዊ ፅሁፍ ሲሆን በሙስሊሞች ዘንድ ከአላህ ለመሀመድ(ሰ.አ.ወ) የተገለጠ ነው ተብሎ ይታሰባል, መሀመድም ዋነኛ እና የመጨረሻ እስላማዊ ነብይ ነው.ከክርስትና እምነት በመቀጠል በአለማችን በአማኝ ብዛት በሁለተኛ ረድፍ ይመደባል; ከሁለት ቢሊየን ተከታይ በላይ ; በአለም አቀፍ ደረጃ 25ፐርሰንት ይሸፍናል።እስልምና አምላክ(አላህ)(ምስጋና ይገባው) አዛኝ, አይነተኛ, ሀያል እና የሰው ልጆችን በተላያዩ ነብያት ,ሀይማኖታዊ መፅሀፍት እና ተአምራት አማካኝነት ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራል። የመሀመድ አስተምህሮት እና ተግባራት(ሱና) ተሰብስቦ እና ተጠርዞ በሰነድ ይገኛል ይህም ሀዲስ ይባላል።ሀዲስ በሙስሊሞች ዘንድ ከቁርአን በመቀጠል ለህግ እና ለተዛማጅ አገልግሎት ይውላል።

ሙስሊሙን አሊያም ሙስሊሚን ነው ፣ ሙስሊማ አንስታይ ሲሆን የርሱ ብዙ ቁጥር ሙስሊማት ነው። ኢስላም إِسْلَٰم ደግሞ ዲኑ ሲሆን 8 ጊዜ ተወስቷል። ወጅህ وَجَّهْ ሁለንተናን አሊያም ህላዌን የሚያሳይ ሲሆን የቃል ትርጉሙ *ፊት* ማለት ነው፣ አንድ ሰው ሁለንተናውን ለአላህ ሲሰጥ ታዛዥ፣ ተገዥ፣ አምላኪ ይባላል፣ ይህ በአረቢኛ *ሙስሊም* ማለት ነው፦ [1]

2:112 እርሱ በጎ ሠሪ ኾኖ ፊቱን وَجْهَهُ ለአላህ የሰጠ أَسْلَمَ ሰው ለርሱ በጌታው ዘንድ ምንዳው አለው፡፡ በነሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነሱም አያዝኑም፡፡ 4:125 እርሱ መልካም ሰሪ ሆኖ ፊቱን وَجْهَهُ ለአላህ ከሠጠ أَسْلَمَ እና የኢብራሂምን መንገድ ቀጥተኛ ሲሆን፣ ከተከተለ ሰው፣ ይበልጥ ሃይማኖቱ ያማረ ሰው ማነው? 3:20 ቢከራከሩህም:- ፊቴን وَجْهِيَ ለአላህ ሰጠሁ أَسْلَمْتُ ፤ የተከተሉኝም ሰዎች እንደዚሁ ለአላህ ሰጡ በላቸዉ፤

የኢስላም አስኳሉ ተህሊል تهليل‎,ነው፣ ተህሊል ማለትም “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ”لا اله الاّ الله ነው፣ “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” ማለት *ከአንዱ አላህ በስተቀት ሌላ አምላክ የለም* ማለት ነው፣ “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” ሁለት ማዕዘናት አለው፣ አንዱ *ነፍይ* ሲሆን ሁለተኛው *ኢሥባት* ነው፣ ነፍይ ማለት ላ-ኢላሀ*ሌላ አምላክ የለም* ስንል ጣኦታትን ውድቅ ማድረግን ሲያመለክት ኢሥባት ደግሞ ኢልለሏህ*ከአንዱ አላህ በስተቀት* ስንል አንዱን አምላክ እያረጋገጥን ነው፣ ይህ ተህሊል *ጠንካራን ዘለበት* ይባላል፦ 31:22 እርሱ መልካም ሠሪ ሆኖ ፊቱን وَجْهَهُ ወደ አላህ የሚሰጥም يُسْلِمْ ሰው፣ ጠንካራ ገመድ بِالْعُرْوَةِ በእርግጥ ጨበጠ፤ የነገሩም ሁሉ ፍጻሜ ወደ አላህ ነው። 2:256 በጣዖትም የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት بِالْعُرْوَةِ በእርግጥ ጨበጠ፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡

ሙስሊም ማለት እንግዲህ ይህ ነው፣ አንዱን አምላክ በብቸኝነት ከሌሎች ጣኦታት ለይቶ የሚያመልክ ማለት ነው፣ በዚህ ሂሳብ ሁሉም ነቢያት ሙስሊሞች ናቸው፣ ሙስሊሞች አልነበሩም ማለት አንዱ አምላክ አያመልኩም ማለት ነው፣ ነገር ግን ቁርአን ሁሉም ነቢያት አንዱን አምላክ የሚያመልኩ ነበሩ ይለናል፦

ነጥብ አንድ ነቢያት

አላህ ጥንት ለነበሩት ነቢያት ወህይ (melekotawi raey) የሚያወርድላቸው የነበረው “ላ ኢላሃ ኢልላ አና” لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا *ከኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም* የሚል ነው፦ 21:25 ከአንተ በፊትም፣ እነሆ *ከኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም* لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا እና ተገዙኝ፣ በማለት ወደርሱ የምናወርድለት ቢሆን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም። 16:2 ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ መላእክትን ከራእይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል፤ አስጠንቅቁ፤ እነሆ *ከኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም* لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا ፍሩኝም ማለትን አሳታውቁ በማለት ያወርዳል። 20:14 እኔ አላህ እኔ ነኝ፣*ከኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም*لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا እና ተገዛኝ፤ ሶላትንም በርሷ እኔን ለማውሳት ስገድ።

ወደ ሰዎች ሲልካቸውም *ማ ለኩም ሚን ኢላሂ ገይሩሁ* مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ *ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የላችሁም* ብለው እንዲናገሩ ነው፦ 16:36 በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን ተገዙ፤ ጣዖትንም ራቁ፤ በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፤ 23:32 በውስጣቸውም ከእነሱ የኾነን መልክተኛ አላህን ተገዙ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የላችሁም مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ አትጠነቀቁምን በማለት ላክን፡፡ 7:59 ኑሕን ወደ ወገኖቹ በእርግጥ ላክነው፤ አላቸው፦ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፤ ለናንተ *ከእርሱ በቀር ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም* مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ፤ 11:50 ወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን ላክን አላቸው ፦ ወገኖቼ ሆይ አላህን ተገዙ *ከእርሱ ሌላ በቀር ምንም አምላክ የላችሁም* مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ፤ 11:61 ወደ ሠሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን፤ ፦ሕዝቦቼ ሆይ አላህን ተገዙ፤ *ከእርሱ በቀር ሌላ ለናንተ አምላክ፣ የላችሁም* مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ፤ 11:84 ወደ መድየንም ወንድማችውን ሹዐይብን፣ ላክን፤ አላቸው ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፤ *ከእርሱ በቀር ሌላ ለናንተ አምላክ የላችሁም* مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ፤

ይህን መረዳት ይዘን ሁሉም ነቢያት አንዱን አምላክ አላህን የሚያመልኩ ነበሩ በአረቢኛ ሙስሊሞች ነበሩ ማለት ነው፣ ችግራችሁ ቋንቋ ከሆነ ሙስሊም የሚለውን አማርኛው ታዛዦች ብሎ ይፈታዋል፦ 2:133 ያዕቁብን ሞት በመጣበት ጊዜ ለልጆቹ ከኔ በኋላ ማንን ትገዛላችሁ ባለ ጊዜ ቀራቢዎች ነበራችሁን? እነርሱም አምላክህንና የአባቶችህን የኢብራሂምን የኢስማዒልንና የኢስሐቅንም አምላክ አንድ የኾነውን አምላክ እኛ ለርሱ ፍፁም *ታዛዦች* مُسْلِمُونَ ኾነን እናመልካለን አሉ፡፡ 10:83 ሙሳም አለ፡-«ሕዝቦቼ ሆይ! በአላህ አምናችሁ እንደ ሆነ በርሱ ላይ ተጠጉ፡፡ *ታዛዦች* مُسْلِمِينَ እንደ ሆናችሁ በአላህ ላይ ትመካላችሁ» 3:52 ዒሳ ከነርሱ ክሕደት በተሰማዉም ጊዜ ፡-ወደ አላህ ረዳቶቼ እነማን ናቸዉ? አለ፤ ሐዋሪያት ፡ -እኛ የአላህ ረዳቶች ነን፤ በአላህም አምነናል፤ እኛም ትክክለኛ *ታዛዦች* مُسْلِمُونَ መሆናችንን፥ መስክር፥ አሉ። 5:44 እነዚያ ትእዛዝን የተቀበሉት أَسْلَمُوا ነቢያት በነዚያ ይሁዳውያን በሆኑት ላይ በርሷ ይፈርዳሉ፤

አላህ የነቢያችንን ኡማ ሙስሊሞችን ነው ብሎ የተናገረው የጥንቶቹን በተናገረበት ስሌት ነው፦ 29:46 የመጽሐፉን ባለቤቶችም በዚያች እርሷ መልካም በሆነችው ክርክር እንጂ አትከራከሩ፤ ከነሱ ነዚያን የበደሉትን ሲቀር በሉም፦ በዚያ ወደኛ በተወረደው፣ ወደናንተም በተወረደው አመንን፤ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፤ እኛም ለርሱ ታዛዦች مُسْلِمُونَ ነን። 3:84 በአላህ አመንን፤ በኛ ላይ በተወረደዉም በቁርአን በኢብራሂምና በኢስማዒልም፣ በኢስሐቅም በያዕቆብም፣ በነገዶችም ላይ በተወረደዉ፤ ለሙሳና ለዒሳም፣ ለነቢያትም ሁሉ ከጌታቸዉ በተሰጠዉ አመንን፤ ከነርሱ መካከል አንዱንም አንለይም፤ እኛ ለርሱ ታዛዦች مُسْلِمُونَ ነን፣ በል።

2:136 «በአላህና ወደኛ በተወረደው ቁርኣን ወደ ኢብራሂምም ወደ ኢስማዒልና ወደ ኢስሐቅም ወደ ያዕቁብና ወደ ነገዶቹም በተወረደው በዚያም ሙሳና ዒሳ በተሰጡት በዚያም ነቢያት ሁሉ ከጌታቸው በተሰጡት ከነርሱ በአንድም መካከል የማንለይ ስንኾን አመንን፤ እኛም ለርሱ ታዛዦች مُسْلِمُونَ ነን» በሉ፡፡ 21:108 ያ ወደኔ የሚወረደው፣ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ነው፤ ታዲያ እናንተ ፍጹም ታዛዦች مُسْلِمُونَ ናችሁን? በላቸው። 22:34 አምላካችሁም አንድ አምላህ ብቻ ነው፤ ለርሱም ብቻ ታዘዙ أَسْلِمُوا፤ ለአላህ ተዋራጆቸንም አብስራቸው። 40:66 እኔ ከጌታዬ አስረጅዎች በመጡልኝ ጊዜ እነዚያን ከአላህ ሌላ የምታመልኳቸውን እንዳላመልክ ተከልክያለሁ፤ ለዓለማት ጌታም እንድግገዛ أُسْلِمَ ታዝዣለሁ በላቸው። 6:71 «የአላህ መንገድ እርሱ ቀጥተኛው መንገድ ነው፡፡ ለዓለማት ጌታ ልንገዛም لِنُسْلِمَ ታዘዝን» በላቸው፡፡

አላህ ነቢያትን ሲልክ በማህበረሰቡ ሊግባባበት በሚችል ቋንቋ ነው፣ በራሳቸው ቋንቋ ሁሉንም ያለው *ሙስሊም* ማለትም ታዛዢዎች፣ አምላኪዎች፣ ተገዢዎች ነው፣ ሙስሊሞች አይደሉም ብሎ መቃወም አንዱን አምላክ አያመልኩም፣ ጣኦታውያን ነበሩ እንደማለት ነው፣ ስለዚህ ኢስላም በነቢያችን የተጀመረ ሳይሆን የተጠናቀቀ የአላህ ዲን ነው፦

22:78 በአላህም ሃይማኖት ተገቢውን ትግል ታገሉ; አርሱ መርጧችኃል በናንተም ላይ በሃይማኖቱ ውስጥ ምንም ችግር አላደረገባችሁም፤ የአባታችሁን የኢብራሂምን ሃይማኖት ተከተሉ፤ እርሱ ከዚህ በፊት *ሙስሊሞች* الْمُسْلِمِينَ ብሎ ሰይሟችኋል፤ 14:4 ከመልክተኛ ማንኛውንም፤ ለነርሱ ያብራራላቸው ዘንድ በወገኖቹ *ቋንቋ* እንጂ በሌላ አልላክንም፤ 30:22 ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፥ *የቋንቋዎቻችሁ* እና የመልኮቻችሁም መለያየት ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፤

ነጥብ ሁለት የነቢያት አምላክ

አላህ ጥንት ነቢያቶች የሚያመልኩት የነቢያት አምላክ መሆኑን የምናውቀው ከጥንቶቹ ነቢያት ጋር የነበረውን መስተጋብር ለመግለጽ ቁልና قُلْنَا *አልን* ፣ አርሰልና أَرْسَلْنَا*ላክን*፣ አውሃይና أَوْحَيْنَا *አወረድን* በማለት ጥንትም ነቢያትን ሲልክ የነበረው፣ ግልጠተ-መለኮት*Revelation* ሲያወርድ የነበረውና በተለያየ መንገድ ሲያናግራቸው የነበረው እርሱ መሆኑን ይገልጻል፦ 1. አልን፦ 20:116 ለመላእክትም፣ ለአዳም ስገዱ፣ *ባልን* ጊዜ አስታውስ፤ 2:35 «አደም ሆይ! አንተ ከነሚስትህ በገነት ተቀመጥ፤ ከርሷም በፈለጋችሁት ስፍራ በሰፊው ተመገቡ፤ ግን ይህችን ዛፍ አትቅረቡ፤ ከበደለኞች ትኾናላችሁና» *አልንም*፡፡

11:40 ትእዛዛችንም በመጣና እቶኑም በገነፈለ ጊዜ፣ በርሷ ውስጥ ከየዓይነቱ ሁሉ ሁለት ሁለት፣ ወንድና ሴት ቤተሰቦችህንም ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር ያመነንም ሰው ሁሉ ጫን *አልነው*፤ 22:26 ለኢብራሂምም የቤቱን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ፣ በኔ ምንንም አታጋራ፤ ቤቴንም፣ ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት፣ ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው፣ *ባልነው* ጊዜ አስታውስ።

2:125 ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም ቤቴን ለዘዋሪዎቹና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ *ስንል* ቃል ኪዳን ያዝን፡፡ 2:60 ሙሳም ለሕዝቦቹ መጠጥን በፈለገ ጊዜ የኾነውን አስታውሱ፡፡ «ድንጋዩንም በበትርህ ምታ» *አልነው*፡፡ 17:2 ሙሳንም መጽሐፉን ሰጠነው፤ ለእስራኤልም ልጆች መሪ አደረግነው፤ ከኔ ሌላ መጠጊያን አትያዙ *አልናቸውም*።

2. ላክን፦

16:36 በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን ተገዙ፤ ጣዖትንም ራቁ፤ በማለት መልክተኛን በእርግጥ *ልከናል*፤ 57:25 መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ *ላክን*፤

23:32 በውስጣቸውም ከእነሱ የኾነን መልክተኛ አላህን ተገዙ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የላችሁም አትጠነቀቁምን በማለት *ላክን*፡፡ 7:59 ኑሕን ወደ ወገኖቹ በእርግጥ ላክነው፤ 11:50 ወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን ላክን፤ 11:61 ወደ ሠሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን፤ 11:84 ወደ መድየንም ወንድማችውን ሹዐይብን፣ ላክን፤

3. አወረድን፦

4:163 እኛ ወደ ኑሕና ከርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት *እንዳወረድን*፣ ወደ አንተም *አወረድን*፤ ወደ ኢብራሂምም፣ ወደ ኢስማዒልም፣ ወደ ኢስሐቅም፣ ወደ ያዕቆብም፣ ወደ ነገዶቹም ወደ ዒሳም፣ ወደ አዮብም፣ ወደ ዩኑስም፣ ወደ ሀሩንና ወደ ሱለይማንም *አወረድን*፤ ለዳዉድም ዘቡርን ሰጠነው። 21:25 ከአንተ በፊትም፣ እነሆ ከኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ፣ በማለት ወደርሱ *የምናወርድለት* ቢሆን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም።

12:109 ካንተ በፊትም ከከተሞች ሰዎች ወደ እነርሱ ራዕይ *የምናወርድላቸው* የሆኑን ወንዶችን እንጂ አልላክንም፤ 21:7 ከአንተም በፊት ወደ እነርሱ *የምናወርድላቸው* የኾኑ ሰዎችን እንጂ ሌላን አልላክንም፤ 16:43 ከአንተም በፊት ወደ እነርሱ ወሕይን *የምናወርድላቸውን* ሰዎችን እንጂ፣ ሌላን አልላክንም፤

የኢስላም መሰረቶች

አርካኑል ኢስላም أركان الإسلام *የኢስላም መሰረቶች* አምስት ናቸው፣ እነዚህም፦ ሸሃዳ الشهادة‎፣ ሶላት صلاة‎ ፣ ሰውምصوم‎ ፣ ዘካزكاة እና ሃጅ حج ናቸው። ሰሂህ ቡሃሪ ቅጽ 1, መጽሃፍ 2, ቁጥር 8: ይመልከቱ፦

حَدَّثَنَا عُبَيْدُ اللَّهِ بْنُ مُوسَى، قَالَ أَخْبَرَنَا حَنْظَلَةُ بْنُ أَبِي سُفْيَانَ، عَنْ عِكْرِمَةَ بْنِ خَالِدٍ، عَنِ ابْنِ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ بُنِيَ الإِسْلاَمُ عَلَى خَمْسٍ شَهَادَةِ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ، وَإِقَامِ الصَّلاَةِ، وَإِيتَاءِ الزَّكَاةِ، وَالْحَجِّ، وَصَوْمِ رَمَضَانَ

ኢስላም የነቢያት ሃይማኖት ከሆነ ነቢያችን የመሰረቱት ሳይሆን ከጥንት ነቢያት የመጣ አስተምህሮት ነው፣ እነዚህን የኢስላም መሰረቶች የጥንቶቹ ነቢያት ድርጊት መሆኑን አንድ በአንድ እንመልከት፦

1.ሸሃዳ

ሸሃዳ الشهادةምስክርነት ሲሆን ከአላህ በቀር አምላክ አለመኖሩን በቀውል የሚደረግ የኢባዳ ክፍል ነው፣ ይህንን ምስክርነት ሰዎች በእያንዳንዱ ነብይ ዘመን በዘመኑ የነበረውን ነብይ መልእክተኛ አድርገው ይቀበላሉ፦ 23:32 በውስጣቸውም ከእነሱ የኾነን መልክተኛ አላህን ተገዙ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የላችሁም مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ አትጠነቀቁምን በማለት ላክን፡፡

7:59 ኑሕን ወደ ወገኖቹ በእርግጥ ላክነው፤ አላቸው፦ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፤ ለናንተ *ከእርሱ በቀር ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም* مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ፤ 11:50 ወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን ላክን አላቸው ፦ ወገኖቼ ሆይ አላህን ተገዙ *ከእርሱ ሌላ በቀር ምንም አምላክ የላችሁም* مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ፤ 11:61 ወደ ሠሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን፤ ፦ሕዝቦቼ ሆይ አላህን ተገዙ፤ *ከእርሱ በቀር ሌላ ለናንተ አምላክ፣ የላችሁም* مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ፤

11:84 ወደ መድየንም ወንድማችውን ሹዐይብን፣ ላክን፤ አላቸው ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፤ *ከእርሱ በቀር ሌላ ለናንተ አምላክ የላችሁም* مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ፤ 7:61 አላቸው ፦ ወገኖቼ ሆይ! ምንም መሳሳት የለብኝም፤ ግን እኔ ከዓለማት ጌታ *መልክተኛ* ነኝ። 7:67 አላቸው፦ወገኖቼ ሆይ! እኔ ሞኝነት የለብኝም፤ ግን እኔ ከዓለማት ጌታ *የተላክሁ* ነኝ፤

61:5 ሙሳም ለሕዝቦቹ ሕዝቦቼ ሆይ! እኔ ወደ እናንተ *የአላህ መልክተኛ* መሆኔን በእርግጥ የምታውቁ ስትሆኡ ለምን ታሰቃዩኛላችሁ?

61:6 የመርየም ልጅ ዒሳም የ እስራኤል ልጆች ሆይ እኔ ከተውራት በፊቴ ያለውን የማረጋግጥና ከኔ በኋላ በሚመጣው መልክተኛ ስሙ አሕመድ በሆነው የማበስር ስሆን ወደናንተ የተላክሁ *የአላህ መልክተኛ* ነኝ ባለ ጊዜ አስታውስ፤

በተመሳሳይ መልኩ አላህ ለነቢያችን *እርሱ እንጂ ሌላ አምላክ የለም* *የአላህ መልክተኛ* ነኝ በል ብሏቸዋል፦

9:129 ቢያፈገፍጉም አላህ በቂዬ ነው፤ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ፤ በርሱ ላይ ተጠጋሁ፤ እርሱም የታላቁ ዐርሽ ጌታ ነው በላቸው።

7:158 በላቸው፦እላንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ወደ እናንተ ወደሁላችሁም *የአላህ መልክተኛ* ነኝ፤ ያ የሰማይና የምድር ንግስና ለርሱ ብቻ የሆነ ነው፤ ከእርሱ በቀር ሌላ ሌላ አምላክ የለም لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ፤

በአላህና በመልክተኞቹም አምኖ ምስክርነት መስጠት የኢስላም ማዕዘን ነው፣ ለዛ ነው *ከአላህ በቀር አምላክ የለም ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ ነው* لا إله إلا الله محمد رسول الله ብለን የምንመሰክረው፦

3:179 ግን አላህ ከመልክተኞቹ የሚሻዉን ይመርጣል፤ በአላህና በመልክተኞቹም እመኑ።

57:7 በአላህና በመልክተኛው እመኑ፤

63:1 መናፍቃን በመጡህ ጊዜ አንተ የአላህ መልክተኛው መሆንህን በእርግጥ *እንመሰክራለን* ይላሉ፤

2. ሶላት

ሶላት صلاة‎ *ጸሎት* ከኢስላም መሰረቶች አንዱ ነው፣ ሁሉም ነቢያት ሶላት ነበራቸው ምናልባት ይዘቱ ይለያይ ይሆናል፣ በቀን አምስት ጊዜ ላይሆን ይችል ይሆናል እንጂ ሶላት ከነቢያችን በፊት በነበሩት ነቢያት ነበር፦

21:73 በትእዛዛችንም፣ ወደ በጎ ሥራ የሚመሩ፣ መሪዎች አደረግናቸው፤ ወደነሱም መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትን الصَّلَاةِ መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን፣ አወረድን፤ ለኛ ተገዢዎችም ነበሩ።

20:14 እኔ አላህ እኔ ነኝ፣ ያለ እኔ አምላክ የለምና ተገዛኝ፤ ሶላትንም الصَّلَاةَ በርሷ እኔን ለማውሳት ስገድ።

14:37 ጌታችን ሆይ! እኔ አዝመራ በሌለው ሸለቆ ውስጥ በተከበረው ቤት አጠገብ ከዘሮቼ አስቀመጥሁ፤ ጌታችን ሆይ! ሶላትን الصَّلَاةَ ያቋቁሙ ዘንድ አስቀመጥኳቸው፤ ከሰዎችም ልቦችን ወደነሱ የሚናፍቁ አድርግ፤ ያመሰግኑህም ዘንድ ከፍሬዎች ስጣቸው፤

14:40 ጌታዬ ሆይ! ሶላትን الصَّلَاةِ አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ፤ ከዘሮቼም አድርግ፤ ጌታችን ሆይ ጸሎቴን ተቀበለኝ፤

20:132 ቤተሰብህንም በስግደት እዘዝ፤ በርሷም ላይ ዘውትር፤ ሲሳይን አንጠይቅህም፤ እኛ እንሰጥሃለን መልካሚቱ መጨረሻም ለጥንቁቆቹ ናት።

19:31 በየትም ስፍራ ብኾን ብሩክ አድርጎኛል፤ በሕይወትም እስከ አለዉ ሶላትን بِالصَّلَاةِ በመስገድ ዘካንም በመስጠት አዞኛል።

19:55 ቤተሰቦቹንም በሶላት بِالصَّلَاةِ እና በዘካ ያዝ ነበር፤ እጌታዉም ዘንድ ተወዳጅ ነበር።

2:83 የእስራኤል ልጆችንም ጥብቅ ኪዳን አላህን እንጂ ሌላን አታምልኩ፤ በወላጆችም በጎን ሥራ አድርጉ፤ በዝምድና ባለቤቶችም፣ በየቲሞችም በምስኪኖችም በጎ ዋሉ፤ ለሰዎችም መልካምን ተናገሩ፤ ሶላትንም الصَّلَاةَ ደንቡን ጠብቃችሁ ስገዱ፤ ዘካንም ስጡ በማለት በያዝንባቸው ጊዜ አስታውሱ፡፡

10:87 ወደ ሙሳና ወደ ወንድሙ፡- «ለሕዝቦቻችሁ በምስር ቤቶችን ሥሩ፡፡ ቤቶቻችሁንም መስገጃ አድርጉ፡፡ ሶላትንም الصَّلَاةَ በደንቡ ስገዱ፡፡ ለሙሳ ምእምናኖቹንም አብስር» ስንል ላክን፡፡

3. ሰውም

ሰውምصوم‎ ጾም በቀድሞቹ ነቢያት የተሰጠ መመሪያ ነው፣ ምናልባት በዘጠነኛው ወር በረመዳን አይሁን እንጂ ጾም ነበረ፦

2:183 እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት ሕዝቦች ላይ እንደ ተጻፈ በናንተም ላይ ተጻፈ ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡

4.ዘካ

ዘካزكاة ምጽዋት በቀድሞቹ ነቢያት የተሰጠ መመሪያ ነው፣ ምናልባት ከመቶ ሁለት ነጥብ አምስት አይሁን እንጂ ምጽዋት ነበረ፦

21:73 በትእዛዛችንም፣ ወደ በጎ ሥራ የሚመሩ፣ መሪዎች አደረግናቸው፤ ወደነሱም መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትን መስገድን፣ ዘካንም الزَّكَاةِ መስጠትን፣ አወረድን፤ ለኛ ተገዢዎችም ነበሩ።

19:31 በየትም ስፍራ ብኾን ብሩክ አድርጎኛል፤ በሕይወትም እስከ አለዉ ሶላትን በመስገድ ዘካንም وَالزَّكَاةِ በመስጠት አዞኛል።

19:55 ቤተሰቦቹንም በሶላትና በዘካ وَالزَّكَاةِ ያዝ ነበር፤ እጌታዉም ዘንድ ተወዳጅ ነበር።

2:83 የእስራኤል ልጆችንም ጥብቅ ኪዳን አላህን እንጂ ሌላን አታምልኩ፤ በወላጆችም በጎን ሥራ አድርጉ፤ በዝምድና ባለቤቶችም፣ በየቲሞችም በምስኪኖችም በጎ ዋሉ፤ ለሰዎችም መልካምን ተናገሩ፤ ሶላትንም ደንቡን ጠብቃችሁ ስገዱ፤ ዘካንም الزَّكَاةَ ስጡ በማለት በያዝንባቸው ጊዜ አስታውሱ፡፡

5. ሃጅ

ሚሽነሪዎች ስለራሳቸው ዲን በቅጡ ስላልተረዱ ሙስሊሞች ስነ-አመክኖአዊ ጥያቄዎች ስንጠይቃቸው እርርና ምርር ብለው ከመንጨርጨርና ከመንተክተክ ውጪ ምላሽ አይሰጡም፣ ከዚያም አልፎ ከኢስላም ድንቅና ብርቅ መሰረቶች አንዱ የሆነውን ሃጅ ከፓጋን የተቀዳ ነው ሲሉ በመሰለኝ ሲተቹ ይታያል፣ እግር እራስን ሊያክ አይችልም፣ ምን ከኢስላም የተሻለ ነገር ተይዞ ነው ኢስላምን ሊያኩ የተነሱት? እስቲ ይህንን ሃጅ እናስተንትን፣ ሃጅ حج የሚለው ቃል ሃጅጀ حَآجَّ *ጎበኘ* ከሚል የመጣ ሲሆህ *ጉብኝት*“pilgrimage” ማለት ነው፣ ሃጅ የተጀመረው በነቢያችን አሊያም በሙሽሪኮች ሳይሆን በጥንቱ ነብይ ኢብራሂም ዘመን ነው፣ ይህን አምላካችን አላህ ሲናገር እንዲህ ይላል፦

22:26-27 ለኢብራሂምም የቤቱን ስፍራ #መመለሻ# ባደረግንለት ጊዜ፣ በኔ ምንንም አታጋራ፤ ቤቴንም፣ ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት፣ ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው፣ ባልነው ጊዜ አስታውስ። አልነውም፦ በሰዎችም ውስጥ በሐጅ بِالْحَجِّ ትዕዛዝ ጥራ፤

2:125 ቤቱንም ለሰዎች #መመለሻ# እና ጸጥተኛ ባደረግን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከኢብራሂምም መቆሚያ መስገጃን አድርጉ፡፡ ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም ቤቴን ለዘዋሪዎቹና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል ቃል ኪዳን ያዝን፡፡

አላህ ሰዎች እንዲጎበኙት ያዘዘው ቤት የራሱ ጥንታዊ ቤት ነው፦

22:26-27 ለኢብራሂምም የቤቱን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ፣ በኔ ምንንም አታጋራ፤ #ቤቴንም#፣ ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት፣ ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው፣ ባልነው ጊዜ አስታውስ።

2:125 #ቤቴን# ለዘዋሪዎቹና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል ቃል ኪዳን ያዝን፡፡

22:29 ከዚያም እንደ ጠጉርና ጥፍር ያሉትን ትርፍ አካላችቸንንና ዕድፋቸውን ያስወግዱ፤ ስለቶቻቸውንም ይምሉ፤ #በጥንታዊው #ቤት# ይዙሩ ።

3:96-97 ለሰዎች #መጀመሪያ የተኖረዉ #ቤት# ብሩክና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሲኾን ያ #በበካህ ያለው ነው፡፡ በውስጡ ግልጽ የኾኑ ተዓምራቶች የኢብራሒምም መቆሚያ አልለ፡፡ ወደ ውስጡ የገባ ሰው ጸጥተኛ ይኾናል፡፡ ለአላህም በሰዎች ላይ ወደርሱ መኼድን በቻለ ሁሉ ላይ #ቤቱን# መጎብኘት ግዴታ አለባቸው፡፡

አላህ በነቢያችን ያዘዘው ጉብኝት የጥንቱን ትዕዛዝ ዋቢና ታሳቢ ያደረገ ነው፦

3:97ለአላህም በሰዎች ላይ ወደርሱ መኼድን በቻለ ሁሉ ላይ ቤቱን መጐብኘት حِجُّ ግዴታ አለባቸዉ፤ የካደም ሰዉ አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነዉ።

ሃጅ ምንጩ መለኮታዊ እንጂ ፓጋናዊ እንደሆነ የሚያሳይ የቁርአን፣ የሃዲስ፣ የታሪክ መረጃ የለም፣ ለመሆኑ የአረቦችስ ታሪክ ከኢስላማዊ ምንጭ ሌላ ኖሮስ ነው እንዴ ለመተቸት የተበቃው? ሙሽሪኮች የጥንቱን ነብይ የኢብራሂምን አምልኮ ከጣኦት ጋር ቀላቅለው ማምለክ መጀመራቸውን የሚተርከው ኢስላማዊ ምንጭ ነው፣ መመዘንም ያለበት በዚሁ ምንጭ ነው፣ እስቲ የሚተቹትን የሃጅ ስርዓቶች እንመልከት፦

ነጥብ አንድ ጠዋፍ

ጠዋፍ طواف, የሚለው ቃል ጣፈ طَافَ *ዞረ* ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን *መዞር* ማለት ነው፣ ይህንንም ያዘዘው አምላካችን አላህ ለጥንቱ ነብይ ለኢብራሂም ነው

22:26-27 ለኢብራሂምም የቤቱን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ፣ በኔ ምንንም አታጋራ፤ ቤቴንም፣ ለሚዞሩት لِلطَّائِفِينَ እና ለሚቆሙበት፣ ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው፣ ባልነው ጊዜ አስታውስ።

2:125 ቤቱንም ለሰዎች መመለሻና ጸጥተኛ ባደረግን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከኢብራሂምም መቆሚያ መስገጃን አድርጉ፡፡ ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም ቤቴን ለዘዋሪዎቹ لِلطَّائِفِينَ እና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል ቃል ኪዳን ያዝን፡፡

22:27-29 አልነውም፦ በሰዎችም ውስጥ በሐጅ ትዕዛዝ ጥራ፤ ……ከዚያም እንደ ጠጉርና ጥፍር ያሉትን ትርፍ አካላችቸንንና ዕድፋቸውን ያስወግዱ፤ ስለቶቻቸውንም ይምሉ፤ በጥንታዊው ቤት ይዙሩوَلْيَطَّوَّفُوا ።

ነጥብ ሁለት ኢህራም

ኢህራም إحرام ግላዊ ፍላጎትን በመተው በኢህክላስ ወደ አላህ የመቅረብ ውሳኔና ተግባር ነው፦

2:197 ሐጅ ጊዜያቱ የታወቁ ወሮች ናቸው፡፡ በእነርሱም ውስጥ ሐጅን እንዲሠራ ነፍሱን ያስገደደ ሰው በሐጅ ውስጥ ሴትን መገናኘት ማመጽም ክርክርም የለም፡፡

አሲም አነስን ስለ ሶፋና መርዋ ሲጠይቀው አነስ ከመዲና የሆነ ሰሃቢይ ስለሆነ ግንዛቤው ስላልነበረውን እንዲህ ይላል፦

ኢማም ቡሃሪ ቅጽ2 መጽሃፍ 26 ቁጥር 710

حَدَّثَنَا مُحَمَّدُ بْنُ يُوسُفَ، حَدَّثَنَا سُفْيَانُ، عَنْ عَاصِمِ بْنِ سُلَيْمَانَ، قَالَ سَأَلْتُ أَنَسَ بْنَ مَالِكٍ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ الصَّفَا، وَالْمَرْوَةِ،. فَقَالَ كُنَّا نَرَى أَنَّهُمَا مِنْ أَمْرِ الْجَاهِلِيَّةِ، فَلَمَّا كَانَ الإِسْلاَمُ أَمْسَكْنَا عَنْهُمَا، فَأَنْزَلَ اللَّهُ تَعَالَى {إِنَّ الصَّفَا وَالْمَرْوَةَ } إِلَى قَوْلِهِ {أَنْ يَطَّوَّفَ بِهِمَا}

አሲም ኢብኑ ሱለይማን እንደተረከው፦ እኔ አነስ ኢብኑ ማሊክን ስለ ሶፋና መርዋ ጠየኩት፣ እርሱም መለሰልኝ ኢስላም ከመምጣቱ በፊት በዘመነ መሃይማኑ ጊዜ የነበረ ስርአት አድርገን እናስብ ነበር፣ ግን ኢስላም በመጣ ጊዜ በዚያ መዞርን አቆምን፣ ከዚያም አላህ እንዲህ የሚለውን አንቀጽ አወረደ፦

2:158 ሶፋና መርዋ ከአላህ ትዕዛዝ መፈጸሚያ ምልክቶች ናቸው፡፡ ቤቱን በሐጅ ወይም በዑምራህ ሥራ የጎበኘ ሰው በሁለቱ መካከል በመመላለሱ በርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም፡፡

ሙሽሪኮች ሶፋና መርዋ መካከል ማናት የምትባለውን ጣኦት አስገብተው ያመልኩ ነበር፣ ይህን የተረዱት የመዲና ሰዎች ኢህራም የማናት ስም ይመስላቸው ነበር፣ ይህንን ጉዳይ እሜቴ አይሻ ሲናገሩ፦

ኢማም ቡሃሪ ቅጽ 6 መጽሃፍ 60 ቁጥር 384

وَةُ قَالَتْ عَائِشَةُ نَزَلَتْ فِي الأَنْصَارِ كَانُوا هُمْ وَغَسَّانُ قَبْلَ أَنْ يُسْلِمُوا يُهِلُّونَ لِمَنَاةَ. مِثْلَهُ. وَقَالَ مَعْمَرٌ عَنِ الزُّهْرِيِّ عَنْ عُرْوَةَ عَنْ عَائِشَةَ كَانَ رِجَالٌ مِنَ الأَنْصَارِ مِمَّنْ كَانَ يُهِلُّ لِمَنَاةَ ـ وَمَنَاةُ صَنَمٌ بَيْنَ مَكَّةَ وَالْمَدِينَةِ

አይሻ በመጨመር፦ ይህ አንቀጽ የወረደው ከአንሷር ጋር የሚገናኝ ነው፣ እነርሱ ወደ ኢስላም ከመግባታቸው በፊት ኢህራም የማናት ስም ነው ብለው ያስቡ ነበር።

ተቺዎች ይህንን ሃዲስ ይዘው ነው ሃጅ፣ ጠዋፍ፣ ኢህራም፣ ሶፋና መርዋ የፓጋን ነው የሚሉት፣ ጥቅሱ የሚያወራው ደግሞ ሌላ ጉዳይ ነው፣ ለመተቸው ምንጩ ኢስላማዊ እስከሆነ ድረስ መልሱም ኢስላማዊ ምንጭ ነውና መቀበል አለባችሁ፣ ከሃጅ ጋር በተያያዘ መልኩ የሚደረጉ ጠጉርና ጥፍር መቆረጥና ዕድፍን ማስወገድ ለኢብራሂም የተሰጠ ትዕዛዝ ነው፦

22:29 *ከዚያም እንደ ጠጉርና ጥፍር ያሉትን ትርፍ አካላችቸንንና ዕድፋቸውን ያስወግዱ*፤ ስለቶቻቸውንም ይምሉ፤ በጥንታዊው ቤት ይዙሩ።

ማጠቃለያ

ኢስላም የነቢያት ሃይማኖት ነው፣ ይህን የነቢያት አስተምሮት ሙሽሪኮች ከጊዜ በኋላ ከጣኦታት ጋር ደባልቀውታል፣ ያን ጊዜ የመሃይምነቱ ጊዜ ተጀመረ፣ የነቢያቱ አምላክ አላህ ነቢያችንን በማስነሳት የጥንቱን የኢብራሂምን አስተምህሮት አመጣ፣ ሙሽሪኮች የሚሰሩትን ነገር አላህ በቃሉ ሲናገር፦

6:136 ለአላህም ከፈጠረው ከአዝመራና ከግመል፣ ከከብት፣ ከፍየልም ድርሻን አደረጉ፡፡ በሐሳባቸውም «ይህ ለአላህ ነው፡፡ ይህም ለተጋሪዎቻችን ነው፡፡» ለተጋሪዎቻቸውም «ለጣዖታት የኾነው ነገር ወደ አላህ አይደርስም፡፡ ለአላህም የኾነው እርሱ ወደ ተጋሪዎቻቸው ይደርሳል» አሉ፡፡ የሚፈርዱት ፍርድ ከፋ።

አላህ የዓለማቱ ጌታ መሆኑን ቢረዱም አላህም ከፈጠረው ከአዝመራና ከግመል፣ ከከብት፣ ከፍየልም ለጣኦቶቻቸው ድርሻን አደረጉ፡፡ ይህን ያደረጉበት 360 ጣኦቶቻቸው ወደ አላህ ያቃርቡናል ብለው ነው፣ ይህን አድራጎታቸው የቂያማ ቀን ዋጋቸውን ያገኛሉ፦

39:3 እነዚያም ከርሱ ሌላ ጣዖታትን ረዳቶች የያዙት ወደ አላህ ማቃረብን እንዲያቃርቡን እንጅ ለሌላ አንግገዛቸውም፣ ይላሉ፤

19:81-82 ከአላህም ሌላ አማልክትን ለነሱ መከበሪያ አማላጅ እንዲኾኑዋቸዉ ያዙ፤ ይከልከሉ መገዛታቸዉን በእርግጥ ይክዷቸዋል ፤ በነሱም ላይ ተቃራኒ ይኾኑባቸዋል።

29:17 ከአላህ ሌላ የምትግገዙት ጣዖታትን ብቻ ነው፤ ውሸትንም ትቀጣጥፋላችሁ፤ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትግገዙዋችው ለናንተ ሲሳይን ሊሰጧችሁ አይችሉም፤ ስለዚህ ሲሳይን ከአላህ ዘንድ ብቻ ፈልጉ፤ ተገዙትም፤ ለርሱም አመስግኑ፤ ወደርሱ ትመለሳላችሁ።

10:104 «እናንተ ሰዎች ሆይ! ከእኔ ሃይማኖት በመጠራጠር ውስጥ ብትሆኑ እነዚያን ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን አልገዛም፡፡ ግን ያንን የሚገድላችሁን አላህን እገዛለሁ፡፡ ከምእምናን እንድሆንም ታዝዣለሁ» በላቸው፡፡

8:35 በቤቱ ዘንድም ስግደታቸው ማፏጨትና ማጨብጨብ እንጂ ሌላ አልነበረም፤ ትክዱት በነበራችሁትም ነገር ቅጣትን ቅመሱ ይባላሉ።

ኢማም ቡሃሪ ቅጽ 9 መጽሃፍ 83ቁጥር 21

حَدَّثَنَا أَبُو الْيَمَانِ، أَخْبَرَنَا شُعَيْبٌ، عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ أَبِي حُسَيْنٍ، حَدَّثَنَا نَافِعُ بْنُ جُبَيْرٍ، عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ “ أَبْغَضُ النَّاسِ إِلَى اللَّهِ ثَلاَثَةٌ مُلْحِدٌ فِي الْحَرَمِ، وَمُبْتَغٍ فِي الإِسْلاَمِ سُنَّةَ الْجَاهِلِيَّةِ، وَمُطَّلِبُ دَمِ امْرِئٍ بِغَيْرِ حَقٍّ لِيُهَرِيقَ دَمَهُ ”


ወሰላሙ አለይኩም

  1. Meyer, Ronny (2011). "The Role of Amharic as a National Language and an African lingua franca". in Stefan Weninger. The Semitic Languages. Berlin: De Gruyter Mouton. pp. 1212–1220.
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.