እሙን
በስነ- አምክንዮ ወይም ሒሳብ፣ እሙን ማለት በጣም ግልጽ ከመሆኑ የተነሳ ሌላ ማረጋገጫ ሳይቀርብለት እውነትነቱ የታመነ አረፍተ ነገር ማለት ነው። እሙን አረፍተ ነገሮች በአምክንዮ መስተጻምር እንደ ሃረግ በመቀጣጠል ርጉጥ አረፍተ ነገሮችን ይሰጡናል ማለት ነው።
ምሳሌ፡ በዘመናት ታዋቂነትን ያተረፉ የእሙን ስብስቦች ቢኖሩ፣ ከክርስትስቶስ ልደት በፊት በ300 ዓ.ዓ. በነበረው ዩክሊድ የተጻፉት እንህ 5 እሙኖች ናቸው።
- ሁለት ቁጥሮች ከሌላ አንድ ቁጥር ጋር አንድ አይነት ከሆኑ እርስ በርሳቸውም አንድ አይነቶች ናቸው።
- ሐ እና ለ ሁለት አንድ አይነት ቁጥሮች ቢሆኑ ፣ መ እና ሠ እንዲሁ አንድ አይነት ቢሆኑ፣ ሐ+መ እና ለ+ሠ አንድ አይነት ናቸው።
- ሐ እና ለ ሁለት አንድ አይነት ቁጥሮች ቢሆኑ ፣ መ እና ሠ እንዲሁ አንድ አይነት ቢሆኑ፣ ሐ-መ እና ለ-ሠ አንድ አይነት ናቸው።
- ሁለት ቅርጾች ፍጹም አንድ ኅዋን ቢሞሉ፣ እርስ በርሳቸው አንድ አይነት ቅርጽ ናቸው።
- አንድን ቁጥር ከ ፩ በላይ በሆነ ቁጥር ቢያካፍሉ፣ ውጤቱ ምንጊዜም ከመጀመሪያው ቁጥር ያነሰ ነው።
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.