እሑድ
እሑድ የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ሲሆን በቅዳሜ እና በሰኞ መካከል ይገኛል። ሰኞ የሳምንቱ መጀመሪያ ቀን በሆነባቸው አገሮች ግን እሑድ የመጨረሻ ቀን ነው።
በብዙ አብያተ ክርስትያናት ዘንድ እሑድ እንደ ሰንበት ይቆጠራል። ሆኖም በሕገ ሙሴ ሰባተኛው ቀን ቅዳሜ ሲሆን ከሥራ ሁሉ እረፍት የሚድረግበት ሰንበት ቅዳሜ ነው። እሑድ ለአረመኔ ሮማውያን ሃይማኖት ጸሐይ ያመለኩበት ቀን ስለ ነበር፣ የሮማ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ በመጋቢት 10 ቀን 313 ዓ.ም. በአዋጅ እሑድ ለሮማ ዜጎች ሁሉ የእረፍት ቀን እንዲሆንላቸው አዘዘ። ጥቂት አመታት ከዚህ በኋላ ቆስጠንጢኖስ ወደ ክርስትና ቢገባም እሑድ በሮማ ሕጋዊ እረፍት ቀን ከመሆኑ አልተቋረጠም። ስለዚህ ነው እሑድ በካቶሊክና በብዙዎቹ አብያተ ክርስትያናት እስከ ዛሬ ድረስ እንደ ሰንበት የሚቆጠረው።
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.