ኤንሻኩሻና
ኤንሻኩሻና በሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ላይ የኡሩክ ንጉሥ ሲሆን ከሐማዚ ንጉሥ ሀዳኒሽ በኋላ በሱመር ላዕላይነቱን ለ60 አመታት ያዘ። በዚህ ዝርዝር ያሉት ቁጥሮች ግን ታማኝ አይደሉም፤ ብዙ ጊዜም በእጥፍ ተረዠሙ። ዘመኑ ምናልባት 2215-2195 ዓክልበ. ግድም እንደ ነበር ይመስላል። ኤንሻኩሻና ሐማዚንና የኪሽን ንጉሥ ኤንቢ-ኢሽታርን አሸነፈ፤ ከዚህ በላይ በኒፑር፣ አካድና አክሻክ ከተሞች ላይ ሥልጣን ያዘ። ልጁ ሉጋል-ኪኒሼ-ዱዱ በኡሩክ የተከተለው ሲሆን፣ ዋና ተወዳዳሪያቸው የላጋሽ ንጉሥ ኤአናቱም ግን ዑርን በመያዝ በላዕላይነት እንዳሸነፈ ይመስላል።
በአንድ ሰነድ ዘንድ የኪሽን ንጉሥ ኤንቢ-እሽታርን ማርኮ ኪሽን አጠፋ፣ የኪሽንና የአክሻክንም ሰዎች እንዳዛወረ ይላል።[1]
ቀዳሚው የሐማዚ ንጉሥ ሀዳኒሽ |
የሱመር አለቃ 2215-2195 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ የላጋሽ ንጉሥ ኤአናቱም |
ቀዳሚው ሉጋል-ኪቱን ? |
የኡሩክ ንጉሥ 2215-2195 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ሉጋል-ኪኒሼ-ዱዱ |
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.