ኤናናቱም
1 ኤናናቱም ከ2195 እስከ 2190 ዓክልበ. ድረስ ግድም የሱመር ከተማ ላጋሽ ገዢ («ኤንሲ») ነበረ።
የኤናናቱም ወንድምና የአኩርጋል ልጅ ኤአናቱም ንጉሥ በሆነበት ዘመን ላጋሽ ሰፊ መንግሥት ይዞ ነበር። ነገር ግን ኤአናቱም በ2195 ዓክልበ. ግድም ካረፈ በኋላ ግዛቱ እንደገና በየከተማው ተከፋፈለ። ያንጊዜ የኡሩክ ንጉሥ የኤንሻኩሻና ልጅ ሉጋል-ኪኒሼ-ዱዱ ኒፑርንና የሱመርን ላዐላይነት ያዘ፤ ኤናናቱምም የላጋሽ አለቃ ሆነ።
የኤናናቱም ንግሥት አሹመ-ኤረን ተባለች። በኤናናቱም ዘመን የላጋሽ ጎረቤት ኡማ በአለቆቹ ኡር-ሉማ እና ኢሊ ተመርቶ ከላጋሽ ጋር ተዋጋ። ኤናናቱም ተገድለና ልጁ ኤንመተና ተከተለው።
ቀዳሚው ኤአናቱም |
የላጋሽ ገዥ 2195-2190 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ኤንመተና |
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.