ኤችአይቪ
ኤችአይቪ ቫይረስ የሰውነትን የበሽታ መከላከያ በተለይ የነጭ ደም ሴሎችን (ህዋሳትን) በማጥቃት በቀላሉ ሰውነት ለበሽታ እንዲጋለጥ የሚያደርግ ቫይረስ ነው። ኤችአይቪ ያለባቸው ሰዎች የበሽታው ምልክት ሳይታይባቸው ለብዙ ዓመታት መኖር ይችላሉ። ቫይረሱ በሰውነታ ውስጥ እስከ አስር ዓመት በመቆየት ምንም ሳይታውቅ እና ምንም አይነት የህመም ምልክት ሳይታይበት በመኖር እና አለማውቅ ከአንድ ሰው ወደሌላ ሰው ሊተላለፍ የሚችል አደገኛ ቫይረስ ነው።
ኤችአይቪ የሚያጠቃው
ኤችአይቪ የሚያጠቃው የሰውነት የነጭ የደም ሴሎችን የሰውነት የበሽታ የመከላከያ ተቁዋማትን ነው። የሲዲፎር በመባል የሚታውቀውን የሰውነት የነጭ የደም ሴል ቁጥሩን (cd4 count) ከ 200 በታች በማድረግ የቫይረሱ መጠን በደም ውስጥ እንዲጨምር በማድረግ ለሕይወት ኣደገኛ እና ምቹ ጊዜ ተባቂ በመባል የሚታውቁትን በሸታዎች (ኦፓርቹንስቲክ ኢንፈክሽስ Opportunistic infections) OIs. በመፍጠር ኤድስ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ያደርጋል።
ኤድስ
ኤድስ ማለትም ኣኳየርድ ኢምዩኖደፊሸንሲ ሲንድረም ሲሆን ኤድስ ኤችእይቪ የማያማጣው የመጨረሻ ደረጃ ነው። ኤችአይቪ ያለበት ሰው ኤድስ ደረጃ ላይ ለመድረስ ብዙ ዓመታት ይወስድበታል። እንዲሁም መድኃኒቱንም ሳይጅምር ኤድስ ደረጃ ሳይደርስ ብዙ ዓመታት ሊቆይ ይችላል። አንድ ሰው የኤድስ ደረጃ ላይ ደረሰ ማለት የኤችአይቪ ቫይርስ የበሽታ መከላከያ ሃይል ተቁዋማትን ደምስሶ እና ሰውነታችን ከማንኛውም በሽታ የመቋቋም ኃይሉን በማሳጣት ለተለያዩ ኢንፈክሽኖች ይጋለጣል። አንድ ሰው አንድ ወይም ሁለት ኢንፌክሽኖች ሲኖሩበት እና በጣም ዝቅያለ የቲ-ሴል ቁጥር ሲኖረው ያሰው የኤድስ ደረጃ ደረሰ ሊያስብለው ይችላል።
የኤችአይቪ አመጣጥ
ሳይንቲስቶች የኤችአይቪን ቫይረስ አመጣጥ እንደጠቆሙት ከሆነ ከዌስት አፍሪካ ከሚገኝው ቺፓንዝ ዝርያ የመጣ መሆኑን አሳወቀዋል። ይህውም ሊሆን የቻለው የሰው ልጅ ቺፓንዚን ለምግብነት በሚይድንበት ጊዜ በሚደረገው የደም ንክኪ መሰርት ቫይርሱ ሊተላለፈ እንደቻለና። ከብዙ አመት በሃላም ቀስ በቀስ ወደ መላው አለም ሊስፋፋ እንደቻለ ገልጽዋል ኤችአይቪ ቀስ በቀስ እየተስፋፋ የመጣው ከ1978 (፲፱፻፸ ዓ.ም.) ወዲህ ነው። በአሁኑ ሰአት በኢትዮጵያ ውስጥ 1.3 ሚሊዮን በላይ የሚቆጠሩ ሰዎች ከኤችአይቪ ቫይርስ ጋር አብረው ይኖራሉ። በዓለም ላይም ከ 25 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች በኤድስ በሚመጣ በሸታ ተይዘው ሞተዋል። ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዬጵያ ውስጥ የኤድስ ታማሚዎች መኖራችው የተረጋገጠው በ1978 ዓ/ም ነው። በ2006ዓ/ም ወደ 2.9 ሚሊዮን የሚጠጉ ወንዶች፤ ሴቶች እና ሕጻናትም ሕይወታቸውን አተዋል። ኤችአይቪ ከተያዙት ውስጥ ከግማሸ በላይ የሚገምቱት ሲሞቱ 39.5 ሚሊዮን የሚሆኑ ከቫይርሱ ጋር በመኖር ይገኛሉ። በቅርቡ በUNAIDS/WHO እንደተዘገበው 4.3 ሚሊዮን የሚጠጉ አዲስ ሰዎች በኤችአይቪ እንደተያዙ ይገልጻል።
ኤችአይቪ መተላለፊያ መንገዶች
- የኤች አይቪ ቫይረስ ከሰውንት ከውጣ በሃላ በጣም ደካማ ከመሆኑ የተነሳ ብዙ አይቆይም ወድያውኑ ይሞታል። በዛ የተነሳ ነው ኤችአይቪ ከማንም ሰው ጋር በምናደርጋቸው የዕለት ተለት እንቅስቃሴዎች ለምሳሌ፣ እንደ እጅ መጨባበጥ፣ መተቃቅፍ፣ እና መሳሳም ሊያስተላልፉ እንደማይችሉና። በተጨማሪም ኤች አይቪ በመጸዳጃ ቤት መቀመጫ፣ በበር መኽፈቻ፣ በብርጭቆ መጠጫ፣ በምግብ ወይም በማንኛውም አይነት እንስሳ እንደ ቢንቢ ንክሻ በመሳሰሉት ሊይዝ አይችልም።
- ኤችአይቪ ለመያዝም ሆነ ለማስተላለፍ የሚችሉበት መንገዶች የተለያዩ ናቸው፣ መንገዶቹ ምን እንደሆኑ ማወቁ በጣም ጠቀሜታ አለው። ስለ ኤችአይቪ ዕውቀት ያለውን ሰው ማነጋገር ተገቢ ሆኖ ሳለ ይህንንም ከታች የተዘርዘረውን በተግባር ላይ ቢያውሉት መልካም ነው፣
- ኤችአይቪ በሚከተሉት ሁኔታዎች ሊተላለፍ ይችላል
- ቫይረሱ ያለበት ሰው የተጠቀመበትን የድረግ (Drugs) መርፌ ሌላ ሰው ቢጠቀምበት (Intravenous) ቫይረሱ ሊተላለፍ ይችል።
- ቫይረሱ ካለበት ማንኛውም ሰው (ወንድ ወይም ሴት) ጋር የግብረ ሰዶም ግንኙነት (Homosexual, bisexual intercourse) በማድረግ በሽታው ሊይዝ ይችላል።
- ቫይረሱ ካለበት ሰው ጋር በሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት (Heterosexual intercourse)
- ኤችአይቪ ያለባት እናት ቫይረሱን (ማህፀን ውስጥና በወሊድ ጊዜም) ለሕፃንዋ ማስተላለፍ (Intrauterine, perinatal) ትችላለች።
- ቫይረሱ የለባት እመጫትን ጡት ወተት ካጠባች ቫይረሱን ሊተላለፍ ይችላል።
መከላከያ እርምጃዎች 4ቱ " መ" ዎችይ
- መታቀብ/መቆጠብ
- መወሰን
- መጠቀም
- መመርመር
ለመከላከል የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ በጣም ጠቃሚ ነው
ከኤችአይቪ ቫይረስ ለመከላከል የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ ይጠቅማል
- ከማንኛውም ዓይነት የግብረ ሥጋ ግንኙነት (ከተቻለ) መቆጠብ፣ ካልተቻለ ኣንድ ታማኝ የፍቅር ጓደኛ ጋር በመወሰን ኮንዶም መጠቀም
- ለረዥም ጊዜ ተማምነው ኣብረው የቆዩ ባልና ሚስት በመስጋትና ለኤችአይቪ ይይዘኛል በሚል ፍራቻ በኮንዶም (Condom) መጠቀም የለባቸውም። ታማኝነት ከመቼውም ጊዜ በላይ ኣስፈላጊ ስለሆነ ባለትዳሮች ታማኝንታችውን ማጎልበት ይጠበቅባቸዋል
- የሚወጉ ድራጎች (እየተደበቁ ተሰባስበው ባልፀዱ መሣሪያዎች ከሚወስዱ ጋር) አለመውሰድ ማለት መርፌና ሲሪንጋ ኣለመጋራት
- ከማያውቁት ሰው ወይም ከብዙ ሰዎች ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ካደረጉ ከሌላ ሰው ጋር ምንም አይንት ግንኙንት ከመፈጽም በፊት መመርመራ ያድርጉ
- ለገንዘብ ብለው ከማያቁት ሰው ጋር ማንኛውንም ዓይነት የግብረ ሥጋ ግንኙነት ኣለማድረግ deze taal kan ik nit lezen.
ኤችአይቪ ለመያዝ የሚያስችሉ ባህሪዎች ዋነኞቹ
-በጣም አስጊ ደረጃ ላይ ሊሆኑ የሚችሉ
- የሚወጉ ድራጎች (እየተደበቁ ተሰባስበው ባልፀዱ መሣሪያዎች ከሚወስዱ ብዙ ሰዎች ጋር) መርፌና ሲሪንጋ ከተጋሩ
- ልቅ የሆነ የግብረ ሥጋ ግንኙነት፣ የግብረ ሰዶም ግንኙነት (Heterosexual intercourse,Homosexual, bisexual intercourse) ከፈጸሙ
- ለገንዘብ ብለው የግብር ሥጋ ግንኙንት ወይም የግብረ ሰዶም ግንኙነት ከፈጸሙ
- ለአባላዘር በሽታ ተጋለጠው የሚያቁ ከሆነና
- ወይም ከላይ የተዘርዘሩትን ከፈጸመ ግለሰብ ጋር የወሲባዊ ግኑኘንት ከፈጸሙ
የኤችአይቪ ምርመራ
እርግጠኛ ዕራስን ለማወቅ ግዴታ መልሱ የሚገኘው የኤችአይቪ ምርመራ በማድረግ ብቻ ነው። ስለዚህ ዕራሶን የሚጠራጠሩ ከሆነ ተመርመሩ። ተመርምረው ውጤቶን ከቫይረሱ ነፃ መሆኖ ቢነገሮትም የውሽት ውጤት የሚባል (ዊንዶ ፔሬድ የሚባል) ነገር ስላለ ከ 3-6 ወር በሃላ እርግጠኛ ለመሆን ደግመው መመርመር ይገባል። ይህን ሲያረጉ ግን አሁንም ኮንዶም መጠቀሞን አይርሱ።
ኤችአይቪ ቀስ በቀስ እየተስፋፋ የመጣው ከ1978 (፲፱፻፸ ዓ.ም.) ወዲህ ሲሆን እስከ 1985 ድረስ የተበከለ ደም ናሙና በመወጋትና በመሳሰሉት ብዙ ሰዎች ይዚህ ሰለባ በመሆን ብዙ ሰዎች ተይዘዋል። ከ1988 ወዲህ ግን ኤችአይቪ ሲኖር ደም ውስጥ ነጭ ሴል የሚሠራውን ኣንቲቦዲ (Antibody) በመመርመር ኤችአይቪ ቫይረስ እንዳለ እና እንደሌለ የሚጣራበት ፈጣን የምርመራ ዘዴ ስለተሠራ በሆስፒታል ከሚሰጠን ደም መተላለፉ ቀርትዋል።
ከአካል የሚወጡ ፈሳሾች ላይ ሁሉ ኤችአይቪን ማግኝት የሚቻል ቢሆንም መደበኛ የኤችአይቪ ምርመራ በደም ናሙና ላይ የሚደረግ የኤችአይቪ-1/2 አንቲ ባዲ ምርመራ ነው።
እስታሁን የተሰሩትን የአንቲባዲ ምርመራ አይነቶችን በሁለት ከፍል ማየት ይቻላል።
ኤላይዛ መሰረት አርገው የሚከናወኑ
- ኤላይዛ አይ.ኤፍ.ኤ
- ኤላይዛ-ዌስተርን ቦሎት
ፈጣን ምርመራዎች የሚባሉት ተመርተው በገበያላይ የቀርቡ ወደ 60 የሚቆጠሩ መመርመሪያዎች ሲኖሩ በሶስት ዋና ዋና ቴክኒኮች ላይ የተመረኮዙ ናችው።
- ፓርዲክል አጉሌሽን (Particle agulation)
- ላተራል ፍሎ (lateral flow)
- ፍሎ ትሩ (Flow through)
እነዚህ መመርመሪያዎች እያንዳንዳቸው ለምርመራ ማከናወኛነት በምንጠቀምበት ጊዜ ምንም አይነት ተጨማሪ ኪሚካል አያስፈልጋቸውም።
ለመጠቀምም ጊዜ የማይፈጅና ዋጋውም ተመጣጣኝ ነው። አስተማማጝነታቸውም ከኤላይዛር ጋር የሚስተካከል ነው።
ፈጣን የኤችአይቪ ምርመራ ማለት ለቫይረሱ የተዘጋጀ አንቲ ቦዲ በደም ውስጥ መኖሩንና አለመኖሩን የሚያመልክት የምርመራ አይነት ነው። በፈጣን የምርመራ ዘዴ ውጤቱን ከ10-60 ደቂቃዎች ውስጥ ማውቅ የሚያስችል የመመርመሪያ ዘዴ ነው።
ተመርምረው ውጤቶዎ ኤችአይቪ ፖዘቲቨ ከሆነስ
በአሁኑ ጊዘ በኤችአይቪ ዙሪያ ላይ በዙ መረጃዎች የሚገኘበት ግዘ ስለሆነ ከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር ተስማምቶ ለመኖርይቻላል። በአሁን ሰአት ኤችአይቪን እንደማንኛውም አይንት ቫይረስ አይቶ ጤናን እየጠበኩና መንፈስን ሳያስጨንቁ ተረጋግቶ መኖር ይቻላሉ።
ኤችአይቪ እንዳይዘን የምንከላከልበት ክትባት በአሁኑ ሰአት የለም። ኤችአይቪ ከያዘም በኋላ የሚፈውስ መድኃኒት የለም። ነገር ግን ከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር ተስማምቶ ለመኖር የቻላለ። በአሁኑ ጊዜ ፀረ-ኤችአይቪ መዳኒቶች ከፈተኛውን አስታውጾ በማድረግ ላይ የገኛሉ። ኤችአይቪ ያለበት ሰው በትክክል የፀረ-የኤችአይቪ መዳኒቶቹን በመውሰድ እንደማንኛውም ሰው መኖር ይችላል። ቫይርሱ ያለባቸው ሰዎች መውለድ ሲፈልጉ ተገቢውን የህክምና አገልግሎት ከጤና ባለሙያቸው ጋር በመነጋገር ጤነኛ ልጀ መውለስ ይችላሉ። ኤችአይቪ ያለባት እናትከማርገዝዋ በፊት ማወቅ የሚገባትን ቅድመ ተከተሎች መከተል ይኖርባታል።
ኤችአይቪ እንዴት እንደሚተላለፍ መረጃዎችን በመከታተል ቫይረሱ እንዳይሰራጭ ትክክለኛዎቹን ጥንቃቄዎች መከተልና ለሌሎችም ማስተማር የያንዳንዳችን ኃላፊነት መሆን አለበት። ኤችአይቪ እንዴት እንደሚተላለፈ ግንዛቤዎች እንዴት እንደምንከላከል መረዳትና ወደ ሌሎች እንዳይተላለፍ እንዴት መጠንቀቅ እንዳለብን ማወቅ በጣም ጠቃሚ ነው።
እንዳይስፋፋ መከላከል
- መታቀብ (ከማንኛውም አይነት የገብረስጋ ግንኙነት መቆጠብ) እንድ የትዳር ጛደኛ እስከሚያገኙ ድረስ ወይም ደሞ ኤችአይቪ እንዳለባችሁ ካወቃችሁ
- ሁለት ኤችአይቪ እንዳለባቸው ያወቁ ባለትዳሮች ወይም አበረው ያሉ ጉዋድኞች በግብረ-ሥጋ ግንኙነት ጊዜ ኮንዶም መጠቀም አለባቸው ምክንያቱም ከተለያዩ የአባላዘር በሽታዎች ለመከላከል እና ከተለያዩ የኤችአይቪ ንዑስ ዝርያዎች ላለመያዝ
- ከሁለት አንዳቸው ብቻ ከሆኑ ኤችአይቪ ያለበት ሁልጊዜ ኮንዶም መጠቀም እና ቅባት (Lubricant) ያለው ኮንዶም መጠቀም
- ወይ ደሞ ከአንድ ሰው በላይ ጋር የግብረ-ሥጋ ግንኙንት የሚፈጸሙ ከነበሩ ወይም ከሆኑ፦
- የኤችአይቪ ምርመራ ያድርጉ
- ወንድ ከሆኑ እና ከወንድ ጋር የግብረ-ሰዶም ግንኙነት ፈጸመው ከሆነ ቢያንስ ቢያንስ በአመት አንዴ ይመርመሩ
- ሴት ከሆኑ እና ለማርገዝ እቅድ ካሎት ወይም ካርገዙ በአስቸኩዋይ ይመርምሩ (ጤነኛ ልጅ ለመውለድ ሲባል)
- የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ከመፈጸሞ በፊት ስለ ኤችአይቪ እና ሰለ ተለያዩ የአባላዘር በሽታዎች ከወንድ/ከሴት ጛድኛ ጋር በግልጽ ማውራት ልምድ ማረግ አለብን
- በደንብ ተጠናኑ፣ ተወያዩ ስለ ሁለታችሁም ስለ አለፈው የወሲብ ሕይውታችሁ ውይም ድራግ ትጠቀሙ ከነበረ ( መጠጥ፣ ጫት ሱሰኝነት) ሌሎችም
- ከዚህ በፊት የኤችአይቪ ምርመራ አርገው እንደሚያቁና እንደማያቁ መጠያየቅ
- ምንም እንኩዋን የኤችአይቪ እያዛለሁ ብለው ምንም ጥርጣሬ ባይኖሮትም ሁሌ ለጠቅላላ ምርመራ በሚሄዱበት ጊዜ የኤችአይቪ ምርመራ ቢያረጉ በጣም ጠቃሚ ነው
የውጭ መያያዣዎች
- አበሻ ኬር የበጎ እድራጊ ድርጅት Archived ፌብሩዌሪ 29, 2008 at the Wayback Machine
- Divisions of HIV/AIDS Prevention / October 20, 2008 Archived ፌብሩዌሪ 29, 2008 at the Wayback Machine ትርጉም በአበሻ ኬር
- Center for Disease Control: What is AIDS? ትርጉም በአበሻ ኬር
- የኢትዮጲያ ኤድስ መረጃ ማእከል
- ኣበራ ሞላ AIDS in Amharic, 1991.
- ዶ/ር ኣበራ ሞላ AIDS in Amharic, 1991
- Understanding AIDS, 1988