ኤሽኑና

ኤሽኑናሱመር ጥንታዊ ከተማ ነበር። ዛሬው ሥፍራው ተል አስማር ተብሎ በዘመናዊው አገር ኢራቅ ውስጥ በዲያላ ወንዝ ሸለቆ ይገኛል። ኤሽኑና ከስሜኑ ተራሮች ወደ መስጴጦምያ በደረሰው መንገድ ላይ ስለተቀመጠ የብርቅ ሸቀጦች (ፈረስሰንፔር፣ ዕንቁዎች ወዘተ.) ንግድ ማዕከል ሆነና በለጸገ።

ኤሽኑና
(ተል አስማር)
የሚጸልይ ምስል፣ ኤሽኑና
ሥፍራ
ኤሽኑና is located in መስጴጦምያ
{{{alt}}}
መንግሥት አካድ፣ ኤላም፣ ዑር፣ ኢሲን፣ ላርሳ፣ ባቢሎኒያ ወዘተ.
ዘመን 2075-1674 ዓክልበ. ግድም
ዘመናዊ አገር ኢራቅ
ጥንታዊ አገር ሱመር

አካድ መንግሥት እየደከመ (በሹዱሩል ዘመን 2001-1986 ዓክልበ. ግ.) ኤሽኑና በአካድ ቅሬታ ግዛት ውስጥ እንደ ቀረ ይታወቃል። ከዚያ የኤላም ንጉሥ ኩቲክ-ኢንሹሺናክ ያዘው። ከዚህ በኋላ ለዑር መንግሥት ተገዥ ሆነ፤ ከዚያ በተራው ለኢሲንና ለላርሳ ተገዛ። አንዳንድ የኤሽኑና ገዢ ግን እንደ ነጻ ንጉሥ ይገዛ ነበር። 2 ኢፒቅ-አዳድ 1771-1729 ዓክልበ. በተለይ ለኤሽኑና ሰፊ ግዛት አሸነፈ። በመጨረሻ በ1674 ዓክልበ. ኤሽኑና ለባቢሎን ንጉሥ ሃሙራቢ ወደቀ።

የኤሽኑና ሕግጋት ደግሞ ለሥነ ቅርስ ታውቀዋል፤ የትኛው ንጉሥ እንዳወጣቸው ግን እርግጥኛ አይደለም።

የኤሽኑና ነገሥታት

(ኡልትራ አጭር)

  • - ኢቱሪያ - ገዥ (ኤንሲ) ለዑር-፫ መንግሥት
  • 1910-1904 - ሹ-ኢሊያ
  • 1904-1896 - ኑራኹም - ገዥ ለዑር
  • 1896-1886 - ኪሪኪሪ - ገዥ
  • 1886-1872 - ቢላላማ - ገዥ ለኢሲን
  • - ኢሻር-ራማሹ - ገዥ
  • - ኡሹር-አዋሱ - ገዥ
  • - አዙዙ - ገዥ
  • - ኡር-ኒንማርኪ - ገዥ
  • - ኡር-ኒንጊዚዳ - ገዥ
  • 1806-1793 - 1 ኢፒቅ-አዳድ
  • 1793-1791 - ሳሪያ - ገዥ
  • 1784-1778 - ዋራሣ - ገዥ
  • 1791-1784 - በላኩም - ገዥ
  • 1778-1771 - 1 ኢባልፒኤል
  • 1771-1729 - 2 ኢፒቅ-አዳድ
  • 1729-1719 - ናራም-ሲን
  • 1719-1718 - ኢብኒ-ኤራ
  • 1718-1716 - ኢቂሽ-ቲሽፓክ
  • 1716-1712 - ዳኑም-ታሃዝ
  • 1712-1692 - ዳዱሻ
  • 1692-1680 - 2 ኢባልፒእል
  • 1680-1674 - ሲሊ-ሲን
የኤሽኑና መንግሥት በ1680 ዓክልበ.
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.