ኤምፒ3
ኤምፒ3 ድምፅን ወይም ዘፈንን በኮምፒውተር ላይ ማስቀመጫ ፎርማት ነው። ቴክኖሎጂው ከተፈጠረ ፳ ዓመት ገደማ ይሆነዋል። በብዛት በዘፈን ማጫዎቻዎች እንዲሁም ለድረ ገጽ ራዲዮዎች፣ ለፖድካስት ማጫዎቻዎች ይጠቅማል።
ኤምፒ3 ለምን ይጠቅማል?
ዋና ጥቅሙና ተወዳጅ ያደረገው ነገር ብዙ የድምፅ መረጃን፣ዘፈን በጣም ጥቂት በሆነ ቦታ ለማስቀመጥ ያስችላል። ለምሳሌ 20(፳) ገደማ የሚሆን ሲዲ ከኤምፒ3 የዘፈን ፎርማት ውጭ የተዘጋጀ ሲዲ ኤምፒ3 የዘፈን ፎርማት በመጠቀም በአንድ ሲዲ ልናዘጋጀው እንችላለን።ይህ ማለት ወደ 200(፪፻) ዘፈኖችን በአንድ ሲዲ ማስቀመጥና ማጫዎት ማለት ነው።
የኤምፒ3 ማጫዎቻዎች አይነት
የኤምፒ3 ማጫዎቻዎች ሙዚቃውን የሚያከማችበት የተለያየ ዘዴ አለው። አይነቶቹም የሚከተሉት ናቸው።
- ሶሊድ ስቴት(ፍላሽ ዲስክ) አይነት የኤምፒ3 ማጫዎቻ።
- ሐርድ ዲስክ አይነት የኤምፒ3 ማጫዎቻ።
- ባለ ሲዲ አይነት የኤምፒ3 ማጫዎቻ።
የኤምፒ3 ማጫዎቻዎች።
- አይፖድ(ipod)
- አፓሰር(Apacer)
- ሶኒ(Sony)
- የማይክሮሶፍት ዙን (Zune from Microsoft)
- የክሬቲቭ ዜን( Creative Zen)
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.