ኢንካ መንግሥት

የኢንካ መንግሥት1430 እስከ 1525ደቡብ አሜሪካ በተለይም ፔሩ የነበረ መንግሥት ነው።

የኢንካዎች አምባ በቁስቁ ፔሩ
የኢንካ መንግሥት መስፋፋት ከ1430 እስከ 1525 ዓም ደረስ

ቀድሞ በአንዴስ ተራሮች የነበሩት መንግሥታት የቲዋናኩ መንግሥት (300-1150 ዓም ግድም) እና የዋሪ መንግሥት (600-1100 ዓም ግድም) እንደ ተገኙ ታውቋል። ከነዚህ መንግሥታት ውድቀት በኋላ ከተነሡት አነስተኛ ክፍላገራት አንዱ የቁስቁ መንግሥት በ1190 ዓም ግድም ተነሣ። ይህ የቁስቁ መንግሥት በ1430 ዓም የኢንካ መንግሥት ተብሎ ጎረቤቶቹን በመያዝ መስፋፋት ጀመር። የኢንካ መንግሥት ስም በራሱ ቋንቋ በቀቿ «ታዋንቲንሱዩ» («አራቱ አውራጆች») ተባለ።

1518 ዓም የእስፓንያ አለቃ ፍራንሲስኮ ፒዛሮ ከነሥራዊቱ ጎበኛቸውና ወደ እስፓንያ ተመለሰ። የእስፓንያ ንግሥት እንዲወርራቸው ፈቃዷን ሰጥታ፣ ይህ ወረራ በ1524 ዓም ተከሠተ። ፒዛሮ በተመለሰበትም ጊዜ ኢንካዎች ከ1521 ዓም ጀምሮ በእርስ በርስ ጦርነት እንደ ተያዙ አገኛቸው። በዚህ ብሔራዊ ትግል ደክመውና ጠመንጃ ባለመኖራቸው ቶሎ ወደቁ። ሆኖም ቅሬታው አዲሱ ኢንካ መንግሥት እስከ 1564 ዓም ድረስ ቆየ።

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.