ኢንተርስላቪክ
ኢንተርስላቪክ (Interslavic) ወይም መድዡስሎቭያንስኪ (medžuslovjansky) የስላቪክ ሰው ሠራሽ ቋንቋ ነው። የተፈጠረው በ፲፱፻፺፰ (1998) ዓ.ም. በኦንድረይ ረችኒክ፣ ጋብሪዬል ስቮቦዳ፣ ያን ቫን ስቴንበርገንና ኢጎር ፖልያኮቭ ነበር። በመጀመርያው ስሙ «ስሎቭያንስኪ» (Slovianski) ነበር። የቋንቋው ስም ከስላቭኛ ቃላት «መድዡ» (መካከል) እና «ስሎቭያንስኪ» (ስላቭኛ) ደርሷል። ዛሬ ከ፭፻ እስከ ፳፻ ሰዎች ይችሉታል።
ቋንቋው በጣም ቀላል ነው። ቃላቱ ከስላቪክ ቋንቋዎች ብቻ የተመሠረተ ነው። የሚጻፈው በላቲንና ቂርሎስ ፊደል ነው።
ምሳሌ
የጌታ ጸሎት በኢንተርስላቪክ፥
ላቲን፥
Otče naš, ktory jesi v nebesah, nehaj svęti sę imę Tvoje. Nehaj prijde krålevstvo Tvoje, nehaj bųde volja Tvoja, kako v nebě tako i na zemji. Hlěb naš vsjakodenny daj nam dneś, i odpusti nam naše grěhi, tako kako my odpušćajemo našim grěšnikam. I ne vvedi nas v pokušeńje, ale izbavi nas od zlogo. Ibo Tvoje je krålevstvo i moć i slava, na věki. Amin.
ቂርሎስ፥
Отче наш, кторы јеси в небесах, нехај свети се име Твоје. Нехај пријде кралевство Твоје, нехај буде вольа Твоја, како в небе тако и на земји. Хлеб наш всьакоденны дај нам днес, и одпусти нам наше грехи, тако како мы одпушчајемо нашим грешникам. И не введи нас в покушенје, але избави нас од злого. Ибо Твоје је кралевство и моч и слава, на веки. Амин.
አጠራር፥
ኦትቼ ናሽ፣ ክቶሪ ዬሲ ቭ ነበሳኽ፣ ነኻይ ስቨቲ ሰ ኢመ ትቮዬ። ነኻይ ፕሪይደ ክራለቭስትቮ ትቮዬ፣ ነኻይ ቡደ ቮልያ ትቮያ፣ ካኮ ቭ ነበ ታኮ ኢ ና ዘምዪ። ኽለብ ናሽ ቭስያኮደንኒ ዳይ ናም ድነስ፣ ኢ ኦድፑስቲ ናም ናሼ ግረኺ፣ ታኮ ካኮ ሚ ኦድፑሽቻዬሞ ናሺም ግረሽኒካም። ኢ ነ ቭቨዲ ናስ ቭ ፖኩሼኜ፣ ኣለ ኢዝባቪ ናስ ኦድ ዝሎጎ። ኢቦ ትቮዬ ዬ ክራለቭስትቮ ኢ ሞች ኢ ስላቫ፣ ና ቨኪ። ኣሚን።
አማርኛ፥
አባታችን ሆይ! በሰማያት የምትኖር ስምህ ይቀደስ መንግስትህ ትምጣ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን የዕለት እንጀራችንን ስጠን ለዛሬ በደላችንንም ይቅር በለን እኛም የበደሉንን ይቅር እንድንል አቤቱ ወደ ፈተና አታግባን ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ መንግሥት ያንተ ናትና ኅይል ክብር ምስጋና ለዘለዓለሙ አሜን!
የውጭ መያያዣዎች
- የቋንቋው ስዋሰው መረጃ
- በኢንተርስላቪክ የዜና ምንጭ Archived ዲሴምበር 9, 2019 at the Wayback Machine
- እንግሊዝኛ-ኢንተርስላቪክ መዝገበ ቃላት