ኢሉሉ

ኢሉሉ ወይም ኤሉሉ፣ በሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ ንጉሡ ሻርካሊሻሪ ካረፈ በኋላ ለሦስት ዓመት (2013-2010 ዓክልበ. ግድም) ለአካድ መንግሥት ከተወዳደሩት አራት ሰዎች አንዱ ነበር።

ሌሎቹ ሦስት የተዘረዘሩት ተወዳዳሪዎች፣ ኢርጊጊ፣ ኢሚ፣ እና ናኑም ሲሆኑ፣ ስለዚያው ዘመን «ማን ንጉሥ ነበር? ማን ንጉሥ አልነበረም!» የሚለው ምሳሌ በመስጴጦምያ ሥነ ጽሑፍ ለረጅም ዘመናት ይስታወስ ነበር። ስለነዚህ አራት ግለሰቦች ምንም ቅርስ ወይም መረጃ የለንም። በዚህ ወቅት ጉታውያን ወደ መስጴጦምያ ገብተው መሬት ከአካድ ለመያዝ እንደ ጀመሩ ይመስላልና ከጉታውያን ነገሥታት አንዱ «ኤሉልመሽ» ወይም «ኤሉሉመሽ» ስለሚባል ይህ ምናልባት ለአካድ ዙፋን የተወዳደረው ኢሉሉ ይሆናል የሚሉ ደራስያን አሉ።[1][2] በመጨረሻ ዱዱ የሚባል ንጉሥ አሸነፈና በአካድ ዙሪያ ብቻ ገዛ፤ በደቡብ ግን ኤላምና የሱመር ዋና ከተሞች ((ኡርኦሬክላጋሽ) ከአካድ ተለይተው ነጻነታቸውን እንደገና አዋጁ።

ቀዳሚው
ሻርካሊሻሪ
አካድ ንጉሥ
2013-2010 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ዱዱ
ሱመር ንጉሥ
2013-2010 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ጉታውያን

ተዋቢ መጻሕፍት

  1. The Near East: The Early Civilizations, 1967, p. 119.(እንግሊዝኛ)
  2. James G. MacQueen, Babylon, 1964, p. 27.(እንግሊዝኛ)
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.