ኡር-ናሙ

ኡር-ናሙ ከ1984 እስከ 1966 ዓክልበ. ግድም ድረስ የኡርና የሱመር ንጉሥ ነበር። በተለይ የሚታወቀው የኡር-ናሙ ሕግጋት በ1983 ዓክልበ. ግድም ስለ ማውጣቱ ነው።

ኡር-ናሙ ቅርጫት ይዞ (ጎን)
ኡር-ናሙ ቅርጫት ይዞ

ኡሩክ ንጉሥ ኡቱ-ኸጛል ጉታውያንን አስወጥቶ ለአጭር ዘመን እንደ ቀረ ይመስላል። በአንዱ ሰነድ መሠረት በመስኖ ወደቀና ሰመጠ። ኡር-ናሙ ከዚያ ኡሩክንና ላጋሽን ይዞ የሱመር ገዥ ሆነ። ለረጅም ዘመን ሱመር በአካድ ወይም በጉታውያን ይገዛ ነበር። አሁን ግን አዲስ የሱመር ኗሪ ግዛት በኡር ጀመረ፤ ይህም የኡር መንግሥት ወይም የኡር ሦስተኛ ሥወ መንግሥት (ኡር-፫) ይባላል። በይፋ ግን ስያሜው «የሱመርና የአካድ መንግሥት» ነበረ። ታላቁ ሳርጎን ዋና መቅደሱን ከኒፑር ወደ ባቢሎን አዛውሮ ነበር፤ አሁን ግን ኡር-ናሙ ለጊዜው ወደ ኒፑር መለሠው።

በኡር-ናሙ ዘመነ መንግሥት ካሉበት ፲፰ ዓመታት፣ ፲፯ቱ ከሰነዶች ይታወቃሉ፤ ቅድም-ተከተላቸው ግን እርግጠኛ አይደለም። አንዱ «ጉቲዩም የጠፋበት ዓመት» ሲሆን፣ ሁለት ልዩ የአመት ስሞች ምናልባት ሕግ ስለ ማውጣቱ ይመስላሉ፤ እነርሱም «ንጉሡ ኡር-ናሙ ሥርዓቱን ከታች እስከ ላይ ያስተካከለበት ዓመት» እና «ኡር-ናሙ በብሔሩ ውስጥ ፍትሕ የሠራበት ዓመት» ናቸው።[1]

በአንድ ግጥም በሱመርኛ፣ ኡር ናሙ በጉቲዩም ላይ እየዘመተ ሥራዊቱ ካደውና በውግያ ሞተ ይላል። ፲፰ ዓመታት ከገዛ በኋላ ልጁ ሹልጊ ተከተለው።

ቀዳሚው
ኡቱ-ኸጛል
ሱመር ነጉሥ
1984-1966 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሹልጊ
  1. Year-names for Ur-Nammu
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.