ኡራኑስ
ኡራኑስ፡ (ምልክት፦) መሬት በምትገኝበት ማለትም ሚልክ ዌይ ተብሎ በሚጠራው ረጨት ወይም የከዋክብት ስብስብ ውስጥ የሚገኝ ፕላኔት ነው። ይህ ፕላኔት ከፀሐይ ባለው ርቀት 7ኛ ( ሰባተኛ ) ነው። ከበፊቱ ኣጣርድ፣ ቬነስ፣ መሬት፣ ማርስ፣ ጁፒተር እና ሳተርን የተባሉ ፕላኔቶች ይገኛሉ። ከበስተኋላው ደግሞ ነፕቲዩን እና ትንሹ ፕሉቶ ይገኛሉ።
ይዘት
ይህ ፕላኔት በዚህ ረጨት ውስጥ ከሚገኙ ፕላኔቶች በግዝፈቱ የሶስተኛነትን ደረጃ ይይዛል። ግዙፍ የ ጋዝ ክምችት እንደሆነ ይታመናል። በ ረጨቱ ውስጥ የጋዝ ክምችት የሆኑት ፕላኔቶች ጁፒተር፣ ነፕቲዩን፣ ሳተርን እና ራሱ ኡራኑስ ናቸው። በዚህም የተነሳ ጆቪያን ወይም ጁፒተርን መሳይ እየተባለ ይጠራል። በአብዛሃኛው ሃይድሮጅን እና ሂሊየም ከተባሉ ንጥረነገሮች የተሰራ ነው። በአጠቃላይ ክብደኡ ደግሞ የአራተኛነትን ደረጃ የያዘ ነው።
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.