አዶልፍ ሂትለር

አዶልፍ ሂትለር (ጀርመንኛ: Adolf Hitler አዶልፍ ሂትለ) እ.አ.አ. ከ1933 ጀምሮ የጀርመን ቻንስለር እንዲሁም ከ1934 ጀምሮ ደግሞ የጀርመን መሪም (Führer) ጭምር የነበረ ሰው ነው።

አዶልፍ ሂትለር
Adolf Hitler
አዶልፍ ሂትለር
አዶልፍ ሂትለር
የተወለዱበት ቀን ሚያዝያ 13 1881
ያረፉበት ቀን ሚያዝያ 22 1937
ፓርቲ ብሔራዊ ሶሻሊስት ጀርመን ሰራተኞች ፓርቲ
ዋና ማዕረጎች
  • የብሔራዊ ሶሻሊስት ጀርመን ሰራተኞች ፓርቲ መሪ
  • የጀርመን ቻንስለር


ሕይወት

ሂትለር በሚያዝያ 13 ቀን 1881 ዓ.ም. (20 አፕሪይል 1889 እ.ኤ.አ.) በዛሬይቷ ኦስትሪያ ተወለደ። በሚያዝያ 22 ቀን 1937 ዓ.ም. (30 አፕሪይል 1945 እ.ኤ.አ.) በርሊን ውስጥ ከአንድ ቀን በፊት ካገባት ሚስቱ ኤቫ ብራውን ጋር የራሱን ህይወት አጠፋ።

1925 ዓ.ም. መጀመርያ የሂትለር ናዚ ወገን ከጓደኞቹ ወገን ጋር በራይክስታግ ምክር ቤት ትብብር መንግሥት ለመሥራት በቂ መንበሮች አልነበራቸውም። ተቃራኒዎቻቸው የኰሙኒስት ወገን 17% መንበሮች ስለ ነበራቸው የሂትለር ወገኖች የድምጽ ብዛት ሊያገኙ አልተቻላቸውም ነበር። በዚያው ዓመት ግን ከምርጫው ትንሽ በፊት የራይክስታግ ሕንጻ በእሳት ተቃጠለ። ይህ የኰሙኒስቶች ሥራ ነው ብለው የሂትለር ወገን ኰሙኒስት ፓርቲ ቶሎ እንዲከለከል አደረጉ። ስለዚህ ከምርጫው በኋላ የኰሙኒስትን መንበሮች ስለ አጡ የሂትለርም ወገኖች አሁን ከ50% መንበሮች በላይ ስላገኙ፣ የትብብር መንግሥት ሠሩና ወዲያው በድንጋጌ አቶ ሂትለር ባለሙሉ ሥልጣን አደረጉት።

ሂትለር የጻፈው የርዮተ አለሙ ጽሑፍ «የኔ ትግል» (Mein Kampf) ሟርት ብቻ ነው። ለመጥቀስ ያህል፦ «ትኩረቴ ወደ አይሁዶች ስለ ተሳበ፣ ቪየናን ከበፊት በሌላ ብርሃን ለማየት ጀመርኩ። በሄድኩበት ሁሉ አይሁዶችን አየሁዋቸው፤ በብዛትም እያየኋቸው፣ ከሌሎች ሰዎች ፈጽሞ እንድለያቸው ጀመርኩ።»... «የግዛቱ (ኦስትሪያ-ሀንጋሪ) ዋና ከተማ የከሠተውን የዘሮች ውሑድ ጠላሁት፤ የዚህን ሁሉ የቼኮች፣ ፖሎች፣ ሀንጋርዮች፣ ሩጤኖች፣ ሰርቦች፣ ክሮዋቶች ወዘተ. የዘሮች ድብልቀት፤ በሁላቸውም መካከል፣ እንደ ሰው ልጅ መከፋፈል ሻገቶ፣ አይሁዶችና ተጨማሪ አይሁዶች።»

ፖለቲካ

በነበረው ዘረኛ አስተዳደሩ 6 ሚሊዮን የአውሮፓ አይሁዶችን እና 5 ሚሊዮን ሌሎች የተለያዩ ሀገራት ህዝቦችን (በተለይም ስላቮችን) በገፍ (በሆሎኮስት) አስጨርሷል።

በሂትለር ሥር የናዚዎች ፍልስፍና በሂንዱኢዝም እንደሚገኘው በዘር የተከፋፈለ ካስት ሲስተም መመሥረት አይነተኛ ነበር። «አርያኖች» የተባሉት ዘሮች በተለይም የጀርመናውያን ብሔሮች ከሁሉ ላዕላይነት እንዲገኙ አሠቡ። ይህ ዝብረት የተነሣ በርግ ቬዳ ዘንድ በ1500 ዓክልበ. ያህል ወደ ሕንድ የወረሩት ነገዶች «አርያን» ስለ ተባሉ ነው፤ በጥንትም «አሪያና» የአፍጋኒስታን አካባቢ ስም የዘመናዊው ኢራንም ሞክሼ ነበር። በናዚዎቹ እንደ ተዛበው ግን ታሪካዊ ባይሆንም የ«አርያኖች» ትርጓሜ ጀርመናውያን ብቻ ነበሩ፤ ስላቮች (በተለይ የሩስያና የፖሎኝ ሕዝቦች) ግን አርያኖች ሳይሆኑ እንደ ዝቅተኞች ተቆጠሩ። የሂትለር እብደት እየተራመደ በ1926 ዓም የሀንጋሪ ሕዝብ ደግሞ «አርያኖች» ተደረጉ፣ በ1928 ዓም የጃፓን ሕዝብ እንኳን በይፋ «አርያኖች» ተደረጉ፤ በ1934 ዓም የፊንላንድ ሕዝብ ወደ «አርያኖች» በሂትለር ዐዋጅ ተጨመሩ። በሙሶሊኒ ሥር የፋሺስት ጣልያኖች እኛም አርያኖች ነን ቢሉም ጣልያኖች አርያን መሆናቸው በናዚዎች ዘንድ መቸም አልተቀበለም ነበር።

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.