አዲስ ከተማ

አዲስ ከተማኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ ካሉት ዐሥሩ ክፍለ ከተሞች ውስጥ አንዱ ነው። እስከ እ.ኤ.አ 2011 ባለው መረጃ መሠረት የሕዝብ ብዛቱ 271, 664 ነው።[1]

አዲስ ከተማ
ክፍለ ከተማ
አዲስ ከተማ (በቀይ) ከአዲስ አበባ መሃል
የሕዝብ ብዛት
    አጠቃላይ 271,664

መልከዓ-ምድራዊ አቀማመጥ

አዲስ ከተማ በአዲስ አበባ ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ ላይ የሚገኝ ሲሆን በሰሜን ጉለሌ ፣ በምስራቅ አራዳ ፣ በደቡብ ልደታ እና ደግሞ በምዕራብ ኮልፌ ቀራንዮ ያዋስኑታል። የአፍሪካ ታላቁ ክፍት ገበያ የሆነው መርካቶም በዚሁ ክፍለ ከተማ ውስጥ ነው የሚገኘው።

ዋቢ ምንጮች

  1. "Addis Ketema" በእ.ኤ.አ ኖቬምበር 24 ቀን 2012 የተወሰደ።
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.