አክሻክ
አክሻክ የሱመር ጥንታዊ ከተማ ነበር። ሥፍራው በአካድ ስሜን ጠረፍ ጤግሮስና ኤፍራጥስ ወንዝ በሚቀራረቡበት አካባቢ ቢሆን፣ ፍርስራሹ ገና ስላልተገኘ ግን ቦታው በልክ እርግጠኛ አይደለም።
የዱሙዚድ ሕልም በተባለ ሱመራዊው ትውፊት ሰነድ መሠረት፣ ረሃብተኛ ሰዎች ከአክሻክና ከሌሎች ከተሞች በአመጽ ወጥተው የኡሩክን ንጉስ ዱሙዚድ፣ አሣ አጥማጁን ከዙፋኑ አወደቁት።[1] በኋላ ዘመን (2200 ዓክልበ. ግ.) ሌላ የኡሩክ ንጉሥ ኤንሻኩሻና አክሻክን በዘበዘ። የላጋሽም ንጉሥ ኤአናቱም የአክሻክን ንጉሥ ዙዙን እንዳሸነፈው ከጽላቶች ይታወቃል።[2]
በሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ፣ የአክሻክ ነገሥታት ለጊዜው የመላ ሱመር ላዕላይነት ያዙ። ከነኚህ ነገሥታት የአንዱ ብቻ ስም እርሱም ፑዙር-ኒራሕ ከሌላ ምንጭ ይታወቃል። በአንድ ዜና መዋዕል ዘንድ፣ በዚህ ፑዚር-ኒራሕ ዘመነ መንግሥት፣ ወታደሮቹ የዐሣ መሥዋዕት ከቤተ መቅደስ ስለ ከለከሉ፣ የማርዱክ ቄሳውንት ዘውዱን ከፑዚር-ኒራሕ ቃሙና ከኪሽ ለሆነችው ለአንዲት ባለ ቡና ቤት ኩግ-ባው ሰጥተውት እርስዋ የሱመር ንግሥት ሆነች፤ ላዕላይነቱም ያንጊዜ ከአክሻክ ወደ ኪሽ ተመለሰ።
የአካድ ንጉሥ ሻርካሊሻሪ በ2019 ዓክልበ. ግድም በኤላማውያን ላይ በአክሻክ በተደረገ ውግያ ድል አደረጋቸው።
- Dumuzid's dream - ETCSL
- William J. Hamblin, Warfare in the Ancient Near East to 1600 BC , Routledge, 2006, ISBN 0-415-25589-9
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.