አቶም
አቶም ወይም አተም ሁሉም ቁስ የተገነባበት መሰረታዊ እኑስ ነው። እንደ ግዝፈታቸው፣ መጠናቸው የተያየ ስም ያላቸው ብዙ አይነት አተሞች አሉ። እነዚህ የተያዩ አይነት አተሞች የኬሚካል ንጥር ይባላሉ። ለምሳሌ ወርቅ አንዱ የንጥር አይነት ነው።
አተም | ||||
---|---|---|---|---|
የሂሊየም አተም
ጥቁሩ አሞሌ መስመር (10−10 m or 100 pm)ን ይወክላሉ። | ||||
ክፍፍሎች | ||||
| ||||
ጸባዮች | ||||
|
አተሞች ለአይን እማይታዩ፣ በጣም ደቃቅ ቢሆኑም ትክክለኛ መጠናቸው ግን ከንጥር ንጥር ይለያያል። በአጠቃላይ መልኩ አተሞች ከ 0.1 እስከ 0.5 ናኖ ሜትር ስፋት ሊኖራቸው ይችላል
አብላጫውን ጊዜ አተሞች ብቻቸውን አይገኙም። ይልቁኑ አንዱ አቶም ከሌላ አቶም ጋር በመጋጠም ሞልኪዩል የተሰኘውን እኑስ ይፈጥራሉ። ለምሳሌ ሁለት የሃይድሮጅን እና አንድ የኦክሲጅን አተሞች ሲጋጠሙ የውሃ ሞልኪዩልን ይፈጥራሉ።
አተሞች በራሳቸው ከ3 አንስተኛ እኑሶች የተሰሩ ናቸው። እነዚህም ኤሌክትሮን፣ ፕሮቶን እና ኒውትሮን ይባላሉ። ፕሮቶኖችና ኒውትሮኖች አንድ ላይ ሆነው በአቶሙ መሃል ተጠጋግተው ሲቀመጡ የአተሙን ኒኩሊየስ ይፈጥራሉ። ኤሌክትሮኖች በበኩላቸው ይህን ኒኩሊየስ በደመና መልክ ከበው ይገኛሉ። ኤሌክትሮኖች ምንም እንኳ ኒኩሊየሱን እየከበቡ ቢሽከረከሩም ከኒኩሊየሱ በረው እንዳይጠፉ የኤሌክትሮመግነጢስ ጉልበት አዋዶ ይይዛቸዋል።
በአተም ውስጥ የሚገኙት የፕሮቶን፣ ኒውትሮንና እና ኤሌክትሮን ብዛቶች ያ አተም ምን ንጥር እንደሆነ ይወስናል። ለምሳሌ አንድ አቶም 1 ፕሮቶን፣ 0 ኒውትሮን እና 1 ኤሌክትሮን ካለው ሃይድሮጅን ይሆናል፣ በአንጻሩ 16 ፕሮቶን፣ 16 ኒውትሮን እና 16 ኤሌክትሮን ካለው ድኝ (ሰልፈር) ይሆናል ማለት ነው።
አተሞች እርስ በርሳቸው ሳይጋፉ ሰፋ ብለው ሲቀመጡ ጋዝ ወይንም አየር ይሆናሉ። በተቃራኒ፣ ጭፍግ ብለው አንድ ቦታ ላይ ሲገኙ እና መንቀሳቀስ እሚችሉ በመንቀጥቀጥ ከሆነ ጠጣር ነገር ይሆናሉ።
እቶን የአቶም እሳት በአቶም ፉዝዮን ወይም አቶምን በመክፈል የሚገኝ እጂ-ትልቅ ኃይል ነው።
ማጣቀሻ
ተጨማሪ ንባቦች
- http://web.jjay.cuny.edu/~acarpi/NSC/3-atoms.htm Archived ዲሴምበር 23, 2012 at the Wayback Machine
- http://www.watertown.k12.wi.us/HS/Staff/Buescher/atomtime.asp Archived ሴፕቴምበር 26, 2007 at the Wayback Machine