አቤ ጉበኛ

አቤ ጉበኛ (፲፱፻፳፭ ዓ/ም በባሕር-ዳር አካባቢ፣ ይስማላ ጎጃም ተወልደው - ፲፱፻፸፪ ዓ/ም አዲስ አበባ ላይ አረፉ። ባለቅኔ፤ ደራሲና ገጣሚ የነበሩት አቤ ጉበኛ በስድስት ዓመት ፊደል ቆጥረው ንባብ ከተማሩ በኋላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት ሲከታተሉ ቆዩ። ከዚያም ወደ ደንጎላ ሄደው በቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል።

አቤ ጉበኛ የመጀመሪያ ሥራቸው በማስታወቂያ ሚኒስቴር ሲሆን ቀጥሎም በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተቀጥረው በመንግሥት ሥራ ለስድስት ዓመታት ያህል ካገለገሉ በኋላ ሕይወታቸውን በአብዛኛው የገፉት በደራሲነት ነው። በ1967 እ.ኤ.አ.አዮዋ ክፍለ-ሀገር ወደ ዓለም አቀፍ የጽሑፍ ህብረት ፕሮግራም (International Writing Fellowship Program) ሄዱ።

ከሥራዎቻቸው በከፊሉ፦

  • መስኮት (ግጥምና ቅኔ)
  • እሬትና ማር (ግጥምና ቅኔ)
  • ከልታማዋ እኅቴ (ልብ-ወለድ)
  • ምልክዐም ሰይፈ ነበልባል (ልብ-ወለድ)
  • አንድ ለናቱ (ታሪካዊ ልብ-ወለድ)
  • የረገፉ አበቦች (ልብ-ወለድ)
  • ከመሰፍት ሠራዊት፥ ይጠንቀቅ ሰውነት (ተውኔት)
  • ቂመኛው ባሕታዊ (ተውኔት)
  • የሮም አወዳደቅ (ተውኔት)
  • የራሔል ዕንባ (ተውኔት)
  • የደካሞች ወጥመድ (ተውኔት)
  • አልወለድም (፲፱፻፶፭ ዓ.ም.) (ልብ-ወለድ)
  • የዓመፅ ኑዛዜ (፲፱፻፶፭ ዓ.ም.) (ልብ-ወለድ)
  • The Savage Girl 1964 እ.ኤ.አ. (በእንግሊዝኛ)
  • Defiance 1975 እ.ኤ.አ. (በእንግሊዝኛ)

የአቤ ጉበኛ ቤተሰቦች ይስማላ ጊወርጊስ ኮረንች ባታ ጎጥ በመምትባል ቦታ ይኖራሉ የአቤጉበኛ ትንሽ ወንድም ጌትነት አዛለ ይባላል፡፡

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.