አስዋን ግድብ

የአስዋን ግድብ ደቡባዊግብፅ ከተማ በሆነችው አስዋን ውስጥ የሚገኝ የናይል ትልቅ ግድብ ነው። ከ1950ዎቹ እ.አ.አ. ጀምሮ ሥሙ የሚገልፀው ከፍተኛው ግድብ የሚለውን ሲሆን ይህም በ1902 እ.አ.አ. የተጠናቀቀውን የአስዋን ዝቅተኛ ግድብ አዲስ እና ታላቅ መሆኑን ለማሳየት ነው። ከ1960 እስከ 1970 እ.አ.አ. ነበር ከእንግሊዝ የሀገሪቱን ቅኝ ግዛት ነፃ መሆን ተከትሎ የዚህ ግድብ ግንባታ የተካሄደው። የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ከማሳደግ አንጻር ከፍተኛ ሚና እንዲጫወት ተደርጎ የተገነባው ይኸው ግድብ ከአላስፈላጊ የጎርፍ አደጋዎች ለመጠበበቅ፣ ለግብርና የሚውል የውሃ ክምችት እንዲኖር በማድረግ በመጨረሻም በቂ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲኖር ለማድረግ አስችሏል። ኡህ ግድብ ለግብፅ ምጣኔ ሃብታዊ እድገት እና ባህል ከፍተኛ አስተዋፅዖ አለው።

የአስዋን ግድብ ከጠፈር እንደሚታየው

ከግድቡ መገንባት በፊት ባሉት ዓመታት አካባቢው በተደጋጋሚ የወንዝ ሙላት ያጋጥም ነበር። በዚህ ሙላት የተለያዩ ማዕድናት ከምስራቅ አፍሪካ የወንዙ ምንጭ ሀገራት ተጠራርጎ ይመጣል። ይህም የናይል ወንዝ አካባቢን ከጥንታዊ ግብፆች ጀምሮ ለግብርና ምቹ ያደርገዋል። ይህ የወንዝ ሙላት በጣም ከፍተኛ በሚሆንበት ጊዜ የተተከሉ አዝዕርቶችን እንዳለ ጠራርጎ ሊወስድ ይችላል። እንዲሁም ወንዙ በጣም ዝቅ በሚልበት ወይም በሚደርቅበት ጊዜ ደግሞ ድርቅ እና ረሃብ በአካባቢው ይከሰታል። በአሁኑ ጊዜ ግን የሀገሪቱ የህዝብ ቁጥር በመጨመሩ እና እነዚህን መሰል አደጋዎች የመከላከል እና የመቋቋም ብቃቱን እያዳበረች በመምጣቷ ለጥጥ ምርት ተጨማሪ ውሃ ማጠራቀም ተችሏል። ይህም የተጠራቀመ ውሃ የወንዙ መድረቅ በሚከሰትበት ጊዜ ጥቅም ላይ ይውላል።

የግንባታ ታሪክ

የዚህ ግድብ ቀዳሚ የግንባታ ሙከራ የተካሄደው በ11ኛው ክፍለ ዘመን ነበር። በዚህ ጊዜ የኢራቅ ተወላጅ የሆነው መሃንዲስ ኢብን አል ሃያትም (እንግሊዝኛ: Ibn al-Haytham) በጊዜው በነበሩት የሃገሪቱ ከሊፎች ፋጢሚድ ከሊፍ እና አል ሃኪም ቢ-አምረላህ ተጠርቶ ነበር።[1] ይህ የመጀመሪያው የግድቡ ግንባታ ሙከራ ሲሆን በመስክ ስራ ላይ አመርቂ ውጤት ባለማምጣቱ እና የጊዜውን ሀገረ ገዢዎች ቁጣ በመፍራቱ የአዕምሮ ጤና መታወክ ደርሶበት በቤት ውስጥ እስር ከ1011 እ.አ.አ. እስከ አልሃኪም ሞት 1021 እ.አ.አ. ድረስ እንዲቀጣ ተደርጎ ነበር። በዚህ ጊዜ ነበር ተጽዕኖ አሳዳሪ የሆነውን (እንግሊዝኛ)Book of Optics የተሰኘውን የጻፈው።

የአስዋን ዝቅተኛ ግድብ

የ1882 እ.አ.አ. የእንግሊዝ ግብፆችን ወረራ ተከትሎ ነበር እንግሊዝ በ1898 እ.አ.አ. የግድቡን ስራ የጀመረችው። ግንባታው በ1902 እ.አ.አ. ተጠናቆ ክፍት የሆነው ዲሴምበር 10፣ 1902 ሲሆን ሙሉ ዲዛይን የተደረገው በዊሊያም ዊልኮክስ ((እንግሊዝኛ) William Willcocks) እና በጊዜው በነበሩ መለስተኛ መሃንዲሶች ነበር።[2]

የአስዋን ግድብ አጀማመር

በ1946 እ.አ.አ. የአስዋን ዝቅተኛ ግድብ በመሙላቱ እና የእንግሊዝ መንግስት ተጨማሪ ግድብ አስፈላጊ መሆኑን በማመኑ ይህን ግድብ ለሶስተኛ ጊዜ ከማራዘም ይልቅ በወንዙ 7 ኪሎ ሜትር አካባቢ ከፍ ብሎ አዲስ ግድብ ለመስራት ተወሰነ። ቀጥሎ በተከሰተው የፖለቲካ ለውጥ የነበረውን አሃዳዊ አገዛዝ በጋማል አብደል ናስር በሚመራው እንቅስቃሴ በማስወገድ እና የ1936ቱ የአንጎሎ ግብጾች ስምምነት ((እንግሊዝኛ):Anglo-Egyptian Treaty of 1936) በማድረግ ለዋናው ግድብ እ.አ.አ. በ1954 ፕላን ወጣ።

የአስዋን ግድብ እይታ

ማጣቀሻዎች

  1. http://www.sciencemag.org/cgi/content/full/297/5582/773
  2. "Archive copy". Archived from the original on 2005-05-13. በ2011-04-04 የተወሰደ.
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.