አራት
አራት በተራ አቆጣጠር ከሦስት የሚከተለው ቁጥር ነው።
ምልክቱ ከግዕዝ እንደ ተወረሰ ፬ ነው፣ ይህም ከግሪክ አልፋቤት ፬ኛው ፊደል ደልታ (በትልቁ «Δ») እንደ ተወሰደ ይታመናል።
በብዙ ልሳናት የሚገኘው ምልክት 4 ከሕንዳዊ ቁጥር ምልክቶች ተደረጀ። እነዚህ ምልክቶች በአውሮፓ ከ968 እና 1550 ዓም መካከል እየተደረጁ ተቀባይነት አገኙ። ከዚያ አስቀድሞ በሮማውያን ቁጥር ምልክቶች የ«አራት» ምልክት «IV» (ወይም «iv») ነበር።
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.