አራም (የሴም ልጅ)

አራም ሴም (ዕብራይስጥאֲרָם) በመጽሐፍ ቅዱስ ኦሪት ዘፍጥረት (ምዕ. 10) መሠረት የኖህ ልጅ ሴም ከወለዱት ልጆች አንድ ሲሆን የዑፅሁልጌቴርሞሶሕ አባት ይባላል።

በጥንቱ ታሪክ ጸሐፊዎች ዘንድ፣ ይህ አራም የስሜን መስጴጦምያና የሶርያ ሕዝብ የአራማውያን አባት ነበር። በኤብላ ጽላቶች ላይ (2300-2100 ዓክልበ. ግድም) «አራሙ» እና «አርሚ» የሚሉ ስያሜዎች ይገኛሉ፤ «አርሚ» የሐላብ (አሌፖ) ስም ነበር። በ2034 ዓክልበ. ያሕል በአካድ ንጉሥ ናራም-ሲን በስሜን ተራሮች በተደረገው ዘመቻ «የአራም አለቃ ዱቡል» እንደማረከው ይመዘገባል።[1] የአራም ሕዝብ ወይም አገር ደግሞ በማሪ ጽላቶች (1900 ዓክልበ. ግድም) እና በኡጋሪት ጽላቶች (1300 ዓክልበ. ግድም) ታይተዋል። ሆኖም እነዚህ ስያሜዎች ትርጉሞች ለሊቃውንት ክርክር ሆነዋል፤ የአራም ሕዝብ መኖሩ ከ1100 ዓክልበ. ጀምሮ በእርግጥ ይታወቃል።

መጽሐፈ ኩፋሌ (9፡19) መሠረት፣ የኖህ ልጆች ምድሪቱን ሲያከፋፈሉ የአራም ልጆች የወረሱት ርስት ከኤፍራጥስና ከጤግሮስ ወንዞች መካከል ያለው አገር ሁሉ ያጠቅልል ነበር። ይሁንና በታሪካዊው ዘመን አራማውያን በተለይ በዚያ አቅራቢያ ስሜን ሠፍረው ነበር።

በብሉይ ኪዳን የተጠቀሰው ካራንንም ከተማ የጠቀለለው ሀገር «አራም-ናሐራይን» (የሁለት ወንዞች አራም) እንዲሁም በአካባቢው የተገኙት አራም-ደማስቆአራም-ረሆብ በአራም ልጆች እንደ ተመሰረቱ ይታመናል።

ደግሞ የሴም ልጅ አራም በማንዳያውያን ሃይማኖት እንደ ነቢይ ሆኖ ይከብራል።

  1. Year-Names for Naram-Sin
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.