አልወለድም
«አልወለድም» በደራሲ አቤ ጉበኛ ብዕር ተከሽኖ የቀረበና በ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. ለሕትመት የበቃ ልብ ወለድ መጽሐፍ ነው። በ ፲፱፻፷፮ ዓ/ም ዳግም ለኅትመት የበቃው እና አብዮቱ በሀገሪቱ ሲቀጣጠል በኅብረተሰቡ ዘንድ በከፍተኛ ሁኔታ የተነበበው ‘አልወለድም’ ማንንም ሰው ከእናቱ ማሕጸን ጀምሮ ምኞትና ጥንቃቄ ሊለየው እንደማይገባ የሚያትት ሲሆን በመታየት ላይ ያለው እውነታ ግን አዳጋች የሆነና የሰው ዘር በድህነት ተወልዶ፣ አድጎ እና ኑሮው በድህነት እንደሚያልፍ ያሳያል። እንዲህ ያለው ሁኔታ አግባብ አለመሆኑንም ይቃወማል። [1] መጽሐፉ የሰው ልጅ የሚደርስበትን መከራ በመቃወም ይሞግታል። የሰው ልጅ መብት በአግባቡ መጠበቅ እንዳለበት ያስረዳል።
ማጣቀሻ
- ናሽናል ቢብሊዮግራፊ ቡድን፣ መዝገበ ሕትመት ዳሰሳ፣ ቅፅ ፳፭፣ ቁጥር ፭፣ ፳፻ ዓ.ም.፣ ገፅ ፲፬ Archived ጁላይ 20, 2011 at the Wayback Machine
- የኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር ለ’ሚሌኒዬም’ ካሳተመው አጀንዳ፤ http://www.ethioreaders.com/index.php
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.